Monday, August 15, 2016

ወያኔ 
እነሆ እኛ ኢትዮጵያዉያን ህብረት፣ መደጋገፍ፣ ስምምነትና አርቆ አሳቢነት 
የሚጠይቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ያለፉት ዓመታት የወያኔውን ጥቁር ሥርዓት ምንነት አሳይቶናል። ይህንን ብቻ አይደለም፤ በአምባገነን ሥርዓትና ለቅኝ ገዥዎች በባንዳነት በሚያድር ሥርዓት መካከል ያለውን ልዩነትም በሚገባ አሳውቆናል። የንጉሡ ዘመን ኋላ ቀር ነበር። የደርግ ዘመን አምባገነን ነበር። በሁለቱም ሥርዓት ወቅት ግን ሃገር ነበረች። ኢትዮጵያ እስከ ባህረ በሯ ሉዓላዊ እስከ ሕዝቦቿ ክቡር ነበረች። ዛሬ ለየት ያለ ነው። ወያኔ ዘረኛ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሙስናዊ አምባገነን ሥራዓት ቋሚ ተጠሪ ስብስብ ተቋም ብቻ አይደለም። ወያኔ "የአናቁረህ ግዛ" ግፍ አራማጅ ብቸኛ የቀማኞች ድርጅት ብቻ አይደለም። ወያኔ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለውጭ ባለሃብቶች የሸበሸበ የኃጢአተኞችና "የአስረሽ ምቺ" ዳንኪረኞች፣ መዝባሪዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሁሉም የኃጢዓት ሥርዓቶች ድምር ነው። ወያኔ ድንገት ከተሰባሰበበት ደደቢት ሸለቆ ተንከባሉ ሠይጣን ዋሻ ውስጥ ለአመታት ከርሞ ዲያቢሎስ ሳያኝክ የተፋው የርኩስ ሥርዓት ቁንጮ ነው። እድሏ ሆኖ ቅድስት ኢትዮጵያ የዚህ ሥርዓት ተሸካሚ ሆናለች። እንዲያ እንዳልተከበረች፣ እንዲያ እንዳልተፈራች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ቅርጫ ቀረበች። ሥርዓቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በቁሟ የገነዘ፣ ሕዝቧን ያስጨነቀ መሪር ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከዚህ ሥርዓት የሚገላግላት ቆራጥነትና በህብረት መነሳት ብቻ ነው። ህዝብን በመርዘኛ ራዕይ ሰልቦ፣ ወጣቱን በሥራ አጥነት አጠውልጎ ለስደትና ሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ፣ ነዋሪውን በልማት ስምና በከተማ ማስፋፋት እያፈናቀለ ሕዝብን በቅኝ ገዥዎች ቋንቋና በምጣኔ ኃብት እድገት እያደናገረ የሃገሪቱን ሃብት መዝብሮ ወደ ውጭ በማሸሽና በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በጥቂቶች ስም ሃብት እያከማቸ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊገዛ የሚቃጣ ዘመነኛ የግፍ ሥርዓት አራማጅ ወያኔ ብቻ ነው።

