Wednesday, October 26, 2016

ኢትዮጵያ ስትበታተን ምናምን ለምትሉ ሁሉ!
ኢትዮጵያ መቼም አትበታተንም የትግሉ ባለቤት ህዝቡ ስለሆነ የነጻነት ቻርተርም ሆነ ሌላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ራሱ የሚቀርጸው ነው የሚሆነው።የአርባ ዓመቱ የግራ ክንፉ የትግል ዘይቤና የደደቢቱ ማኒፌስቶ አጥፊና ትውልድን ገዳይ አንድነትን አጨናጋፊ ነው። እነዚህኑ የግራው ክንፍ ፖለቲካ በደርግ ዘመን ለአስራ ሰባት ዓመት በወያኔ ዘመን ለሃያ አምስት ዓመት ባጠቃላይ ለአርባ ዓመት በተግባር አይተን ፈትነናቸው እርባና ቢስነታቸውን ሙሉ በሙሉ አረጋግጠናል። ይህ ትውልድ፣ ሃገር ቤት መከራውን የሚያየው ትውልድና ከጎኑ ያልተለዩት መሪዎቹ ራሳቸው ወደፊት ኢትዮጵያ የምትመራበትን ሠነድ በህብረት ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል። ዛሬ የአማራውና ኦሮሞውን ትግል ተቀናጅቶ የወያኔው ከፋፋይ ማኒፌስቶ መቀዳደዱ ሕዝቡ የደረሰበትን የንቃት ደረጃ ያሳያል። ፖለቲካ ብዙ እምቅ ኃይልና እንቅስቃሴ በመሆኗ ሕዝቡ የራሱን ኢትዮጵያዊ ሠነድ ማዘጋጀት ይችል ዘንድ ላገሪቱ የወደፊት ዕጣ፣ ሠላምና መረጋጋት፣ እድገትና እርምጃ ራዕይ የሌላቸው ምሁራን ወይንም ፖለቲካንና ተግባርን አዛምዶ ማየት የማይችሉ የግራው ትግል ዘይቤ የወለዳቸው ሰዎች ጣልቃ መግባቱን ትተው ይህን ሃገራዊ ኃላፊነት ለባለቤቱ ለሕዝቡ ቢተዉለት መልካም ነው።
አዲሱን ሠነድ የኢትዮጵያ ሕዝብና አብረውት መከራውን የቀመሱት መሪዎቹ ያዘጋጁ። ሠርጎ ገቦች፣ ገዳዮችና አሽቃባጮች ተዉ ሊባሉ ይገባል።

T&T's disscussion on Oromo charter, Oromo transitional government and Or...

የኦሮሚያን ቻርተርን በማዘጋጀት ላይ ነኝ ባለው ጁሀር መሀመድን የሞገተው ጋዜጠኛ ተስፋየ ተሰማ

Tuesday, October 4, 2016

ሰበር ዜና 
በአዲስ አበባ ዙሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ነው።
በአዲስ አበባ አለም ገና በወያኔ ንብረት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡ ወጣቱ መንገዶች እየዘጋ ትግሉን አቀጣጥሎታል፡፡

Saturday, September 24, 2016

The Great Conspiracy against Ethiopia: Part 2 – The TPLF disorders

The Great Conspiracy against Ethiopia: Part 2 – The TPLF disorders

ESAT Special Program Interview with Feyisa Lelisa Fri 23 Sep 2016

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማሪያም ደሳለኝ፣
"አንዳንድ ሰዉ እንደራሱ ነዉ ሰዉን የሚያስበዉ እሱ በራሱ ወስኖ ስለማይሰራ ፈይሳ እንደዛ ያስባል ብሎ ነው ሚገምተዉ፤ ራሴ ነኝ ራሴን የምመራው፤ ሰው አይደለም ሚመራኝ ሰዉ ጽፎ የሰጠኝን እኔ አላነብም።"

Wednesday, August 31, 2016

ሰበር ዜና የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ

ሰበር ዜና
የትግራይ ወጣቶች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ተሰጠ 
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ እና ከፍተኛ የህወሓት ሹማምንቶች እምነት የሚጣልባቸው የፓርቲው ወጣት አባላትን ስብስበው ጠንካራ ትእዛዝ አስተላለፉ::
"በእናቶቾቻችሁ፥ በአባቶቻችሁ፥ በእህት፥ ወንድሞቻችሁ ደምና አጥንት ማንነታቸሁ ተከብሯል:: ደርግ ወንበዴ እያለ ሲጨፈጭፈን መስዋዕትነት ከፍለን በሰላም የምትኖሩበት፥ የምትማሩበት፥ የምትሰሩበት እና በክብር ወጥታችሁ የምትገቡበት ናጽነት አግኝተናል::
አሁን ግን የጥፋት ኃይሎች በሻእቢያ እና ግብጽ በመታገዝ ደርግን መልሰው ሊያመጡብን ትግራዋይ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጀዋል:: ስለዚህ ይህን የመመከት ኃላፊነት በእናንተ ወጣቶች ላይ ተጥሏል::
ወላጆቻችሁ ትምክህተኞችን ጠባቦችን ደምስሰው በኢትዮጵያ ሰላም ልማት እና ዲሞክራሲ አንዳሰፈኑት ሁሉ እናንተም አኩሪውን ታሪክ የመድገም ግዴታ አለባችሁ:: አለበለዚያ የተጋሩ ህልውና አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎም ከላይ የሻእቢያ ከታች የትምክህተኞች ጥቃት መፈንጫ ሆኖ እንደ ሕዝብ የመቀጠል እድል የማይታሰብ ይሆናል:: በተለይ በ አሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ሁከት በተጋሩ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ይህንኑ ያመላክታል::
ይህን አውቃችሁ ህወሓትንም ትግራይንም ከጥፋት በማዳን የተጋሩን ቀጣይነት አረጋገጡ:: ባለራዕዩ መሪያችን መለስ ዜናዊ የጣለብንን አደራ እንወጣ::በእናንተ ፍጹም እምነት አለን::"
በትላንትናው ዕለት ገዢው ስርዓት በግልጽ አማራ ክልል በወታደራዊ እዝ ስር እንደሚሆን በመግለፅ በከባድ መሳሪያ የታገዘ መከላከያ ሰራዊት ወደስፍራው አሰማርቷል ::
ኦሮሚያ ክልል አብዛኛው ክፍሉ በህወሓት ሰራዊት የታጠረ መሆኑ ይታወቃል::
የህወሓት ትእዛዝ ፈጻሚ የሆነው ብአዴን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አያፈነገጠ በመምጣቱ እና ሕዝባዊ ንቅናቄው ላይ የሚጠበቀውን የኃይል እርምጃ ባለመወሰዱ በኦህዴድ አመራሮች ላይ እንደደረሰው የመባረር እጣ የሚገጥማቸው ባለስልጣናት ይኖራሉ:: በተጨማሪ የብአዴን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ በህወሀት ቁጥጥር ስር ይሆናል::

Sunday, August 21, 2016

ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ዋልድባ ፡ ከእሾህ የተጠጉ አጋሞች ከ ሚክያስ ግዛው

