Thursday, December 3, 2015

የአቶ መለስ ራዕይ


የአቶ መለስ ራዕይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስደፈረ፣ ኅልውናዋን የተፈታተነ፣ ታሪኳን ያንቋሸሸ ደረቅ ራዕይዕ ነዉ።
ራዕዩ የሕንድና የአረብ ከበርቴዎችን ያስፈነጠዘ፣ ሼሁንና ሎሌዎቹን ያወፈረ፣ የቅኝ ገዢዎችን ምኞት ያሳካ፣ በርካታ ቀን የሰጣቸውን
ባለስልጣናትና ዘመዶቻቸውን ያባለገ ራዕይ ነበር። በአለም ባንክ ርዳታ የተነጠፈው ጎዳና ረጅም - ግን ደረቅ
የሙስናውንና የኤፈርቱን የዘረፋ ሸቀጥ በተሸከሙ ከባድ መኪኖች የተጨናነቀ ጎዳና ነው። በየመስኩ
የተንጣለሉት ሌብነትና ጉቦ ወለድ ፋብሪካዎቹ የሕዝቡን ኑሮ አላሽቀውታል። ራዕዩ ሃይማኖትን ሳይቀር
የተፈታተነ ሕዝብን ያጠወለገ የክፋት ምንጭ ነበር። ዛሬ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ቀድሞ ተንሰራፍቶ የነበረው
ሙስና ገሃድ ወጥቶ ሙስናውያኑን እያባረረ ነው። በቅርቡ በኦሮምያና ትግራይ ክልሎች ባሉ ትልቁ የሙስና
ዋሻ የመሸጉ ሁሉ ሙቅ ውሃ እንደተደፋባቸው አይጦች ይራወጣሉ። የስባዓዊ መብት ጥሰቱ ይቁም (Stop
human rights violation)፣ አምባገነንነት ይውደም (Down with Dictatorship)፣ ሙስናው ያብቃ (Stop
Corruption)፣ የሚሉ ሰላማዊ መፈክሮች ይዘን ስለወጣን ለስደት የዳረጉን ከቀበሌ እስከ መንግስት አመራር
ያሉ ሁሉ ነገ ተጠያቂዎች ናቸው።
አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃት።

No comments:

Post a Comment