Thursday, August 11, 2016

ነሃሴ ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ገዢው ፓርቲ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የጸጥታ ሃይሉን በብዛት በማሰማራት ውጥረቱን አባብሶታል። የፌታችን ቅዳሜ እና እሁድ ተቃውሞ ይካሄድባቸዋል በሚባሉት በርካታ የ አማራ ክልል ወረዳዎች ብዛት ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፌደራል ፖሊሶች እየገቡ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ሊያስተባብሩ ይችላሉ የተባሉት ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው። በተለይ በደብረማርቆስ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደርሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳርም እንዲሁ የፊታችን እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል ተብሎ እየተነገረ መሆኑን ተከትሎ ወታደሮች ጥበቃቸውን አጠናክረዋል። በዛሬው እለት አንዳንድ ንግድ ድርጅቶችና የትራንሰፖርት መኪኖች እንቅስቃሴ ቢጀምሩም አብዛኛው ወጣት ከወታደሮች እይታ ውስጥ ላለመግባት ጊዜውን በቤቱ ማሳለፍን መርጧል። በአንድ ላይ ሰብሰብ ብለው መንገድ ላይ የተገኙ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። የክልሉ ጤና ቢሮ ሰራተኞች የታሰሩት ካልተፈቱ ስራ አንጀምርም ማለታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ክልሉን በብቃት አልመሩም በሚል ወሳኝ የሚባሉትን ጉዳዮች የፌደራል ባለስልጣናት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ አቶ ገዱን በሂደት ከስራ እንቅስቃሴ ውጭ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አብዛኛውን የክልሉን እንቅስቃሴ በፌደራል ደረጃ በሚሰሩ የህወሃት ታማኞች ለመምራት የሚያስችል አሰራሮች መተግበር ጀምረዋል። በወልድያ ዛሬ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንና ባለንብረቶችን ለመሰብሰብ የተደረገው ሙከራ እንዲበተን ተደርጓል። በሰሜን ወሎ ዋና ከተማ ወልድያ ፣ በባህል አዳራሽ የተጀመረው ስብሰባ በክልሉ የትራንስፖርት ሃላፊ የተመራ ሲሆን ፣ ከ200 ያላነሱ ሹፌሮችና ባለሃብቶች ብቻ በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ስብሰባው በጭቅጭቅ መሞላቱን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች አዳራሹን ለቀው የወጡ ሲሆን ፣ እንደገና በልመና 30 የሚሆኑ ሰዎች ስብሰባውን ተካፍለዋል። በመጨረሻም የጸጥታ ሃላፊው አቶ ሙልቀን ማርዬ በእሁድ ስልፍ ላይ እንዳትወጡ በማለት መስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ተመሳሳይ ስብሰባዎች በከተማዋ የተለያዩ ቀበሌዎች ተካሂዷል። በላሊበላ ከተማም እንዲሁ ካድሬዎች በየፅ/ቤቱ፣በየቀበሌውና በየትምህርት ቤቱ ህዝቡን በመሰብሰብ በእሁዱ ሰላማዊ ሰለፍ ብትሳተፉ ወዮላችሁ እያሉ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ በርካታ የገጠር ሚኒሻዎች እና የአካባቢ ፖሊሶች ከተማይቱን የወረሩ ሲሆን አቶ ግርማ የተባለ በልስ ስፌት የሚተዳደር ሰው ትቀሰቅሳለህ በሚል ተይዞ ታስሯል። በደብረብርሃን ከተማም ተመሳሳይ ስብሰባ ተካሂዶ ተበትኗል። በከተማዋ የጸጥታ ሃይሎች እየዞሩ ህዝቡን በማስፈራት ላይ ናቸው። በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ሲሞክሩ በፖሊሶች የተዋከቡ ሲሆን፣ የተቃውሞውን ሰልፍ በሳምንቱ መጨረሻ ለማካሄድ እንዳቀዱ ተናግረዋል። ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ የታፈሱ 1 ሺ የሚሆኑ ወጣቶች በአዋሽ አርባ መታሰራቸውን ለማውቅ ተችሎአል። የደህንነት ሃይሎች የታሰሩትን ለመጠየቅ የሚሄዱ ሰዎችን ገንዘብ ስጡንና እንፈታቸዋለን ማለት መጀመራቸውን ለጥየቃ የሄዱ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ድርጊቱ ያስገረማቸው የእስረኞች ቤተሰቦች ፣ “ደህንነቶች የሚጠይቁት ገንዘብ ማንኛውም ደሃ ህዝብ ሊከፍለው የማይችለው ነው” ካሉ በሁዋላ ፣ ደህንነቶች ሁኔታው አስግቷቸው ገንዘብ መሰብሰብ የጀመሩ ይመስለናል ሲሉ ትዝብታቸውን አክለዋል።

Monday, August 8, 2016

ሰበር ዜና በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ሰሮቃን ለቀው በመውጣት በየጫካው መሽገዋል። ሴቶችና ህጻናት ሰሮቃ ከተማ ለቀው ወጥተዋል። ትናንት በሚሊሺያዎችና በወታደሮች መካከል የነበረው ፍጥጫ በሽማግሌዎች እንዲበርድ ቢደረገም፣ ገዢው ፓርቲ ራሱ ያስታጠቃቸው አርሶአደር ታጣቂዎች ከእንግዲህ በህወሃት አንገዛም በማለት ጫካ በመግባታቸው በማንኛውም ጊዜ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3 ታንኮች እና በ6 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮችም ሰሮቃን ለቀው ወደ ማክሰኚት አቅጣጫ በማምራት ላይ ይገኛሉ። ከዳንሻ የመጣ ጦር ሰሮቃ የነበረውን ጦር ተክቶ ከተማዋን ተቆጣጥሯል። ከጎንደርና ሁመራ የተነሳ ጦር ወደ አርማጭሆ እየሄደ ነው። በትክል ድንጋይ አካባቢ 7 ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ተገድለዋል። በሰሜን ጎንደር ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