                            ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ዋልድባ ፡ ከእሾህ የተጠጉ አጋሞች
                                                 ከ ሚክያስ ግዛው
የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩትን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፎቶግራፎችና ቪዲዮዎች ማየት እወዳለሁ። በተለያዩ አጋጣሚዎች ከልጅ ልጆቻቸው ጋር አብረው ሆነው ፎቶግራፍ ተነስተዋል። ልጆቹ አያታቸው ንጝር ሲያደርጉ ያዳምጣሉ፣ ጉብኝት ሲያደርጉም ያያሉ። ገና ከጨቅላነታቸው የሃገር መሪን ሥራና ኃላፊነት እየተገነዘቡ ያድጋሉ። እርሳቸው ጃንሆይም ቢሆኑ አጼ ሚኒሊክ አጠገብ ፎቶግራፍ ተነስተው እንደነበር አይቻለሁ። አጼ ሚኒልክም አጼ ቴዎድርስን እየተከተሉ አስተዳደርና ፍርድ ተመልክተዋል። ጥሩ ነው፣ መጥፎ ድርጊት አይደለም። እኛም እናትና አባታችንን እየተመለከትን የነሱን ባህርይ ቀድተናል፣ የነሱን ሥብዕና ተላብሰናል። የጃንሆይን ፎቶግራፎች ግን ስመለከት አንድ ነገር ወደ ውስጤ ይወረወራል። ጃንሆይ እነዛን የሚሳሱላቸው እምቦቅቅላዎች ነገ ስደተኞች እንደሚሆኑ ግን ከቶ ያሰቡ አይመስለኝም። እርሳቸው ከአጼ ሚኒልክ የተረከቡትን ሥርዓት እንዲህ በቀላሉ ለልጅ ልጆቻቸው የሚያስረክቡ መስሏቸው ነበር። የአድዋው ጀግና የራስ መኮንን ልጅ፣ ያንን የአጼ ሚኒልክን ስብዕና በዓይን የቃኙ፣ አስተዋይና ብርቱው ጃንሆይ እንዴት የወደፊቱን መተንበይ እንዳልቻሉ ሳስበው ይገርመኛል። የጃንሆይ መንግሥት ሲገረሰስ ልጆቻቸው፣የልጅ ልጆቻቸው ስደተኞችና እስረኞች ሆኑ። ከጃንሆይ ሃገሪቱን የተረከቡት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ለፎቶግራፍ ብዙም ጊዜ አልነበራቸውም። የእፎይታ ጊዜ ስላልነበራቸው ልጆቹን ፎቶግራፍም አለስነሱም። ባለቤታቸውም ብዙ አይታወቁም። ቢሆንም ግን ተሰደዱ። ከደርግ ሥርዓቱን የተረከቡት አቶ መለስ ዜናዊ ግን ከሁለቱ መሪዎች ይልቅ ጮሌ ነበሩ። ለልጆቻቸው ፎቶግራፍ አይደለም የሚያወርሱት። ለልጆቻቸው ገንዘብ ለማውረስ ነው የማኦ ሴቱንግን መጽሃፍ ተንተርሰው ያድሩ የነበረው። የማኦ ሴቱንግ መጽሃፍ ስለገንዘብ አያወራም ግን ሥልጣን ከጠመንጃ አፈሙዝ መወለዱን ያብራራል። የደደቢቱ ፈላስፋ አቶ መለስ ዜናዊም ገንዘብ ከጠመንጃ አፈሙዝ ይወለዳልዕ ሲሉ የማኦን ሃሳብ ጠመዘዙት። ሥልጣን የገንዘብ ምንጭ ነውዕ አሉ አቶ መለስ፣ ገንዘብ የኃጢዓት ሁሉ ምንጭ ነው የሚለውን ዘንግተው። ይህን መጻፌ የታሪኩን ሂደት ለማብራራት እንጂ ሙት ወቃሽ ሆኜ አይደለም።
አቶ መለስ ኢትዮጵያን የሚያህል ትልቅ አገር ማስተዳደር እንደማይችሉ ገና ከጠዋቱ ያውቁ ነበር። አቶ መለስ እነ አጼ አምደጽዮንን፣ አጼ ገላውዲዎስን፣ አጼ ሚኒልክን የሚተካ የአመራር ችሎታ ይቅርና በቅርብ በታሪክ ከሚታወቁት ጀግናው ራስ አሉላ፣ ራስ ጎበና ወይም ራስ መስፍን ጋር እንኳን የሚተካከል ያንዲት ሳንቲም ክፋይ ጀግንነትም ይሁን ማስተዋል እንደሌላቸው ስብዕናቸው ጠንቅቆ ያውቃል። አቶ መለስ ከሻዕቢያ ጋር የተስማሙት ትግራይን ታላቋ ትግራይዕ ብለው ከልለው ወይም ገንጥለው ወደብ ለኢትዮጵያ እያከራዩ ገንዘብ እንደ ውሃ ቦና የሚሰበስቡ መስሏቸው ነበር። ይህን ምስጢር የኤርትራም የትግራይም ሕዝብ አያውቅም። አቶ መለስ ስለ ገንዘብ ሲያስቡ ገንዘቡን ለልጆቻቸው እየሰጡ በውጭ ሃገር እያንደላቀቁ ሊያኖሯቸውም ጭምር አስበው ነበር። ይህ ሃሳብ በማኦ ሴቱንግ መጽሃፍ ላይ እንዴት እንደተጻፈ አላውቅም። አቶ መለስ ግን ትርጉሙ ገብቷቸዋል። አጠገባቸው ካሉት ውስጥ ትልቁ አቦይ ካልሆኑ በቀር ተራ ተጋዳላዮቹ ሊገለጽላቸው አይችልም። የአቶ መለስን ራዕይ የሚያውቁት ባለቤታቸው ብቻ ናቸው። እሳቸውም ቢሆን በድንግዝግዙ ነው።
አቶ መለስ ስለገንዘብና ስደት ሲያውጠነጥኑ የመንገዳቸውን መጀመርያ ያደረጉት መውጫ፣ መላወሻ፣ መፈርጠጭያ፣ መጋለብያ መሬቶችን ማፈላለግ ነበር። ይህን ጊዜ የቅዱሳን ምድሯ ዋልድባ፣ የሰሊጥ አምራችዋ ሁመራ፣ የጀግኖቹ ምድር ወልቃይጥ፣ ጠለምትና ጠገዴ ፈረደባቸው። አቶ መለስ ችግር ከመጣ ወደ ሱዳን ለመጠጋት እነዚህን መሬቶች ከትግራይ ጋር መደባለቅ ሊኖርባቸው ነው። እስከዛው ድረስ ግን ለሟን መሬት ይበዘብዛሉ። ፍርጃ ማለት ይህ ነው። አቶ መለስ የማኦ ሴቱንግን መጽሃፍ ብቻ ሳይሆን የኢጣልያ የቅኝ ግዛት ካርታንም ከየትም አፈላልገው ሲያጠኑት፣ ሲያስተውሉት ይኖሩ ነበር። ኢጣልያ በዘር ከፋፍላ ለመግዛት እንዲያመቻት አልያም ከጦር ስትራቴጂካዊነት አኳያ ወድያና ወዲህ አደበላልቃ፣ ከልሳ አከላልሳ የፈጠረችውን የዘር ክልሎች አቶ መለስ ያገናዝቧቸው ነበር። እነዚህ ናቸው የአቶ መለስ ፍልስፍና ፈር ቀዳጆች፣ የቻይናው ማኦ ሴቱንግ ሥልጣን (ገንዘብ) ከጠመንጃ አፈሙዝ ይወለዳል ና የኢጣልያ የዘር ክልል ካርታ። እነዚህ ናቸው አቶ መለስን በደጋፊዎቻቸው ዘንድ እንደ ናፖሊዎን ስትራቴጂካዊ፣ እንደ አዳም ስሚዝ ልማታዊ፣ እንደ ሆ ቺሚንህ ነጻ አውጭ፣ እንደ ኢንቫዮርሜንቱ ሳይንቲስቶቹ ሊቃዊንት ያስባላቸው። በእርግጥ አቶ መለስ እግዚአብሄር የሰጣቸውን አዕምሮ በመልካም ቢጠቀሙበት ኖሮ ለሃገራቸው ይጠቅሙ ነበር። ይህ አለመሆኑ በጣም ያሳዝናል።
ከወልቃይት ብሎግ ባገኘሁት ማስረጃ መሠረት ከአንገረብ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙት ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋልድባ፣ ጠለምት፣ ሰሜን፣ ዋገራ ከአገው ፈላሻ የተወረሰ የራሳቸው ባህል፣ ኃይማኖትና ቋንቋ እንዳላቸው ነው። እነዚህ ሃገሮች በተከዜ በኩል ከትግራይ ጋር ስለሚዋሰኑ የንግድ ልውውጥ ያደርጉም ነበር። የወቅቱ የአክሱም ትግራይ የበላይነት መንፈስ የግዕዝ ትግሬኛ ቋንቋ በተለይ በወልቃይት ውስጥ እንዲሰርጽ ምክንያት ሆኗል። ጠለምትም ከትግራይ በሚሾመው በሹም ጠለምት በመተዳደርዋ እስከ አስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ ለትግራይ አስተዳደር ትገብር ነበር። የኦሮሞ ሕዝብ ከደቡብ ወደ ሰሜን መስፋፋት ሲጀምሩ የአማራ፣ አንጎትና ሸዋ ንጉሳዊ አስተዳደር ተፋለሰ። ሕዝቡም ከአባይ ማዶ ሰሜናዊ ግዛት ትግራይ አጠገብ መስፈር ጀመረ። ነገሥታቱ ኃይላቸው በመመናመኑ ምክንያት ከጣና ሃይቅ ሰሜን በደንብያና ወልቃይት ሠፋሪ የነበረውን አገውና ፈላሻን በመውረር ክርስትያን ኃይማኖትን በግድ እንዲቀበል አደረጉት። ይህ አዲሱ አካባቢ በአማራ ንጉሳዊ አስተዳደር ስር ተማከለ። ቋንቋቸውም ልሳነ ንጉሥ የሆነው አማርኛ ሆነ። ከዚህ ቀደም የነበረው ምዕራብ ተከዜን አስታኮ የነበረው የትግራይ ገዥዎች ተፅዕኖም ፈጽሞ ተቋረጠ። ይህ ሁኔታ ከዘመነ መሳፍንት አንስቶ በአጼ ቴዎድሮስ፣ በትግራዩ ንጉሥ ዮሃንስ፣ በአጼ ሚኒልክ፣ በኢያሱና ዘውዲቱ፣ በቀዳማው ኃይለ ሥላሴና ደርግ ድረስ አንዳች ለውጥ አልተደረገበትም። ጎንደር የኢትዮጵያ ማዕከላዊነቷ ተቋርጦ ዋና ከተማው አዲስ አበባ ሲዞርም እንኳን ይህ ይዞታ ለውጥ አልተደረገበትም ነበር።
ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጵያን ዳግመኛ ስትወር ከአንገረብ ወንዝ ሰሜን ያሉትን የጎንደር ክፍለ ግዛት ከኤርትራ ጋር ደባለቀችው። ኢጣልያ ይህን ያደረገችው ወታደራዊ የገዥ መሬት ከመያዝ አኳያና በአካባቢው ያለውን የአርበኞች ትግል ለመቆጣጠር ነበር። አካባቢው በተለይም ሰሜን፣ ጠለምት፣ ወልቃይትና ጠገዴ ከጥንት ጀምሮ የአመጽና የሽፍቶች መሰማርያ ነበር ይባላል። ከአንገረብ ወንዝ ደቡብ የሚገኘውም ታሪካዊው አካባቢ እስከ ሱዳን ጠረፍ ኦም ሃጀር ድረስ የሚያካልለው አርማጭሆ ለኢጣልያ አስጊ አካባቢ ነበር። ፊታውራሪ ውብነህ ወይም አሞራው ውብነህና ቢትወደድ አዳነ መኮንን በዚሁ አካባቢ ሸፍተው ኢጣልያን መውጫ መግቢያ ያሳጡ ጀግኖች ነበሩ። ቢትወደድ አዳነ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ሕብረት (ኢዲዩ) መሪ ሆነው ደርግን በመፋለም ላይ እንዳሉ ኢሕአፓ በሰማንያ አራት አመታቸው ሱዳን ድንበር አካባቢ በግፍ ገደለቻቸው።
አቶ መለስ ይህን የኢጣልያ ዘረኛ ካርታ ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ በማዋል ግማሹን በጌምድር ከምዕራብ ትግራይ ጋር አደባለቁ። ለሞቹ የአንገረብ ወንዝ አካባቢዎች ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋልድባና ጠለምት ከትግራይ ጎን የሚገኙ አካባቢዎች በመሆናቸው ከእሾህ የተጠጉ አጋሞች ሆኑ። የትግራይ ትግርኝ የአቶ መለስ ፕሮጀክት ሕዝቡን በማይፈልገው አሳዛኝ ተፅዕኖ ሥር አምበረከከው። ባጠቃላይ አቶ መለስ በምስራቅ ከቀይ ባህር ጋር ለመገናኘት ጢዮን ወይም መርስ ፋትማን ለማካለል እያሰቡ በሌላ በኩል ደግሞ ከሱዳን ጋር ለመዋሰን በጋሽና ሰቲት ወንዝ መሃከል ያሉትን አካባቢዎች በመንጠቅ እንዲሁም እስከ ምዕራብ ወሎ ዋግ ክልልን በማስገባት ገንዘብ የማሰባሰብ ዓላማቸውን ያሳኩ ዘንድ የዕብሪት ራዕያቸውን ከፍ አደረጉ። የሠመረላቸው ሰምሮ የተቀረውን የቤት ሥራ ለተባባሪዎቻቸው አስረክበው እስከ ወድያኛው አሸለቡ።
የአቶ መለስና ተባባሪዎቻቸው የትግራይ ትግርኝ ፕሮጀክት በምን ምክንያት ጋብ አለ። አንደኛ አሜሪካ ሶሻሊስታዊ አስተሳሰባቸውን ካቆሙ ሥልጣን ላይ እንደሚያወጣቸው ለአቶ መልሰ በግልጽ ነገረቻቸው። እሺ በማለታቸው አዲስ አበባ ሚኒልክ ቤተመንግሥት በሰላም ገቡ። ሁለተኛ ከአቶ ኢሳያስ ጋር የተማማሉበት ትግራይን ገንጥሎ ወደብ ሸጦ ገንዘብ የመሰብሰብ እቅዳቸው በሌላ አዲስ እድል ተተካ። መላ ኢትዮጵያን ከያዙ በርካታ እንደውም ካሰቡት በላይ ገንዘብ ስለሚያገኙ ወደብ ሽያጩን ናቁት። ይባስ ብለው ከእቶ ኢሳያስ ጋር በገንዘብ ምክንያት ሲጣሉ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት ገብተው ብዙ ሰዎች ተሰዉ። አሰብ የግመል መፈንጫ ነው የምትሆነውዕ ብለው ወደ ማህል ኢትዮጵያ ዘልቀው ገቡ። ያደቆሰ ሰይጣንዕ እንደሚባለው ገንዘብ እያሸተቱ ይበልጥ ወደ መሃል ተሳቡ። ኦርቶዶክስንና አማራን አከርካሪውን ሰብረነዋልዕ አሉ አቦይ ስብሃት የዋልድባንም የመሬት ሸንኮራአገዳ ሊተክሉበት እያሰቡ። ዋልድባ አለቀሰች፣ አነባች ሁለቱን እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ዘረጋች። አቶ መለስና ባለቤታቸው፣ አቶ መለስና ተባባሪዎቻቸው፣ አቶ መለስና ዘመዶቻቸው በኢንቬስትሜንት ስም፣ በልማት ዘፈን ለሟን ኢትዮጵያ ከላይ አርማጭሆ እስከታች ሞያሌ መጠመጧት። ልጆቻቸውን ገንዘብ እየሰጡ በውጭ ያዝናኗቸው ጀመር። የኢትዮጵያ ወጣቶችም ሃገራቸውን እየለቀቁ ሲሰደዱ ልጃቸው መንገድ ዳር እየተጸዳዳች ፎቶ ትነሳ ጀመር። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ መለስና ጳጳሱ ድንገት ሞቱ። የባለቤታቸው፣ ተባባሪዎቻቸውና ኢንቨስተሮቻቸው ገንዘብ የማሰባሰብ ዘዴና ትልም በአጭረ ተቀጨ። ሌላ ስትራቴጂ የሚያመነጭ ጠፋ። የተማሩ ናቸው ተብለው የተቀመጡትም አቶ ኃይለማርያም ትምህርቱ ተሰወረባቸው። በድንገት ኦሮምያ ላይ አመጽ ፈነዳ። የመለስ ፋውንዴሽን፣ የሼኩ ንብረቶች፣ የውጭ ኢንቬስተሮች ተቋም፣ የልማታዊው ዲያስፖራው ሱቆች በእሳት ጋዩ፣ በድንጋይ ተወገሩ። የአቶ መለስ የብዝበዛ ፍልስፍና በአጭር ሊቀጭ ሆነ። የኦሮምያ ወጣቶች ሆ ብለው ተነሱ። ወተቷን ጠጥተው፣ እሸቷን በልተው ያደጉትን ልማታዊ ኦሮሞዎችንም አስጠነቀቁ። እነዚህ ሁል ያመጹት ወጣቶች የልማቱን ዘፈንዕ እየሰሙ ያደጉ ወጣቶች ናቸው።
ለም በመሆንዋ ከትግራይ ጋር ሳትወድ የተደባለቀችው መሬት ድምጿን ከፍ አድርጋ ጮኸች። ጊዜ ጥሏት ማንነቷን የተነጠቀችው ያች የቅዱሳን መሬት አመጸች። ከወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ የአማራውን ሕዝብ እያፈናቀሉ ከትግራይ ሰዎች እያሰፈሩበት በውሳኔ ሕዝብ (ረፈርንዱም) ስልት አካባቢን ከትግራይ ጋር ለመደባለቅ የወጠኑት ስልትም ተቀባይነት የለውም። ይህ ቢደረግ ታሪክ ትፋረዳለች፣ ዋልድባ ታለቅሳለች፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች። እርሱ አምላክ ከላይ ከከፍታው መብረቅ ያወርዳል። ያች መውጫ፣ መላወሻ፣ መፈርጠጭያ፣ መጋለብያ ተብላ በግፍ የተወሰደች የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት ለም መሬት፣ ለቅዱሳኑ ኪዳናት ባለአደራ የሆነችው ዋልድባም ጭምር መወለጃ መሆኗ ቀርቷል። እናንተ እብሪተኞች ያጽመ ርስት ይዞታዎቼን ልቀቁልኝ አለች።
ከላይ እንዳነሳሁት ጃንሆይም፣ ኮሎኔል መንግሥቱም አቶ መለስም ለልጆቻቸው ያሰቡ አይመስለኝም። የጃንሆይ ልጆች፣ የልጅ ልጆች ስደተኞች ሆኑ። የኮሎኔል መንግስቱም ልጆች እሳቸውም ስደተኞች ሆኑ። የአቶ መልሰ ልጆች ግን ስደተኛ እንኳን ሆነው መኖር የሚችሉ አይመስለኝም። አባታቸው ሥጋዊ ኑሯቸው የሲዖል ኑሮ እንደሆነባቸው አሸለቡ። ልጆቻቸውም ገንዘብ ታቅፈው ወደ ውጭ ሊኖሩ የሚችሉበት የዓለም ክፍል የለም። የአለም አቀፍ ህግ ተሻሽሏል። ባለቤታቸው፣ ሌሎቹም የራዕዩ ወራሾች በሁመራ አግርገው ወደ ሱዳን እንዳይፈረጥጡ ወደ ማህል ተስበው እግሮቻቸው በዝርፍያ ከተሠሩት ሕንፃዎች መሠረት ጋር አብሮ ወደ መሬት ተቀበረ። እጆቻቸው ከንግድ ቤቶቻቸው ግድግዳና ከኤፈርቱ የሙስና ኃብት ጋር ተጣበቁ። እንዴት ይውጡ፣ ወዴት ይሰደዱ። ቢሰደዱም ያሰደዷቸው ወጣቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ይጋፈጧቸዋል። አሁንም መከራ እያዩ ነው።
ከእሾህ የተጠጉት ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ዋልድባ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ አለቀሱ። ኦሮምያም አነባች፣ ተጋጠች፣ ከብቶቿ ታለቡ፣ ወርቋ ተዘረፈ። መላ ኢትዮጵያ ቆሰለች። ለአቶ መለስና ተባባሪዎቻቸው ሥልጣኑን ለሕዝቡ በሠላም እንዲያስረክቡ አሁንም ዕድሉን አልተነፈጉም። ይህ ካልሆነ ውሎ አድሮ ምን እንደሚፈጠር ሳይገነዘቡት አይቀሩም። የዝርፍያ፣ የቀማኝነትና የቁማር ፖለቲካ አሜሪካ የቱንም ያህል ቢረዳው መጨረሻው አያምርም።
እባክህ እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ከስቃይ አውጣት። መች ይሆን ሕዝብህ እፎይ የሚለው፧

