ሰበር ዜና በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ሰሮቃን ለቀው በመውጣት በየጫካው መሽገዋል። ሴቶችና ህጻናት ሰሮቃ ከተማ ለቀው ወጥተዋል። ትናንት በሚሊሺያዎችና በወታደሮች መካከል የነበረው ፍጥጫ በሽማግሌዎች እንዲበርድ ቢደረገም፣ ገዢው ፓርቲ ራሱ ያስታጠቃቸው አርሶአደር ታጣቂዎች ከእንግዲህ በህወሃት አንገዛም በማለት ጫካ በመግባታቸው በማንኛውም ጊዜ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3 ታንኮች እና በ6 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮችም ሰሮቃን ለቀው ወደ ማክሰኚት አቅጣጫ በማምራት ላይ ይገኛሉ። ከዳንሻ የመጣ ጦር ሰሮቃ የነበረውን ጦር ተክቶ ከተማዋን ተቆጣጥሯል። ከጎንደርና ሁመራ የተነሳ ጦር ወደ አርማጭሆ እየሄደ ነው። በትክል ድንጋይ አካባቢ 7 ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ተገድለዋል። በሰሜን ጎንደር ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።