Tuesday, August 2, 2016

ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና

ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተጻፈውና በቅጅ ለኢሳት የተላከው ደብዳቤ ፣ “ በእብሪተኛ ገዢዎች እየተፈጸመ ያለው ግፍ በሃገርና በህዝብ ላይ የደገሰውን የሞት ድግስ ከማድረሱ በፊት የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሎአል። ደብዳቤው በጎንደር ባለፈው እሁድ ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች በአፋጣኝ መልስ እንዲያገኙ ይጠይቃል። በግፍ ታፍነው የተወሰዱት የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ህዝብ ወኪሎች የሆኑት አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ ጌታቸው አደመ፣ አቶ አለነ ሻማ፣ አቶ መብራህቱ ጌታሁንና ሌሎችም የተጣለባቸውን የህዝብ አደራ አቤቱታ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመንግስት ከማቅረባቸው ውች ሌላ ምንም ከህዝብ እይታ የተሰወረ የሰሩት ወንጀል ሳይኖር ሆን ተብሎ የጥያቄውን መስመር ለማስቀየር የሃሰት ውንጀላ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ይጠይቃል። የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲፈታ፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር በአንድነት የሚኖሩ ቤተሰቦችን አማራ ቅማንት የሚል ከፋፋይ ሴራ በመፍጠር በተለያዩ ጊዜ በሽፋን ጭልጋ ትክል ድንጋይ ሮቢት ማውራና ሌሎች ቦታዎች ለሞቱትና ያለ አገባብ ለታሰሩት ወንድሞችንና እህቶች የሃሳቡ ጠንሳሾች፣ አስፈጻሚና ፈጻሚ ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ሃምሌ 5 2008 ዓም በጎንደር ደህንነትና ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል በመግለጫ ያስተላለፉት መልእክት ፍጹም የተሳሳተና ውሸት በመሆኑ ማስተባበያ በመስጠት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁም ደብዳቤው ይጠይቃል። “ከዚህ በሁዋላ በኦሮምያ ጋምቤላ ቤንሻንጉልና ሌሎችም የኢትዮጵያ መሬቶች በኢትዮጵያውያን የሚቀርቡ ሰላማዊ ጥያቄዎችን በተጠየቁበት በሰላማዊ መልስ ከመስጠት ውጭ ሻዕቢያ ቅጠረኛ ሽብርተኛ የሚል የሃሰት ስም በመለጠፍ እራሱ በሚከፍላቸው ሰራዊቶች፣ በእራሱ ገንዘብ በተገዛ መሳሪያ በማፈን በመግደል ሰላማዊ ጥያቄዎችን ለመድፈቅ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንዲቆምና እንዳይሞከር በጥብቅ እናሳስባላን” የሚለው ደብዳቤው ፣ ለእነዚህ ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠም ጠይቋል። የሳንጃ ነዋሪዎች እና ታጣቂዎች ጎንደር ከተማ ገብተው የተቃውሞ ድምጻቸውን ካሰሙ በሁዋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ምሽት ላይ ህዝቡ በጀግና አቀባባል ተቀብሎአቸዋል። በጎንደር እና በእስቴ ወረዳ በመካነየሱስ ከተማ የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ተከትሎ ተመሳሳይ ተቃውሞች በመጪው እሁድ በባህርዳር ፣ በደብረታቦር እንዲሁም በመካነሰላም በድጋሜ ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። ሰልፎቹ በጎንደር የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመደገፍ የተጠራ ነው።

Friday, July 8, 2016

PM David Cameron was asked by Chris Law MP if in his final days of premiership if he will be asking for Andargachew Tsege's release from Ethiopian prison and return to his family during the final days የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉት መሆኑን ገለጹ።