Wednesday, August 17, 2016

ወያኔዎች ሆይ

ወያኔዎች ሆይ ልብ ልትገዙ ይገባል፡፡ የህዝብን ቁጣ ጥቂቶች የፈጠሩት ሁከት ነው እያሉ በሕዝብ ላይ መሳለቃችሁን አቁሙና ከማናቸውም የኃይል እርምጃ በመታቀብ ሕዝብ የሚላችሁን ብታደምጡ ይበጃል፡፡ ህዝቡ በቃችሁኝ ብሉአል ያላቹ ጊዜ በጣም አጭር ነዉ፡፡ ከረፈደ ይሄንን እድል አታገኙም፡፡

Monday, August 15, 2016

ወያኔ 
እነሆ እኛ ኢትዮጵያዉያን ህብረት፣ መደጋገፍ፣ ስምምነትና አርቆ አሳቢነት 
የሚጠይቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ያለፉት ዓመታት የወያኔውን ጥቁር ሥርዓት ምንነት አሳይቶናል። ይህንን ብቻ አይደለም፤ በአምባገነን ሥርዓትና ለቅኝ ገዥዎች በባንዳነት በሚያድር ሥርዓት መካከል ያለውን ልዩነትም በሚገባ አሳውቆናል። የንጉሡ ዘመን ኋላ ቀር ነበር። የደርግ ዘመን አምባገነን ነበር። በሁለቱም ሥርዓት ወቅት ግን ሃገር ነበረች። ኢትዮጵያ እስከ ባህረ በሯ ሉዓላዊ እስከ ሕዝቦቿ ክቡር ነበረች። ዛሬ ለየት ያለ ነው። ወያኔ ዘረኛ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሙስናዊ አምባገነን ሥራዓት ቋሚ ተጠሪ ስብስብ ተቋም ብቻ አይደለም። ወያኔ "የአናቁረህ ግዛ" ግፍ አራማጅ ብቸኛ የቀማኞች ድርጅት ብቻ አይደለም። ወያኔ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለውጭ ባለሃብቶች የሸበሸበ የኃጢአተኞችና "የአስረሽ ምቺ" ዳንኪረኞች፣ መዝባሪዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሁሉም የኃጢዓት ሥርዓቶች ድምር ነው። ወያኔ ድንገት ከተሰባሰበበት ደደቢት ሸለቆ ተንከባሉ ሠይጣን ዋሻ ውስጥ ለአመታት ከርሞ ዲያቢሎስ ሳያኝክ የተፋው የርኩስ ሥርዓት ቁንጮ ነው። እድሏ ሆኖ ቅድስት ኢትዮጵያ የዚህ ሥርዓት ተሸካሚ ሆናለች። እንዲያ እንዳልተከበረች፣ እንዲያ እንዳልተፈራች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ቅርጫ ቀረበች። ሥርዓቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በቁሟ የገነዘ፣ ሕዝቧን ያስጨነቀ መሪር ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከዚህ ሥርዓት የሚገላግላት ቆራጥነትና በህብረት መነሳት ብቻ ነው። ህዝብን በመርዘኛ ራዕይ ሰልቦ፣ ወጣቱን በሥራ አጥነት አጠውልጎ ለስደትና ሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ፣ ነዋሪውን በልማት ስምና በከተማ ማስፋፋት እያፈናቀለ ሕዝብን በቅኝ ገዥዎች ቋንቋና በምጣኔ ኃብት እድገት እያደናገረ የሃገሪቱን ሃብት መዝብሮ ወደ ውጭ በማሸሽና በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በጥቂቶች ስም ሃብት እያከማቸ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊገዛ የሚቃጣ ዘመነኛ የግፍ ሥርዓት አራማጅ ወያኔ ብቻ ነው።

