Monday, August 15, 2016

ወያኔ 
እነሆ እኛ ኢትዮጵያዉያን ህብረት፣ መደጋገፍ፣ ስምምነትና አርቆ አሳቢነት 
የሚጠይቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ያለፉት ዓመታት የወያኔውን ጥቁር ሥርዓት ምንነት አሳይቶናል። ይህንን ብቻ አይደለም፤ በአምባገነን ሥርዓትና ለቅኝ ገዥዎች በባንዳነት በሚያድር ሥርዓት መካከል ያለውን ልዩነትም በሚገባ አሳውቆናል። የንጉሡ ዘመን ኋላ ቀር ነበር። የደርግ ዘመን አምባገነን ነበር። በሁለቱም ሥርዓት ወቅት ግን ሃገር ነበረች። ኢትዮጵያ እስከ ባህረ በሯ ሉዓላዊ እስከ ሕዝቦቿ ክቡር ነበረች። ዛሬ ለየት ያለ ነው። ወያኔ ዘረኛ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሙስናዊ አምባገነን ሥራዓት ቋሚ ተጠሪ ስብስብ ተቋም ብቻ አይደለም። ወያኔ "የአናቁረህ ግዛ" ግፍ አራማጅ ብቸኛ የቀማኞች ድርጅት ብቻ አይደለም። ወያኔ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለውጭ ባለሃብቶች የሸበሸበ የኃጢአተኞችና "የአስረሽ ምቺ" ዳንኪረኞች፣ መዝባሪዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሁሉም የኃጢዓት ሥርዓቶች ድምር ነው። ወያኔ ድንገት ከተሰባሰበበት ደደቢት ሸለቆ ተንከባሉ ሠይጣን ዋሻ ውስጥ ለአመታት ከርሞ ዲያቢሎስ ሳያኝክ የተፋው የርኩስ ሥርዓት ቁንጮ ነው። እድሏ ሆኖ ቅድስት ኢትዮጵያ የዚህ ሥርዓት ተሸካሚ ሆናለች። እንዲያ እንዳልተከበረች፣ እንዲያ እንዳልተፈራች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ቅርጫ ቀረበች። ሥርዓቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በቁሟ የገነዘ፣ ሕዝቧን ያስጨነቀ መሪር ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከዚህ ሥርዓት የሚገላግላት ቆራጥነትና በህብረት መነሳት ብቻ ነው። ህዝብን በመርዘኛ ራዕይ ሰልቦ፣ ወጣቱን በሥራ አጥነት አጠውልጎ ለስደትና ሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ፣ ነዋሪውን በልማት ስምና በከተማ ማስፋፋት እያፈናቀለ ሕዝብን በቅኝ ገዥዎች ቋንቋና በምጣኔ ኃብት እድገት እያደናገረ የሃገሪቱን ሃብት መዝብሮ ወደ ውጭ በማሸሽና በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በጥቂቶች ስም ሃብት እያከማቸ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊገዛ የሚቃጣ ዘመነኛ የግፍ ሥርዓት አራማጅ ወያኔ ብቻ ነው።