ኤስፍና ESFNA እና AESA One ታሪካዊ ግብግብ

ኤስፍና ESFNA እና AESA One ታሪካዊ ግብግብ
ከ ሚኪያስ ግዛው
በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ባንዲራዎች ይውለበለባሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ኳሶች ይነጥራሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ድምጻውያን ይዘፍናሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ማልያ የለበሱ ሰዎች ይታያሉ። ሁለቱም ሜዳዎች ግን ልዩነቶች አሏቸው። አንደኛውን ሜዳ ደማቅ ቀለማማ የብርሃን ፍንጣቂ ከቦታል። አንደኛው ሜዳ ላይ ደግሞ ጨለማ ሠፍኗል። በሁለቱም ሜዳ ላይ ተመልካቾች አሉ። ባንደኛው ሜዳ ላይ ጢቅ ብለው የሞላው ሕዝብ ብርሃኑን መልሶ ያንጸባርቃል። በሌላኛው ሜዳ ላይ ደግሞ የተቸረከሙት ጥቂት ሰዎች በዘረኝነቱን ጨለማ ተውጠዋል። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ሰዎች ይታያሉ። ምነው ታድያ አንደኛው ሜዳ ላይ ያሉት ሰዎች እንደ ኃጢዓቱ ምርከኞች ኩርምት አሉ?
እነዚህን ወገኖች ነጻ ማውጣት አለብን። እነዚህን ወገኖች ከጨለማው አውጥተን ወደ ብርሃኑ ለማምጣት ማስተማር፣ መምከር አለብን። ታድያ እንዴት ይሆናል! እኔም ጭንቅ አለኝ!
አዎ - ይህን ሳሰላስል ድንገት ቶሮንቶ (Toronto) ላይ እምዬ ሚኒልክ ምስላቸው ብቅ አለ። በግርማ ሞገሥ የተከበቡት፣ የዋህና ደጉ ንጉሣችን እምዬ ሚኒልክ በፈረሳቸው ዳኛው ላይ ተቀምጠው ድንገት ብቅ ሲሉ ታየኝ። በስታድዮሙ ውስጥ ሌላ ብርሃን ተንጸባረቀ። በምድረ ዓለም ገድላቸው ተነግሮ ያላበቃው የነጻነቱ አባት እምዬ ሚኒልክ "ይህችን ባንዲራ ጠብቋት፣ ብዙዎች ለዚህች ባንዲራ ሲሉ ተሰውተዋል" አሉ በዚያ የዋህ ድምጻቸው። ይህ ድምጽ የስታድዮሙን ግድግዳና የአካባቢውን ሕንጻ በርቅሶ፣ በአየር እየተንሳፈፈ አኤስዋኖች (AESA One)ኩርምት ብለው የቀመጡበት አሌክሳንዴርያ ቨርጂንያ (Alexandria, Virginia)ጨለማው ዋሻ ደረሰ። ድምጹ እንደ ሳይክሎኑ( cyclone) ነፋስ ገረፋቸው፣ ገፈታተራቸው። አዎ እነዚህ በነዋይ ምርኮ ታግደው፣ ቀለብ ተሰፍሮላቸው በጨለማው ውስጥ ዘረኝነቱን ለማድመቅ የተቀመጡ የዋሆች በቶሎ ነጻ ይወጣሉ። የእምዬ ሚኒልክ ድምጽ እንኳንስ ለወገን ለባዕድም ማዕዛ አለው። ነዋይና ስጋቸው በእሳት እንደተበየደ ብረቶች ከተዋሃደው ጥቂቶቹ ቱባ የዘረኝነቱ አዳማቂዎች በቀር ሌሎቹ ቶሎ ነጻ ይወጣሉ።
አሁንም ጭንቅ ይለኛል። በደጉ ዘመን ተንቀባረው ይኖሩ የነበሩት፣ በዘመኑ አጠራር "የዲታ ልጆች" የሚባሉት ግለሰቦች ለምን ለጨለማው ሥራ ተባባሪዎች እንደሆኑ ማወቅ አልቻልኩም። ወያኔ በአብዛናው በሥሩ ያሰለፋቸው ምርከኖች ትላንት "በአማራው ስትጨኮን የነበርህ ነህ" የተባሉ ጥቂት ተላላ ድንባዣሞች ሆኖ ሳለ - ያኔ ተንቀባረው ያደጉ ግለሰቦች ለምን ምርከኞች እንደሆኑ ማሰቡ ያዳግታል። ገንዘቡ አታሏቸው ነው እንዳይባል እኛ የሳር ፍራሽ ሲበዛብን እነሱ ተዝቆ የማያልቅ ገንዘብ ተንተርሰው ያደጉ ቅምጥሉች ናቸው። ሥልጣን ፈልገው ነው እንዳይባል ደግሞ ሥልጣን የያዙ አልያም የባለሥልጣኖች መጋቢ አሽከር ተከታይ ሆኑ እንጂ የነእገሌን ያህል እንኳን ክብር አልተሰጣቸውም። ምንድነው እነዚህን ግለሰቦች ለዘረኝነቱ ጨለማ ተገዥ ያደረጋቸው። ንዋይ፤ ሥልጣን፤ የተወረሰባቸውን ቦታና ቤት ለማስመለስ ወይንስ የዓዕምሮ መላሸቅ? ያ ሁሉ ትምህርት ምነው ላሸቀ እነዚህን ወገኖችም እንዴት አድርገን ነጻ እንደምናወጣ አላውቅም። አንድም ሰው ቢሆን በዘረኝነቱ ጨለማ በምርኮ እንዲሰቃይ አንፈልግም። ለነዚህም ወገኖች መልካም ልብ እንስጣቸው። በጓደኞቻቸው እናስመክራቸው።
ኤስዋን AESA One ሰዎች ከዚህ ውርደት ልትማሩ ይገባል። ሕዝብ በማይደግፈው ነገር ውስጥ ከመሳተፍ ልትቆጠቡ ይገባል። ዲሞክራሲ ማለት የአብዛኛ ሕዝብ የበላይነት ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሳይገባችሁ አይቀርም። ቁጥሩን መገመት ትችላላችሁ። ዘረኝነት አናሳ ነው። ዘረኝነት ኢትዮጵያዊነት አይደለም። ኃያላኑ ሃገሮች ለጊዜዊው ጥቅማቸው ሲሉ ዘረኝነቱን ቢያሞካሹትም እንኳን እናንተ የእምዬ ሚኒልክ ልጆች ልትታለሉ አይገባም። ነገ እንትፍ ብለው ከሚጥሉት ዘረኝነት ጋር ብትወግኑ ነገ የምታዝኑት እናንተው ናችሁ። ለልጅ ልጆቻችሁ ነጻነት ከወዲሁ አስቡበት። የባንዳ ልጅ፤ የምንትስ ልጅ ለምንስ ይባሉ።
ኤስፍና ESFNA እና AESA One የዲያስፖራው ኢትዮጵያው ሌላኛው የግብግብ አውድማዎች ናቸው። ግብግቡ ሰው ከሰው ጋር አይደለም። ግብግቡ ኢትዮጵያዊነት ከዘረኝነት ጋር ነው። ከእግዚአብሄር መንፈስ ጋር አታመሳስሉት እንጂ ሁለቱም መንፈሶች ናቸው። አንዱ ኢትዮጵያዊ መንፈስ፣ አንዱ የዘረኝነቱ የጣር መንፈስ። የኋላ ኋላ የዘረንነቱ የጣር መንፈስ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መሸነፉ አይቀርም። ይህ እውን እስኪሆን ለጥቂት ጊዜ ግብግቡ ይቀጥላል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ ባዲራችን ለዘላለም ትውለብለብ።
ክብር ለአጼ ቴዎድሮስ፣ ክብር ለአጼ ዮሃንስ፣ ክብር ለእምዬ ሚኒልክ