Thursday, August 11, 2016

ነሃሴ ፭ ( አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ገዢው ፓርቲ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማስቆም የጸጥታ ሃይሉን በብዛት በማሰማራት ውጥረቱን አባብሶታል። የፌታችን ቅዳሜ እና እሁድ ተቃውሞ ይካሄድባቸዋል በሚባሉት በርካታ የ አማራ ክልል ወረዳዎች ብዛት ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፌደራል ፖሊሶች እየገቡ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ሊያስተባብሩ ይችላሉ የተባሉት ደግሞ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተጋዙ ነው። በተለይ በደብረማርቆስ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መደርሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳርም እንዲሁ የፊታችን እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ በድጋሜ ሊጀመር ይችላል ተብሎ እየተነገረ መሆኑን ተከትሎ ወታደሮች ጥበቃቸውን አጠናክረዋል። በዛሬው እለት አንዳንድ ንግድ ድርጅቶችና የትራንሰፖርት መኪኖች እንቅስቃሴ ቢጀምሩም አብዛኛው ወጣት ከወታደሮች እይታ ውስጥ ላለመግባት ጊዜውን በቤቱ ማሳለፍን መርጧል። በአንድ ላይ ሰብሰብ ብለው መንገድ ላይ የተገኙ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። የክልሉ ጤና ቢሮ ሰራተኞች የታሰሩት ካልተፈቱ ስራ አንጀምርም ማለታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ክልሉን በብቃት አልመሩም በሚል ወሳኝ የሚባሉትን ጉዳዮች የፌደራል ባለስልጣናት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፣ አቶ ገዱን በሂደት ከስራ እንቅስቃሴ ውጭ ለማድረግ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። አብዛኛውን የክልሉን እንቅስቃሴ በፌደራል ደረጃ በሚሰሩ የህወሃት ታማኞች ለመምራት የሚያስችል አሰራሮች መተግበር ጀምረዋል። በወልድያ ዛሬ የባጃጅ አሽከርካሪዎችንና ባለንብረቶችን ለመሰብሰብ የተደረገው ሙከራ እንዲበተን ተደርጓል። በሰሜን ወሎ ዋና ከተማ ወልድያ ፣ በባህል አዳራሽ የተጀመረው ስብሰባ በክልሉ የትራንስፖርት ሃላፊ የተመራ ሲሆን ፣ ከ200 ያላነሱ ሹፌሮችና ባለሃብቶች ብቻ በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል። ስብሰባው በጭቅጭቅ መሞላቱን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች አዳራሹን ለቀው የወጡ ሲሆን ፣ እንደገና በልመና 30 የሚሆኑ ሰዎች ስብሰባውን ተካፍለዋል። በመጨረሻም የጸጥታ ሃላፊው አቶ ሙልቀን ማርዬ በእሁድ ስልፍ ላይ እንዳትወጡ በማለት መስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። ተመሳሳይ ስብሰባዎች በከተማዋ የተለያዩ ቀበሌዎች ተካሂዷል። በላሊበላ ከተማም እንዲሁ ካድሬዎች በየፅ/ቤቱ፣በየቀበሌውና በየትምህርት ቤቱ ህዝቡን በመሰብሰብ በእሁዱ ሰላማዊ ሰለፍ ብትሳተፉ ወዮላችሁ እያሉ በማስጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ በርካታ የገጠር ሚኒሻዎች እና የአካባቢ ፖሊሶች ከተማይቱን የወረሩ ሲሆን አቶ ግርማ የተባለ በልስ ስፌት የሚተዳደር ሰው ትቀሰቅሳለህ በሚል ተይዞ ታስሯል። በደብረብርሃን ከተማም ተመሳሳይ ስብሰባ ተካሂዶ ተበትኗል። በከተማዋ የጸጥታ ሃይሎች እየዞሩ ህዝቡን በማስፈራት ላይ ናቸው። በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ ለማዘጋጀት ሲሞክሩ በፖሊሶች የተዋከቡ ሲሆን፣ የተቃውሞውን ሰልፍ በሳምንቱ መጨረሻ ለማካሄድ እንዳቀዱ ተናግረዋል። ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ የታፈሱ 1 ሺ የሚሆኑ ወጣቶች በአዋሽ አርባ መታሰራቸውን ለማውቅ ተችሎአል። የደህንነት ሃይሎች የታሰሩትን ለመጠየቅ የሚሄዱ ሰዎችን ገንዘብ ስጡንና እንፈታቸዋለን ማለት መጀመራቸውን ለጥየቃ የሄዱ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ድርጊቱ ያስገረማቸው የእስረኞች ቤተሰቦች ፣ “ደህንነቶች የሚጠይቁት ገንዘብ ማንኛውም ደሃ ህዝብ ሊከፍለው የማይችለው ነው” ካሉ በሁዋላ ፣ ደህንነቶች ሁኔታው አስግቷቸው ገንዘብ መሰብሰብ የጀመሩ ይመስለናል ሲሉ ትዝብታቸውን አክለዋል።

Monday, August 8, 2016

ሰበር ዜና በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች ሰሮቃን ለቀው በመውጣት በየጫካው መሽገዋል። ሴቶችና ህጻናት ሰሮቃ ከተማ ለቀው ወጥተዋል። ትናንት በሚሊሺያዎችና በወታደሮች መካከል የነበረው ፍጥጫ በሽማግሌዎች እንዲበርድ ቢደረገም፣ ገዢው ፓርቲ ራሱ ያስታጠቃቸው አርሶአደር ታጣቂዎች ከእንግዲህ በህወሃት አንገዛም በማለት ጫካ በመግባታቸው በማንኛውም ጊዜ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል። 3 ታንኮች እና በ6 ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮችም ሰሮቃን ለቀው ወደ ማክሰኚት አቅጣጫ በማምራት ላይ ይገኛሉ። ከዳንሻ የመጣ ጦር ሰሮቃ የነበረውን ጦር ተክቶ ከተማዋን ተቆጣጥሯል። ከጎንደርና ሁመራ የተነሳ ጦር ወደ አርማጭሆ እየሄደ ነው። በትክል ድንጋይ አካባቢ 7 ወታደሮች ዛሬ ጠዋት ተገድለዋል። በሰሜን ጎንደር ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

Tuesday, August 2, 2016

ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና

ሐምሌ ፳፮ ( ሀያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተጻፈውና በቅጅ ለኢሳት የተላከው ደብዳቤ ፣ “ በእብሪተኛ ገዢዎች እየተፈጸመ ያለው ግፍ በሃገርና በህዝብ ላይ የደገሰውን የሞት ድግስ ከማድረሱ በፊት የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጡ እንጠይቃለን ብሎአል። ደብዳቤው በጎንደር ባለፈው እሁድ ተካሂዶ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች በአፋጣኝ መልስ እንዲያገኙ ይጠይቃል። በግፍ ታፍነው የተወሰዱት የወልቃይት የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ህዝብ ወኪሎች የሆኑት አቶ አታላይ ዛፌ፣ አቶ ጌታቸው አደመ፣ አቶ አለነ ሻማ፣ አቶ መብራህቱ ጌታሁንና ሌሎችም የተጣለባቸውን የህዝብ አደራ አቤቱታ በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመንግስት ከማቅረባቸው ውች ሌላ ምንም ከህዝብ እይታ የተሰወረ የሰሩት ወንጀል ሳይኖር ሆን ተብሎ የጥያቄውን መስመር ለማስቀየር የሃሰት ውንጀላ በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ይጠይቃል። የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ በአስቸኳይ እንዲፈታ፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ በሰሜን ጎንደር በአንድነት የሚኖሩ ቤተሰቦችን አማራ ቅማንት የሚል ከፋፋይ ሴራ በመፍጠር በተለያዩ ጊዜ በሽፋን ጭልጋ ትክል ድንጋይ ሮቢት ማውራና ሌሎች ቦታዎች ለሞቱትና ያለ አገባብ ለታሰሩት ወንድሞችንና እህቶች የሃሳቡ ጠንሳሾች፣ አስፈጻሚና ፈጻሚ ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ሃምሌ 5 2008 ዓም በጎንደር ደህንነትና ጸረ ሽብር ግብረ ሃይል በመግለጫ ያስተላለፉት መልእክት ፍጹም የተሳሳተና ውሸት በመሆኑ ማስተባበያ በመስጠት የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁም ደብዳቤው ይጠይቃል። “ከዚህ በሁዋላ በኦሮምያ ጋምቤላ ቤንሻንጉልና ሌሎችም የኢትዮጵያ መሬቶች በኢትዮጵያውያን የሚቀርቡ ሰላማዊ ጥያቄዎችን በተጠየቁበት በሰላማዊ መልስ ከመስጠት ውጭ ሻዕቢያ ቅጠረኛ ሽብርተኛ የሚል የሃሰት ስም በመለጠፍ እራሱ በሚከፍላቸው ሰራዊቶች፣ በእራሱ ገንዘብ በተገዛ መሳሪያ በማፈን በመግደል ሰላማዊ ጥያቄዎችን ለመድፈቅ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንዲቆምና እንዳይሞከር በጥብቅ እናሳስባላን” የሚለው ደብዳቤው ፣ ለእነዚህ ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠም ጠይቋል። የሳንጃ ነዋሪዎች እና ታጣቂዎች ጎንደር ከተማ ገብተው የተቃውሞ ድምጻቸውን ካሰሙ በሁዋላ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ምሽት ላይ ህዝቡ በጀግና አቀባባል ተቀብሎአቸዋል። በጎንደር እና በእስቴ ወረዳ በመካነየሱስ ከተማ የተካሄዱትን ተቃውሞዎች ተከትሎ ተመሳሳይ ተቃውሞች በመጪው እሁድ በባህርዳር ፣ በደብረታቦር እንዲሁም በመካነሰላም በድጋሜ ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ነው። ሰልፎቹ በጎንደር የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመደገፍ የተጠራ ነው።

Friday, July 8, 2016

PM David Cameron was asked by Chris Law MP if in his final days of premiership if he will be asking for Andargachew Tsege's release from Ethiopian prison and return to his family during the final days የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ በቅርብ እየተከታተሉት መሆኑን ገለጹ።

