Thursday, February 19, 2015

የካቲት 12
በ1880ዎቹ የአውሮፓ ኢምፔሪያሊስቶች አፍሪካን እና ሌሎቹን የላቲን እና የሩቅ ምስራቅ ሀገሮችን ለመቀራመት ከፍተኛ ፍላጎት እና ተግባራዊ አንቅስቃሴ አደረጉ፡፡በተለይ አፍሪካን ለመቀራመት በጀረመን ተሰብስበው ዕቅድ አወጡ፡፡በዚህ ስሌት መሰረት እንግሊዝ እና ፈረንሳይ 95 በመቶውን የአፍሪካን ቆዳ ሲቆጣጠሩ ሌሎችም የድርሻቸውን ወስደወል፡፡ከአውሮፓ ቅኝ ገዥ ኢምፔሪያሊስቶች ውስጥ ኢትዮጵን መያዝ የጣሊያን ድርሻ ነበር፡፡ስለሆነም በ1888 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ያደረጉት የድፕሎማሲ እና የጦርነት ስትራቴጅ በታለቁ ኢትዮጵያዊ ንጉስ አጼ ምኒልክ በተመራው ሀገርን ከመወራሪ የመታደግ ዘመቻ ለመላው ቅኝ ተገዥ እና ለቅኝ ገዥ ያስደመመ ድል በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ በአድዋ የጦር ሜዳ ተቀዳጁ፡፡ ይህም ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁር ነጭን ያንበረከከበትየዓለም ታሪክ የጠቀየረበት ጣሊያኞችን ጥቁር ማቅ ያስለበስ በአቻ ኢምፔሪያሊስቶች ፊት ያዋረደ ታሪክ ሆነ፡፡
ይህንን ቂም ቋጥረው ለአርባ ዓመታት ራሳቸውን በጦር መሳሪያና በዘመናዊ ወታደራዊ ግንባታ ሲያደራጁ የነበሩት ፍሽስት ወራሪዎች በ1928 ዓ.ም ሀገሪቱን በሶስት አቅጣጫ ወረሩ ለወረራውም እጅግ የዘመኑ የምድር እና የሰማይ የጦር መሳሪያዎችና የመርዝ ጋዝን በመጠቀም ጭምር ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ምንም የዘመነ የጦር መሳሪያ ያልታጠቀውን ምስኪን ኢትዮጵያዊ ባልታሰበ ሁኔታ ድል አደረጉት፡፡ሁኖም በታሪኩ ሽንፈት እና ውረደት አይቶ የማያውቀው ኢትዮጵያዊ እምቢ ለአገሬ እምቢ ለነጸነቴ ብሎ ዱር ቤቴ ብሎ በአርበኝነት ጣሊያንን ሲያረበደብድ ቆይቶ ከአምስት ዓመት በኋላ ድል ሊቀዳጅ ችሏል፡፡ከ1928-1933 ዓ.ም ድርስ ኢትዮጵያን በያዙበት ዘመን የካቲት 12 ለየት ያለ ሪካዊ ክስተት አስተናግዷል፡፡
የካቲት 12 1929ዓ.ም የፍሽስቱ የጦር መሪ ግራዚያኒ የአዲስ አበባን ህዝብ ሰብስቦ ስለ ሮማ መንግስት ታላቅነት የሮማ መንግስት ኢትዮጵያን የሥልጣኔ በረከት ተካፍይ ሊያደረጋት እንደሆነ ድስኩር ሲያሰማ ኢትዮጵያዊነት ስሜት የሚኝተከተክባቸው ሽንፈት የማይወዱት አድዋ ድል ወራሾች ሞገስ አስግዶም እና አብርሃም ደቦጭ ቦንብ በመወርወር ግሪዚያኒን የቆስሉታል፡፡
ዕለቱም የካቲት 12 ነበር ፡፡ግራዚያኒ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ቢደርስበትም ከሞት ተረፈ፡፡በዚህም የተበሳጨው ግሪያዚያኒ በኢትዮጵያዊያን ላይ እልቂት እንድፈጸም ትዕዛዝ ሠጠ፡፡በትዕዛዙ መሰረት በቦነብ በመርዝ ጭስ በእሳት ህዝቡ ተደበደበ ተቃጠለ ታረደ ሙሉ በሙሉ የዐንድ ቤተሰብ አባለት በየት ተዘግቶባቸው ነደዱ፡፡በሶሰት ቀናት ብቻ ከ33,000-50,000 ኢትዮጵውያን በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እልቂት እና ፍጅት ተፈጽሞባቿል፡፡
ይህ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ጥቁር ቀን ተብሎ ይታወቀል፡፡ በፋሽቱ ግፍ ለተፈጸመባቸው ኢትዮጵዊያን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ብዙ ተቋማት ተሰይሞላቸዋል/የካቲት ሆስፒታል፤ የካቲት ትምህርት ቤት ሌሎችም/ ፡፡ታላቁ የሰማዕታት ሀዉልት በስድስት ኪሎ አደባባይ ቁሞላቸዋል፡፡