Saturday, April 2, 2016

በ ወያኔ ዘመን................

በ ወያኔ ዘመን................
ባጠቅላይ ሃቀኝነት፣ ደግነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሙስናንና ጉቦን መጸየፍ – እነዚህ የሕዝቡ የመልካም ባህርይ መገለጫ የሆኑት እሴቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጉሮኖ ተወርውረዋል። እነዚህን እሴቶች ዳግም ሊያንጸባርቅ የሞከረ ሁሉ መሳለቅያ ይሆናል። ኬንያና ናይጄርያ በሙስናና ጉቦ ጫፍ ላይ የደረሱ ሃገሮች እየተባሉ ሲነገር ቆይቷል። ኢትዮጵያ ደግሞ በጥቂት ዓመታት ክብረወሰኑን አልፋ የሙስናና ጉቦ ፍልስፍና የተሃድሶ ምድር እንደሆነች ይታወቃል። ይህን የመሳሰሉት ግፎች ናቸው ዛሬ ሕዝቡን ለአመጽ ያነሳሱት። የፍጥ መዛባት፣ እስር፣ ግድያና የምጣኔ ኃብቱ ይዞታ ልዩነት ካልተገደቡ በቀር ሕዝቡን ለመብቱ ከመታገል የሚያቆመው አንዳች ኃይል የለም። የፌደራል መንግሥቱ እጆች አመድ አፋሽዕ ወይም የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ እንዳሉትየኢትዮጵያ ሕዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለትሆኖ አይደለም ይህ ሁሉ አመጽ የበረከተው። ሙስናው፣ የአስተዳደር በደሉ ፡ ኑሮውን አናግተውበት ፡ በድህነትና ሰቆቃ ጅራፍ መገረፉ፣ በአምባገነኖች ውሳኔ ብቻ መነዳቱ አልበቃ ብሎ ቀማኞች መሬቱንና የመሬቱን የተፈጥሮ ገጸበረከት በጠመንጃ አስገድደው በጠራራ ፀሃይ ስለሚዘርፉት እንጂ።እግዚአብሄር ቸር ዘመን ያምጣልን፣ አሜን