ኤስፍና ESFNA እና AESA One ታሪካዊ ግብግብ

ኤስፍና ESFNA እና AESA One ታሪካዊ ግብግብ
ከ ሚኪያስ ግዛው
በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ባንዲራዎች ይውለበለባሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ኳሶች ይነጥራሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ድምጻውያን ይዘፍናሉ። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ማልያ የለበሱ ሰዎች ይታያሉ። ሁለቱም ሜዳዎች ግን ልዩነቶች አሏቸው። አንደኛውን ሜዳ ደማቅ ቀለማማ የብርሃን ፍንጣቂ ከቦታል። አንደኛው ሜዳ ላይ ደግሞ ጨለማ ሠፍኗል። በሁለቱም ሜዳ ላይ ተመልካቾች አሉ። ባንደኛው ሜዳ ላይ ጢቅ ብለው የሞላው ሕዝብ ብርሃኑን መልሶ ያንጸባርቃል። በሌላኛው ሜዳ ላይ ደግሞ የተቸረከሙት ጥቂት ሰዎች በዘረኝነቱን ጨለማ ተውጠዋል። በሁለቱም ሜዳዎች ላይ ሰዎች ይታያሉ። ምነው ታድያ አንደኛው ሜዳ ላይ ያሉት ሰዎች እንደ ኃጢዓቱ ምርከኞች ኩርምት አሉ?
እነዚህን ወገኖች ነጻ ማውጣት አለብን። እነዚህን ወገኖች ከጨለማው አውጥተን ወደ ብርሃኑ ለማምጣት ማስተማር፣ መምከር አለብን። ታድያ እንዴት ይሆናል! እኔም ጭንቅ አለኝ!
አዎ - ይህን ሳሰላስል ድንገት ቶሮንቶ (Toronto) ላይ እምዬ ሚኒልክ ምስላቸው ብቅ አለ። በግርማ ሞገሥ የተከበቡት፣ የዋህና ደጉ ንጉሣችን እምዬ ሚኒልክ በፈረሳቸው ዳኛው ላይ ተቀምጠው ድንገት ብቅ ሲሉ ታየኝ። በስታድዮሙ ውስጥ ሌላ ብርሃን ተንጸባረቀ። በምድረ ዓለም ገድላቸው ተነግሮ ያላበቃው የነጻነቱ አባት እምዬ ሚኒልክ "ይህችን ባንዲራ ጠብቋት፣ ብዙዎች ለዚህች ባንዲራ ሲሉ ተሰውተዋል" አሉ በዚያ የዋህ ድምጻቸው። ይህ ድምጽ የስታድዮሙን ግድግዳና የአካባቢውን ሕንጻ በርቅሶ፣ በአየር እየተንሳፈፈ አኤስዋኖች (AESA One)ኩርምት ብለው የቀመጡበት አሌክሳንዴርያ ቨርጂንያ (Alexandria, Virginia)ጨለማው ዋሻ ደረሰ። ድምጹ እንደ ሳይክሎኑ( cyclone) ነፋስ ገረፋቸው፣ ገፈታተራቸው። አዎ እነዚህ በነዋይ ምርኮ ታግደው፣ ቀለብ ተሰፍሮላቸው በጨለማው ውስጥ ዘረኝነቱን ለማድመቅ የተቀመጡ የዋሆች በቶሎ ነጻ ይወጣሉ። የእምዬ ሚኒልክ ድምጽ እንኳንስ ለወገን ለባዕድም ማዕዛ አለው። ነዋይና ስጋቸው በእሳት እንደተበየደ ብረቶች ከተዋሃደው ጥቂቶቹ ቱባ የዘረኝነቱ አዳማቂዎች በቀር ሌሎቹ ቶሎ ነጻ ይወጣሉ።
አሁንም ጭንቅ ይለኛል። በደጉ ዘመን ተንቀባረው ይኖሩ የነበሩት፣ በዘመኑ አጠራር "የዲታ ልጆች" የሚባሉት ግለሰቦች ለምን ለጨለማው ሥራ ተባባሪዎች እንደሆኑ ማወቅ አልቻልኩም። ወያኔ በአብዛናው በሥሩ ያሰለፋቸው ምርከኖች ትላንት "በአማራው ስትጨኮን የነበርህ ነህ" የተባሉ ጥቂት ተላላ ድንባዣሞች ሆኖ ሳለ - ያኔ ተንቀባረው ያደጉ ግለሰቦች ለምን ምርከኞች እንደሆኑ ማሰቡ ያዳግታል። ገንዘቡ አታሏቸው ነው እንዳይባል እኛ የሳር ፍራሽ ሲበዛብን እነሱ ተዝቆ የማያልቅ ገንዘብ ተንተርሰው ያደጉ ቅምጥሉች ናቸው። ሥልጣን ፈልገው ነው እንዳይባል ደግሞ ሥልጣን የያዙ አልያም የባለሥልጣኖች መጋቢ አሽከር ተከታይ ሆኑ እንጂ የነእገሌን ያህል እንኳን ክብር አልተሰጣቸውም። ምንድነው እነዚህን ግለሰቦች ለዘረኝነቱ ጨለማ ተገዥ ያደረጋቸው። ንዋይ፤ ሥልጣን፤ የተወረሰባቸውን ቦታና ቤት ለማስመለስ ወይንስ የዓዕምሮ መላሸቅ? ያ ሁሉ ትምህርት ምነው ላሸቀ እነዚህን ወገኖችም እንዴት አድርገን ነጻ እንደምናወጣ አላውቅም። አንድም ሰው ቢሆን በዘረኝነቱ ጨለማ በምርኮ እንዲሰቃይ አንፈልግም። ለነዚህም ወገኖች መልካም ልብ እንስጣቸው። በጓደኞቻቸው እናስመክራቸው።
ኤስዋን AESA One ሰዎች ከዚህ ውርደት ልትማሩ ይገባል። ሕዝብ በማይደግፈው ነገር ውስጥ ከመሳተፍ ልትቆጠቡ ይገባል። ዲሞክራሲ ማለት የአብዛኛ ሕዝብ የበላይነት ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሳይገባችሁ አይቀርም። ቁጥሩን መገመት ትችላላችሁ። ዘረኝነት አናሳ ነው። ዘረኝነት ኢትዮጵያዊነት አይደለም። ኃያላኑ ሃገሮች ለጊዜዊው ጥቅማቸው ሲሉ ዘረኝነቱን ቢያሞካሹትም እንኳን እናንተ የእምዬ ሚኒልክ ልጆች ልትታለሉ አይገባም። ነገ እንትፍ ብለው ከሚጥሉት ዘረኝነት ጋር ብትወግኑ ነገ የምታዝኑት እናንተው ናችሁ። ለልጅ ልጆቻችሁ ነጻነት ከወዲሁ አስቡበት። የባንዳ ልጅ፤ የምንትስ ልጅ ለምንስ ይባሉ።
ኤስፍና ESFNA እና AESA One የዲያስፖራው ኢትዮጵያው ሌላኛው የግብግብ አውድማዎች ናቸው። ግብግቡ ሰው ከሰው ጋር አይደለም። ግብግቡ ኢትዮጵያዊነት ከዘረኝነት ጋር ነው። ከእግዚአብሄር መንፈስ ጋር አታመሳስሉት እንጂ ሁለቱም መንፈሶች ናቸው። አንዱ ኢትዮጵያዊ መንፈስ፣ አንዱ የዘረኝነቱ የጣር መንፈስ። የኋላ ኋላ የዘረንነቱ የጣር መንፈስ በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መሸነፉ አይቀርም። ይህ እውን እስኪሆን ለጥቂት ጊዜ ግብግቡ ይቀጥላል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፣ ባዲራችን ለዘላለም ትውለብለብ።
ክብር ለአጼ ቴዎድሮስ፣ ክብር ለአጼ ዮሃንስ፣ ክብር ለእምዬ ሚኒልክ

Saturday, April 2, 2016

በ ወያኔ ዘመን................

በ ወያኔ ዘመን................
ባጠቅላይ ሃቀኝነት፣ ደግነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሙስናንና ጉቦን መጸየፍ – እነዚህ የሕዝቡ የመልካም ባህርይ መገለጫ የሆኑት እሴቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ጉሮኖ ተወርውረዋል። እነዚህን እሴቶች ዳግም ሊያንጸባርቅ የሞከረ ሁሉ መሳለቅያ ይሆናል። ኬንያና ናይጄርያ በሙስናና ጉቦ ጫፍ ላይ የደረሱ ሃገሮች እየተባሉ ሲነገር ቆይቷል። ኢትዮጵያ ደግሞ በጥቂት ዓመታት ክብረወሰኑን አልፋ የሙስናና ጉቦ ፍልስፍና የተሃድሶ ምድር እንደሆነች ይታወቃል። ይህን የመሳሰሉት ግፎች ናቸው ዛሬ ሕዝቡን ለአመጽ ያነሳሱት። የፍጥ መዛባት፣ እስር፣ ግድያና የምጣኔ ኃብቱ ይዞታ ልዩነት ካልተገደቡ በቀር ሕዝቡን ለመብቱ ከመታገል የሚያቆመው አንዳች ኃይል የለም። የፌደራል መንግሥቱ እጆች አመድ አፋሽዕ ወይም የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ እንዳሉትየኢትዮጵያ ሕዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለትሆኖ አይደለም ይህ ሁሉ አመጽ የበረከተው። ሙስናው፣ የአስተዳደር በደሉ ፡ ኑሮውን አናግተውበት ፡ በድህነትና ሰቆቃ ጅራፍ መገረፉ፣ በአምባገነኖች ውሳኔ ብቻ መነዳቱ አልበቃ ብሎ ቀማኞች መሬቱንና የመሬቱን የተፈጥሮ ገጸበረከት በጠመንጃ አስገድደው በጠራራ ፀሃይ ስለሚዘርፉት እንጂ።እግዚአብሄር ቸር ዘመን ያምጣልን፣ አሜን

Saturday, March 26, 2016

ፍትህ በ ወያኔ ዘመን
ፍትህ (justice)፣ በኢትዮጵያ ፍትህ ደብዝዛለች። ደብዳቢውና ተደብዳቢው ፖሊስ ጣብያ ቢሄዱ ተደብዳቢው ይታሠራል። ዘራፊና ተዘራፊ ሸንጎ ፊት ቢቀርቡ ተዘራፊው ተሸማቆ ከእልፍኙ በአፋጣኝ እንዲወጣ ይደረጋል። ዳኛና ጠበቃ የጥቅም ትሥሥር አድርገዋል። ፍርደ ገምድል ዳኛው የባለጉዳዩን ሳይሆን የጠበቃውን እጆች ያያል። ደህና ጉቦ ሰጪ ጠበቃ ዝናን ያተርፋል፣ በርካታ ደንበኞች ያፈራል። ለፍትህ የቆሙ ጠበቆች ደግሞ ሥራ ፈተዋል። "ፍትህ ይስፈን" እያሉ ሲጮኹ ሙሰኛው ዳኛና መሠሪው ጠበቃ ይሳለቁባቸዋል። ፍትህ በኢትዮጵያ እጅግ ተረግጣለች። ታድያ በአቋራጭ ለመክበር ኢፍትሃዊ ነገሮችን ሳይፈሩ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። በኢፍትሃዊ አሠራሮች ልምድን የቀሰሙት ደላሎችና አቀባባዮች የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። እነርሱ ለዳኞችና ጠበቆች ሐሰትን አደልቦ እንደምን ማሸነፍ እንደሚቻል ህግን ሳይፈሩ፣ ሰውን ሳያፍሩ ምክር ያካፍሏሉ። ክፉዎች የምክር አገልግሎት በሚሰጡባቸው ቢሯቸው ውስጥ የፍትሃብሄር ህግና መጽሃፍ ቅዱስ ሁለቱም ጠረቤዛው ላይ ተቀምጠዋል። አይ ዘመን!

Friday, March 25, 2016

ሰበር ዜና
ዶክተር መረራ ጉዲና ከሀገር እንዳይወጡ ተደረገ። ወደ አሜሪካ ለመምጣት ትላንት ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሄዱም መውጣት አልቻሉም። ዛሬ ወደ ኢሚግሬሽን ሄደው ሃላፊው ስብሰባ ገብተዋል ተብለው ተመልሰዋል። 
''ፓስፖርትዎን መሳሪያው ማንበብ አልቻለም። ምናልባት ሽቶ ነክቶት፡ ወይም ዘይት ተደፍቶበት ሊሆን ይችላል።'' 
ቦሌ የኢሚግሬሽን(ደህንነት) አንድ ሰራተኛ የተናገረው

Monday, March 21, 2016

የወልቃይት ጠገዴ ዳንሻህ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ጦር ጥቃት እየተሰነዘረበት የዘር ማጥራት እየተካሄደበት ነው

የወልቃይት ጠገዴ ዳንሻህ ህዝብ በአሁኑ ሰዓት በወያኔ ጦር ጥቃት እየተሰነዘረበት የዘር ማጥራት እየተካሄደበት ነው
ሰበር ዜና
በዳንሻ ግጭት ተፈጥሯል። በትግራይ ልዩ ፖሊስና በወልቃይቶች መሀል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። መንገዶች ተዘግተዋል። በአቅራቢያ ባሉ መንደሮች የሚገኙ የወልቃይት ነዋሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው።

Saturday, March 19, 2016

ሕወሓት እና የመሬት ቅርምቱ

ሕወሓት እና የመሬት ቅርምቱ
መሬት (Land)፣ መሬት በሕዝባዊ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስትውል ልማት ባግባቡ ይፋጠናል። በሃገራችን የመሬት ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ አልፋና ኦሜጋ ነው። የተፈጥሮ ኃብት (Natural resources) ከጉልበትና ዓዕምሮ (labour and mental) ጋር ሲዋሃድ ምርትን (production) ያስገኛል። መሬት የተፈጥሮ ኃብት ዋነኛ መፍለቅያ ምንጭ ነች። ማንም ሠላምንና ጸጥታን፣ ልማትንና እድገትን የሚፈልግ ስብስብ የመሬትን ጉዳይ ፍትሃዊ (justify) ለማድረግ ሲል ጠቃሚ መሠረታዊ ህጎችን (system of rules)በቅጡ ይቀርጻል። ይህ ጉዳይ ፈጽሞ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ ጥቁር ገበያዎች (black markets) እንደ አሸን ይፈላሉ። ጥቁር ገበያ በሙስና (Corruption) የሚመራ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ፍዳና ዕዳ ነው። መሬት የመንግሥት ኃብት እንዲሆን ፈላስፎችና የምጣኔ ኃብታዊ ሊቆች እጅግ ሠፊ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሠጥተዋል። "መሬት ላራሹ" በኢትዮጵያ ተራማጆች ዙርያ ዘወትር ሲነሳ የቆየ ታሪካዊ መፈክር ነበር። የተጨቋኖችና አጋሮቻቸው እምቅ አስተሳሰብ የወለደው ይህ ታሪካዊ መፈክር ተንቆ ይባስኑ የኢቶዮጽያ መሬት የቀማኞችና ሙሰኞች መገልገያ ሆኗል። በኢቶዮጽያ መሬት አሞሌ ጨው ተሸክሞ ለመጣ ሁሉ በቀላሉ እንደምትቸረቸር ኮማሪት ተንቃለች። መሬት "በሶስተኛ ደላሎች" ስም እንደዋዛ የምትለወጥ ጉቦኛ ባለሥልጣናትና መዝባሪው ነጋዴ የሚሻሟት አሳዳሪ የራቃት ባለቤት አልባ ሆናለች። መሬት በኢቶዮጽያ ምን ያልሆነችው አለ? አሜሪካ የተፈጠረችው በቀይ ሕንዶች ደም ላይ ነው። አሜሪካ የተገነባችው በአፍሪካውያን ባርያዎች ግፍና ሰቆቃ ነው። ይህን ግፍ የዲሞክራሲ ቋሚ ምሰሶ ወይም ዓምድ አይደለም። ገዥው መንግሥት ሰዎችን በፌደራል ፖሊስ ጥይት ካስገደለ በኋላ "ለዲሞክራሲው ግንባታ ገና ነን፤ አሜሪካ እስከ ስድሳዎቹ መባቻ ድረስ ሰዎች ይገደሉ ነበር" ብሎ ያወራል። አገዛዙ ልማቱን እየዘረፈ፣ ሰዎችን እንደ ቀይ ሕንዶች ከቀዪአቸው እያፈናቀለ፣ ጥሬ ሃብቱን ለባዕድ እየቸረቸረና "መሬቴን አትንኩ" ያሉትን ነዋሪዎች እያሽመደመደ "ዲሞክራሲው ገና አልጎለበትም" ብሎ ያሾፋል። ይህን ትምህርት የቀሰሙት ከሱዛብን ራይስ ከሆነ ያሳዝናል። መልካሞቹን የዲሞክራሲ እሴቶችና የመልካም አስተዳደር መርህን ካደጉት ሃገሮች ተሞክሮ እየቀሰሙ ማዳበር ሲቻል መሬትን ለመቀራመት ብሎ ተወላጁን፣ አገር በቀሉን (indigenous) መግደል የዲሞክራሲ ባህሉም ወጉም አይደለም።

Thursday, March 17, 2016

ኦሮምያና “ልማታዊ ሙስናዎቿ”

ኦሮምያና “ልማታዊ ሙስናዎቿ”

ኦሮምያና "ልማታዊ ሙስናዎቿ"ከሚክያስ ግዛው (visit my blog  http://michyas.blogspot.no/ )
እኔ እንኳን ወያኔ በፈጠራቸው ዘረኛ የክልል ስሞች አካባቢዎችን መጥራት አልፈልግም ነበር። በዘር፣ ነገድ፣ ጎሳና ጎጥ የሚወሰን የማንነት ግንባታ (identity empowerment) አፍራሽ ይመስለኛል። ብቻ ይሁን እስቲ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ወዘተ ማለቱን ትቼ እንደው እንደዘበት "ኦሮምያልበል። ኦሮምያ ውስጥ ሙስና (corruption) እንደ አንድ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ዘርፍ (political economic sector) ተቆጥሮ ዋልጌዎች ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ እየተገበሩት ይገኛሉ። ይህ በደጋግና ጀግኖች ሕብረተሰብ ማህል የተደነቀረው የክፋት ገጽታ የመልካም አስተዳደር መርሆችን (good governance principles)፣ ባህላዊ ትሥሥሮችንና ሥነ-ምግባርን በማጨለሙ ሕዝቡን ለድህነት ዳርጓል። እስቲ እኔ ከታዘብኩት ውስጥ ጥቂቱን ላካፍላችሁ።
እውነት (Truth)፣ እውነት እምነት ነች። ሰዎች ስለአካባቢያቸውም ሆነ የዓለም ዙርያ እንቅስቃሴና ክንውኖች እውነቱን የማወቅ መብት አላቸው። ሰዎች እውነትን ሲረዱ ወደፊት ሊተገብሩ ስላቀዱት ዓላማ ግንዛቤ ይጨብጣሉ። በኦሮምያ የስልጣኑ ባሌቤት ኦሕዴድ ቀድሞውም ቢሆን በእብለት መሠረት ላይ የታነጸ በመሆኑ እውነት ማንጸባረቅ አይችልም። ድርጅቱ ባለቀልም የዋርካ ሥዕል ያለበት ባንዲራ እያውለበለበ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ከመንጎድ ውጭ ፋይዳው አይታይም። በአሮምያ ክንውኖች ሁሉ ህፀፅዊ(fallacious) ወደ መሆን ደርሰዋል። በየስብሰባው ውሃ የመይቋጥሩ አረፍተሃሳቦች (fallacious arguments) ይወረወራሉ። ባለስልጣናት ሕዝቡን በመናቅ አደናጋሪና አሳሳች (deceptive, misleading ; fallacious testimony) መረጃዎችን ይበትናሉ። የውስጡ መሠረታዊ ችግር ሳይመረመር ላይ ላዩን የተድበሰበሰ (disappointing; delusive) መፍትሄ መሰል ሃሳብ ቀርቦ ስብሰባው በተዳፈነ ሠላም (fallacious peace) ይጠናቀቃል። በእርግጥ ሁሉንም በአንድ ላይ መጨፍለቅ (generalization) ተገቢ አይደለም። የለበሱትን ሕዝባዊ አደራ በንፃት የሚጠብቁ ቢኖሩም የሙሰኞቹ ጥቁር ሥራ ግን በጎ ክንውኖችን ማጉደፉ አልቀረም። እውነት ኦሮምያ ምድር ሞታ ልትቀበር ትንሽ ቀርቷታል።
መሬት (Land)፣ መሬት በሕዝባዊ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስትውል ልማት ባግባቡ ይፋጠናል። በሃገራችን የመሬት ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ አልፋና ኦሜጋ ነው። የተፈጥሮ ኃብት (Natural resources) ከጉልበትና ዓዕምሮ (labour and mental) ጋር ሲዋሃድ ምርትን (production) ያስገኛል። መሬት የተፈጥሮ ኃብት ዋነኛ መፍለቅያ ምንጭ ነች። ማንም ሠላምንና ጸጥታን፣ ልማትንና እድገትን የሚፈልግ ስብስብ የመሬትን ጉዳይ ፍትሃዊ (justify) ለማድረግ ሲል ጠቃሚ መሠረታዊ ህጎችን (system of rules)በቅጡ ይቀርጻል። ይህ ጉዳይ ፈጽሞ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ ጥቁር ገበያዎች (black markets) እንደ አሸን ይፈላሉ። ጥቁር ገበያ በሙስና (Corruption) የሚመራ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ፍዳና ዕዳ ነው። መሬት የመንግሥት ኃብት እንዲሆን ፈላስፎችና የምጣኔ ኃብታዊ ሊቆች እጅግ ሠፊ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሠጥተዋል። "መሬት ላራሹበኢትዮጵያ ተራማጆች ዙርያ ዘወትር ሲነሳ የቆየ ታሪካዊ መፈክር ነበር። የተጨቋኖችና አጋሮቻቸው እምቅ አስተሳሰብ የወለደው ይህ ታሪካዊ መፈክር ተንቆ ይባስኑ የኦሮምያ መሬት የቀማኞችና ሙሰኞች መገልገያ ሆኗል። በኦሮምያ መሬት አሞሌ ጨው ተሸክሞ ለመጣ ሁሉ በቀላሉ እንደምትቸረቸር ኮማሪት ተንቃለች። መሬት "በሶስተኛ ደላሎችስም እንደዋዛ የምትለወጥ ጉቦኛ ባለሥልጣናትና መዝባሪው ነጋዴ የሚሻሟት አሳዳሪ የራቃት ባለቤት አልባ ሆናለች። መሬት በኦሮምያ ምን ያልሆነችው አለአሜሪካ የተፈጠረችው በቀይ ሕንዶች ደም ላይ ነው። አሜሪካ የተገነባችው በአፍሪካውያን ባርያዎች ግፍና ሰቆቃ ነው። ይህን ግፍ የዲሞክራሲ ቋሚ ምሰሶ ወይም ዓምድ አይደለም። ገዥው መንግሥት ሰዎችን በፌደራል ፖሊስ ጥይት ካስገደለ በኋላ "ለዲሞክራሲው ግንባታ ገና ነን፤ አሜሪካ እስከ ስድሳዎቹ መባቻ ድረስ ሰዎች ይገደሉ ነበርብሎ ያወራል። አገዛዙ ልማቱን እየዘረፈ፣ ሰዎችን እንደ ቀይ ሕንዶች ከቀዪአቸው እያፈናቀለ፣ ጥሬ ሃብቱን ለባዕድ እየቸረቸረና "መሬቴን አትንኩያሉትን ነዋሪዎች እያሽመደመደ "ዲሞክራሲው ገና አልጎለበትምብሎ ያሾፋል። ይህን ትምህርት የቀሰሙት ከሱዛብን ራይስ ከሆነ ያሳዝናል። መልካሞቹን የዲሞክራሲ እሴቶችና የመልካም አስተዳደር መርህን ካደጉት ሃገሮች ተሞክሮ እየቀሰሙ ማዳበር ሲቻል መሬትን ለመቀራመት ብሎ ተወላጁን፣ አገር በቀሉን (indigenous) መግደል የዲሞክራሲ ባህሉም ወጉም አይደለም።
ኢንቨስትሜንት፣ (investment) እኔ ራሴ investment, establishment, department, እንደው ምናለፋችሁ «ment» ያለበት እንግሊዘኛ ሲነገር እፈራ ነበር። ግናስ የሠፈራችን አንድ አጉራ ዘለል "ኢንቬስተርተብሎ ከውጭ ሲመጣ ቃሉን ተለማመድኩኝ። ምን ሊቨሰትር ነውብዬ ስጠብቅ አቀባባይ ረድፈኞችን በእንግሊዘኛ ደልሎ አስደልሎ መሬት ጨመደደ። መሬቱን ደግሞ ሸጦ ገንዘቡን መሬቱን ከሰጡት ከባለስልጣናት ጋር ተካፈላው ሲባል ሰማሁ። በኦሮምያ ብዙ ኢንቬስተሮች ይስተናገዳሉ። ከባለሱቁ አንስቶ እስከትላልቅ ሳሙና፣ ዘይትና ብስኩት ፋብሪካ ድረስ በሙስናው ማህደር ተመዝግቦ በጉቦኛው ማህተም ይለፍ የተመታለት የንግድ ተቋም ሁሉ "እንቬስትሜንትተብሎ ይወደሳል። ባንዳንድ አካባቢዎች የኢንቬስትሜንቱ ባለቤቶች (clandestine wealth) "የማይታዩት ባለስልጣኖችወይንም ተባባሪዎቻቸው ሲሆኑ የንግድ ፈቃዱ የተመዘገበው ባንድ ጭቁን የኢንቬስተሩ ሎሌ ነው። ይህ ዘመናዊ የሎሌነት ሥራ የተቀዳው በቅኝ ግዛት ሥር ከነበሩት የአፍሪካ ሃገሮች ነው።
ስብሰባ (session)፣ አስተማሪያችን "ስብሰባ ሎጂክ (logic) መጠቀምያ ጠቃሚ ጊዜ ነውሲሉ እሰማ ነበር። የፍርድ ሸንጎ ሠብሳቢ የነበረው አጎቴ ደግሞ "የስብሰባ አዳራሽ ዝም ብሎ ተሰባስቦ እንቅልፍና ራስ ምታት መሸመችያ ቦታ አይደለምይል ነበር። ሰው ከተሰበሰበ ንድፈ ሃሳብ አፍልቆ፣ እልባት ያለው ውሳኔ ሸክኖ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ አለበት (Theory + practice = Praxis)። ኦሮምያ ስብሰባ ታበዛለች። በሃያ አምስት ዓመታት ኦሮምያ ያስተናገደችው ስብሰባ በሜትር ሲለካ የዓለም ሊግና የተባበሩት የዓለም መንግሥታት ማህበር ካደረጉት ስብሰባ በሶስት እጥፍ ይበልጣል። ምን ንድፈ ሃሳብ ተወረወረምን ተወሰነምን ተፈየደምንም። በእርግጥ እድሜ ለሙስና ሠማይ ጠቅስ ሕንጻዎች ቆመዋል፣ ጥሬ ኃብቱንና ምርቱን ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ መንግሥት ዘመናዊ መንገድ አንጥፏል። የሕዝቡ ኑሮ ግን አልተሻሻለም። የሕዝቡ ባህልና እሴቶች ተደፍጥጠዋል። ተሰብሳቢዎች የሙስናንና ጉቦ መርሆችን በሰምና (wax) ወርቅ (gold) አሽሞንሙነው ይለያያሉ። ሰሙ "ሙስና ይጥፋሲሆን ወርቁ ደግሞ"ሙስና እጥፍ ይሁንነው። የመናገር ችሎታ፣ በእጅ የመሄድ አክሮባትና ድፍረት መለማመጃ የሆነው የኦሮምያው ሙስና ወለድ ስብሰባ ብዙ ገንዘቦች አባካኝ ጎጂ ባህል እየሆነ መጥቷል። ሃቀኛ ነጋዴዎች የመንግሥት ገቢ ለመክፈል ማለዳ ወደ አገር ውስጥ ገቢ ሲሄዱ "ፋይሉ አልተገኘምተብለው በኪራይ ሰብሳቢዎች ይባረራሉ። ችግሩን ለማን አቤት ይባላል። አለቆች ስብሰባ ላይ ናቸው። ሃቀኞች ዓመታዊውን ግብርና መንግሥት የደነገገውን ቫት ለመክፈል እንኳን ተቸግረዋል። የመንግሥትን ገቢ ለማስገባት ሙስና ለምን አስፈለገፋይሉ ጠፍቷል በመባሉ ምክንያት ግብር የተቆለለበት ሃቀኛ ነጋዴ ሲጉላላ ማየቱ አሳዛኝ ነው። ይህ ክፋት ኬንያና ናይጄርያም እንኳን አልተከሰተም። በኦሮምያ "ስብሰባሙስናን ማጠናከርያና ኪራይ ሰብሳቢዎችን ማሰልጠኛ ሠንበቴ ከሆነች ሰነበተች።
ፍትህ (justice)፣ በኦሮምያ ፍትህ ደብዝዛለች። ደብዳቢውና ተደብዳቢው ፖሊስ ጣብያ ቢሄዱ ተደብዳቢው ይታሠራል። ዘራፊና ተዘራፊ ሸንጎ ፊት ቢቀርቡ ተዘራፊው ተሸማቆ ከእልፍኙ በአፋጣኝ እንዲወጣ ይደረጋል። ዳኛና ጠበቃ የጥቅም ትሥሥር አድርገዋል። ፍርደ ገምድል ዳኛው የባለጉዳዩን ሳይሆን የጠበቃውን እጆች ያያል። ደህና ጉቦ ሰጪ ጠበቃ ዝናን ያተርፋል፣ በርካታ ደንበኞች ያፈራል። ለፍትህ የቆሙ ጠበቆች ደግሞ ሥራ ፈተዋል። "ፍትህ ይስፈንእያሉ ሲጮኹ ሙሰኛው ዳኛና መሠሪው ጠበቃ ይሳለቁባቸዋል። ፍትህ በኦሮምያ እጅግ ተረግጣለች። ታድያ በአቋራጭ ለመክበር ኢፍትሃዊ ነገሮችን ሳይፈሩ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። በኢፍትሃዊ አሠራሮች ልምድን የቀሰሙት ደላሎችና አቀባባዮች የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። እነርሱ ለዳኞችና ጠበቆች ሐሰትን አደልቦ እንደምን ማሸነፍ እንደሚቻል ህግን ሳይፈሩ፣ ሰውን ሳያፍሩ ምክር ያካፍሏሉ። ክፉዎች የምክር አገልግሎት በሚሰጡባቸው ቢሯቸው ውስጥ የፍትሃብሄር ህግና መጽሃፍ ቅዱስ ሁለቱም ጠረቤዛው ላይ ተቀምጠዋል። እግርግዳው ላይ ደግሞ "እግዚአብሄር ያያልየሚል በእንግሊዘኛና ኦሮምኛ የተጻፈ ጥቅስ ተሰቅሏል። አይ ዘመን!
አቀባባይ ረድፈኛ ሚና (liaison role between the corruptor and corruptors of public officials) አቀባባይ ረድፈኛ (እንደ ራሴ አተረጓጎምበሙያው ደላላ ያልሆነ ስልታዊ ደላላ ነው። ከደላሎች የሚለየው ነገር ቢኖር ባለስልጣኖችን በጥቅም አሳውሮ መቅረብ መቻሉ ነው (dangerous liaison)። የመናገርና የማሳመን ፣ የማዘበራረቅና የማዛባት ችሎታ የተላበሱት አቀባባይ ረድፈኞች አገዛዙ ባመቻቸው የሙስና መሠላሎች ወደ ላይ የወጡ የዘመኑ አራዶች ናቸው። እነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች ጉቦ ሰጪንና ጉበኛን፣ ሠነፍ ተማሪንና ቦዘኔ አስተማሪን፣ ባለስልጣንንና አራጣ አበዳሪውን፣ ፍርደገምድል ዳኛውንና ቆቁን ጠበቃ፣ ወዘተ፣ አገናኝ ናቸው። ካለነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች እገዛ ውጭ ባለስልጣን ሊመዘብርና ሙስና ሊቀበል ያዳግተዋል። መሥሪያ ቤቶችን ሁሉ የሙስናና ምዝበራ አርማ ተሸካሚ ያደረጉት እነዚህ በስልታዊ ብረዛ ሳይንስ የተካኑት አቀባባይ ረድፈኞች ዋዛ አይደሉም። ህግና ፍትህ ሚኒስቴር – ሙስናና አድልዎ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር – የምዝበራ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር – መሃይምነት ማስፋፍያ ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር የጨረታና መሬት ሽሚያ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር – የዋጋ ንረት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – ኢንቬስትሜንትና ሃዋላ ሚኒስቴር፣ የእርሻ ሚኒስቴር – እንጀራና በርበሬ ላኪ ሚኒስቴር፣ ወዘተ፣ እንዲሆን ሚናውን የተጫወቱት መለኞች ከአስመጭና ላኪዎቹ ወይም ሕንጻ አከራዮቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ላፍታም ቢሆን የማይርቁ የሙስናና ዝርፍያው ተቋም (kleptocracy) ባለውለታዎች ናቸው።
ቋንቋ (mother tongue)፣ በኦሮምያ ኦሮሚፋ ብቻ ነው የሥራ ቋንቋ። ልጆቿ ሌላ ክልል ሄደው መሥራት አይችሉም። እሷም ከትግራይ ወይም አማራ አልያም ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ ወይም ደቡብ ክልሎች የሚመጡትን ልጆች አታስተናግድም። አትድረሱብኝ – አልደርስባችሁም ብላለች። ኦሮምያ አማርኛ ቋንቋን እንደ መጨቀኞ መሣርያ ያህል በመጥላትዋ ሳብያ አፈሯን ፈጭተው፣ ውሃዋን ጠጥተው ያደጉትን ኦሮምኛ የማይችሉትን አንጡራ ልጆቿን እንኳን የጉዲፈቻ ዜግነት ከልክላቸዋለች። ኦሮምያ አማርኛ የነፍጠኞች ቋንቋ መሰላት እንጂ የጋራ መግቢያብያ ቋንቋ ልማትን እንደሚያፋጥን ቴክኖሎጂንም እንደሚያስፋፋ አላጤነችም። አማርኛ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ ለብዙ ዓመት ማገልገሉ ማንንም ባልጎዳ ነበር። የሆነስ ሆነና የኢትዮጵያ ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ መሆኑስ ይታወቃልኦሮምያ ይህን የልማት እንቅፋት ሽራ ይልቅስ ብዝህነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጠናከር ቀዳሚ ሚናዋ ሊሆን ይገባል።
ባጠቅላይ ሃቀኝነት፣ ደግነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሙስናንና ጉቦን መጸየፍ – እነዚህ የሕዝቡ የመልካም ባህርይ መገለጫ የሆኑት እሴቶች በኦሮምያ ውስጥ ወደ ጉሮኖ ተወርውረዋል። እነዚህን እሴቶች ዳግም ሊያንጸባርቅ የሞከረ ሁሉ መሳለቅያ ይሆናል። ኬንያና ናይጄርያ በሙስናና ጉቦ ጫፍ ላይ የደረሱ ሃገሮች እየተባሉ ሲነገር ቆይቷል። ኦሮምያ ደግሞ በጥቂት ዓመታት ክብረወሰኑን አልፋ የሙስናና ጉቦ ፍልስፍና የተሃድሶ ምድር እንዳትሆን ያሰጋል። ይህን የመሳሰሉት ግፎች ናቸው ዛሬ ሕዝቡን ለአመጽ ያነሳሱት። የፍትህ መዛባት፣ እስር፣ ግድያና የምጣኔ ኃብቱ ይዞታ ልዩነት ካልተገደቡ በቀር ሕዝቡን ለመብቱ ከመታገል የሚያቆመው አንዳች ኃይል የለም። የፌደራል መንግሥቱ እጆች "አመድ አፋሽወይም የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ እንዳሉት"የኢትዮጵያ ሕዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለት..."ሆኖ አይደለም ይህ ሁሉ አመጽ የበረከተው። ሙስናው፣ የአስተዳደር በደሉ ኑሮውን አናግተውበት በድህነትና ሰቆቃ ጅራፍ መገረፉ፣ በአምባገነኖች (tyranny, timocracy, oligarchy, plutocracy) ውሳኔ ብቻ መነዳቱ አልበቃ ብሎ ቀማኞች መሬቱንና የመሬቱን የተፈጥሮ ገጸበረከት በጠመንጃ አስገድደው (military command) በጠራራ ፀሃይ ስለሚዘርፉት እንጂ። የእርምቱ እርምጃ ከሰላው ጫፍ ይጀመር።
ጥቂቶቹ የትግራይ ሕወሓት መሪዎች ለም የሆኑትን የጎንደርና ወሎ አጎራባች መሬቶች በማናለብኝነት ተነሳስተው ወደ ትግራይ ክልል መደባለቃቸው ያስከተለውን አደጋና የህዝብ ቁጣ በሚቀጥለው ጊዜ እዘግባለሁ።
እግዚአብሄር ቸር ዘመን ያምጣልን፣ አሜን

Tuesday, March 15, 2016

ሲኖ ትራክ (Sino Truck) ሲኖ ጭራቅ፣ ቀይ ሽብር – ከ ሚኪያስ ግዛው 

ሲኖ ትራክ (Sino Truck) ሲኖ ጭራቅ፣ ቀይ ሽብር – ከ ሚኪያስ ግዛው 

እነዚያ ቀያዮቹን የቻይኖች መኪኖች ገና ከሩቅ ሲያዩ ጭራቅ የመጣባቸው ያህል ልጆች ይርበደበዳሉ። ገና የሲኖ ትራኩን ድምጽ ሲሰሙ የከለላና መከታ አያያዝ ስልትን ያልተማሩት እነዚያ ጨቅሎች የሚደበቁበትን ቦታ ለመምረጥ ሲባዝኑ ይታያሉ። "ሲኖ ትራክን ገና ከሩቁ ስታዩ..." እያሉ ወላጆቻቸው ጠዋት ጠዋት የሚነግሯቸው የጥንቃቄ አወሳሰድ ምክር ትምህርቱን አስረስቷቸዋል። ይህንኑ አደገኛ ቀይ መኪና ወላጆች በዘመናቸው ካዩት ዘግናኝ ድርጊት ጋር በማመሳሰል "ቀይ ሽብርብለውታል።
ሃገራችን ኢትዮጵያን አንገቷን ካስደፋት ትላልቆቹ ክፋቶች መካከል የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ስግብግብነትና የኅሊና መሸርሸሩ እጅግ አሳዛኞቹ ናቸው። ሃገር የቱንም ያህል ለማች፣ በሰማይ ጥቀስ ሕንጻዎች አሸበረቀችም ሆነ ዘመናዊ መንገዶች ተነጠፉላት ሥነ-ምግባርና ግብረገብነት ከተሸረሸሩ "ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭነው።
በንጉሡም ይሁን በደርግ ዘመን ሙስናና ጉቦ ቢኖርም እንዲህ እንዳሁን ሕዝቡን አላንገሸገሸም ነበር። አብዛኛው ሰው ፈሪሃ እግዚአብሄርነት በውስጡ ስላደረ በኅሊናው ይተዳደር ነበር። በደርግ ዘመን "መንጃ ፍቃድ በጉቦ አውጣ"፣ "መንጃ ፈቃድ ቤቱ ድረስ መጣለት"፣ ሲባል ሰው ወሬውን እንደ ጉድ ተገረሞ ያዳምጥ ነበር። ሰውንም ራስንም አደጋ ውስጥ የሚከት መርዝን በጉቦ መሸጥ የቴክንሽያኑን ኅሊና ቢስነት ደረጃ መገመቻ ነበር። መንጃ ፈቃድ በጉቦ መስጠት የሞት ፍርድ ያህል ነበር። ዛሬ እፍረት መሆኑ ቀርቶ ሁሉም ነገር ሙስናና ጉቦ ሆኗል። ሙስና ሞትንም ትሸጣለች። መሬት በጉቦ ይቸረቸራል። ባለገንዘብ መሬት ገዝቶ ጭሰኞች ይቀጥራል። የሠማይ ስባሪን ያህል ሹመት ተሸካሚ ግለሠብ ሕንጻ አከራይ ሁኗል። የሕዝብ አደራ የተሸከመው አገልጋይ አስመጭና ላኪ ነጋዴ ሆኗል። አለማየሁ እሼቴ ምናልባት በስድሳዎቹ መግቢያ ላይ ነው መሰለኝ፣ ባማረ ድምጹ - "ማን ይሁን ትልቅ ሰው" - በሚለው ዘፈኑ ላይ - "እባክህ አምላኬ ደጉን ዘመን አምጣ" - ሲል ለእግዚአብሄር ምልጃውን አቅርቦ ነበር። የየኔውን ዘመን ገምቶ አምላኩን የተማጸነው ከያኒ ዛሬስ ምን ታዝቧልምናልባት አለማየሁ እሼቴ እንደገና ቢያንጎራጉር "እባክህ አምላኬ ያን ዘመን መልሰውይል ይሆንበእርግጥ የዘንድሮው ከተሻለ ያምናው ታሪክ ነበር። አለመታደል ሆኖ እንጂ "ከዘመን ዘመን አሸጋግረንማለት ከኋለኛው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን በላቀ መንፈሳዊ ጽናት፣ በተሻለ ሠላምና ብልጽግና አሸጋግረን ማለት ነው። "ልማታዊው መንግሥትሥነ-ምግባሩንና ግብረገብነቱን ሸርሽሮ ሁሉንም ደረመሰው።
ሲኖ ትራክ ምንም አላጠፋም። ሲኖ ትራክ በቻይና የተፈረበከ ፈጣን ጉልበታማ መኪና ነው። ጥፋቱ የሹፌሩ ነው። ጥፋቱ የአሽከርካሪው ነው። በእርግጥ ጥፋቱ የአሽከርካሪው አይደለም። ጥፋቱ የሥርዓቱ ነው። ጥፋቱ በእድሜው ለጋ ለሆነው ወጣት ወይም ሱሰኛ ካለችሎታው አራተኛና አምስተኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ የሚሰጠው የየክልሉ መሥሪያ ቤት ነው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ በትምህርት ዲግሬ ከማግኘት ያላነሰ ፈተናና ውጣ ውረድ ነበረው። ቀድሞ መንጃ ፈቃድ ለማግኘት ከሁለተኛ ደረጃ ወደ ሶስተኛ፣ ከሶስተኛ ወደ አራተኛ፣ ከአራተኛ ወደ አምስተኛ፣ ለመዝለል እጅግ ከፍተኛ ልምድንና ብስለትን ይጠይቅ ነበር። ዛሬ መንጃ ፈቃድ በጉቦ መያዝ ከጉልት በቆሎ የመሸመትን ያህል እንኳን አይከብዱም። ዛሬ ሹፌሮችንና ረዳቶችን ለይቶ ማየት አይቻልም። ሹፌሩ አራራ ይዞት ጫት ለመቃም አንዱ ሥርቻ ጎራ ሲል ረዳቱ መኪናውን ያሽከረክራል። የታክሲው አሽከርካሪ ዕቃ ለመግዛት ሱቅ ሲገባ ወያላው ሁለት ቢያጆ ሰርቶ ይጠብቀዋል። የታክሲው ባለቤት ይህን ሁሉ ጉድ አያውቁም። ቢያውቁም፣ ታክሲው የዕለቱን ገቢ ይዞላቸው እስከመጣ ድረስ ለተሽከርካሪው ደህንነትም ሆነ ለተሳፋሪዎቹ ነፍስ፣ ቅጠል ተሸክማ አስፋልቱን ለምትሻገረዋ ባልቴትም ሆነ ወደ ቄስ ትምህርት ቤት ለሚጓዙት ጨቅሎች አይጨነቁም። እሳቸውስ ቢሆን ምን ያድርጉ – ለሾፌራቸውና ረዳቱ መንጃ ፈቃዱን የሠጠው መሥሪያ ቤትን የሕዝብ ጉዳይ ካልቆረቆረው።
ሥርዓቱ መንጃ ፈቃድ አስጣጡም ላይ ሆነ የበሰለ ልምድ ያላቸው የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን በአግባቡ እንዲሰማሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ነበረበት። ይህ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የሚታየው የበርካታ ሰዎች ውድ ሕይወጥ መጥፋትም ሆነ የንብረት መውደም ባልተከሰተ ነበር። ሥርዓቱ ዘመናዊ መንገድን ማንጠፍ ብቻ ሳይሆን አነዳድን፣ በርጋታ መቅደምንም ሆነ በመስመሮቹ ማህል ረግቶ የመንዳትን ሥነ-ጥበብ ቀርጾ ትምህርቱን ማሰራጨት ነበረበት። ፈጣን መንገድን ሥልጣኔ ለጎደለው አሽከርካሪ"ፈንጭበትብሎ መልቀቅ ራሱ "ቀይ ሽብርንማፋፋም ነው። ሲኖ ትራኮች "ቀይ ሽብርየተባሉት ለዚህ ነው። ከአዲስ አበባ አዳማ የተዘረጋው አውራ ጎዳና (motor way) ላይ መንዳት ከተክለ ኃይማኖት መርካቶ እየተሽለኮለኩ የመንዳትን ችሎታ ማሳያ መንገድ አይደለም። በፈጣን መንገድ ላይ ፍሬቻ ሳያበሩ መታጠፍ ወደ ሽንኩርት ተራው ተጋፍቶ እንደመግባት ቀላል አይደለም። በዘመናዊው መንገድ መንዳት "ሥልጣኔንእንጂ "አራዳነትንአይጠይቅም። የመንገዶቹን መስመሮች ማህል (driving field)ጠብቆ መንዳት፣ ወደ ሌላ መሥመር ለመግባት ፍሬቻ ማሳየት (turn signal)፣ እስር የተወተፈ መኪና ወይም ሞተር ሳይክል መኖር አለመኖሩን (blind spot) ማረጋገጥ፣ በጥንቃቄ የመቅደም ስልትን (take over) እንዲሁም ፍጥነትን መቆጣጠርና (speed control) ከፊት ካለው ተሽከርካሪ እርቀትን መጠበቅ (safe gap) ወዘተ፣ የመንዳት ችሎታ ብቻ ሳይሆን ሥልጣኔና (civilization) ለነፍሳት ሁሉ የመጠንቀቅ ሠብዓዊነት (humanity) ነው። በከተማ ውስጥ ለእግረኞች ቅድሚያ መስጠት ከሁሉም በላይ አስተዋይነት ነው። ምናልባት መኪና ማሽከርከር ፈቃድ ያላቸውን ዲያስፖራዎችን አሰባስቦ በአውራጎዳና ላይ አነዳድን በኤግዚቢት መንገድ የማሳየት ወርክ ሾፕ ቢዘጋጅ ጠቃሚ ይመስለኛል። ይህን ስል ካገራችን በቂ ችሎታ ያላቸው አስተዋይ አሽከርካሪዎች ጠፍተዋል ማለቴ ሳይሆን የውስጡንም የውጭውንም ልምድ መለዋወጡ ትምህርትን ከመቅሰምያ ዘዴዎች አንደኛው ነው ማሌቴ ነው። አምላክ ሀገራችንን፣ ወገናችንን ይጠብቀን፣ አሜን።

Saturday, March 12, 2016

ኦሮምያና "ልማታዊ ሙስናዎቿ"ከሚክያስ ግዛው (visit my blog  http://michyas.blogspot.no/ )
እኔ እንኳን ወያኔ በፈጠራቸው ዘረኛ የክልል ስሞች አካባቢዎችን መጥራት አልፈልግም ነበር። በዘር፣ ነገድ፣ ጎሳና ጎጥ የሚወሰን የማንነት ግንባታ (identity empowerment) አፍራሽ ይመስለኛል። ብቻ ይሁን እስቲ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ ወዘተ ማለቱን ትቼ እንደው እንደዘበት "ኦሮምያልበል። ኦሮምያ ውስጥ ሙስና (corruption) እንደ አንድ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ዘርፍ (political economic sector) ተቆጥሮ ዋልጌዎች ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ እየተገበሩት ይገኛሉ። ይህ በደጋግና ጀግኖች ሕብረተሰብ ማህል የተደነቀረው የክፋት ገጽታ የመልካም አስተዳደር መርሆችን (good governance principles)፣ ባህላዊ ትሥሥሮችንና ሥነ-ምግባርን በማጨለሙ ሕዝቡን ለድህነት ዳርጓል። እስቲ እኔ ከታዘብኩት ውስጥ ጥቂቱን ላካፍላችሁ።
እውነት (Truth)፣ እውነት እምነት ነች። ሰዎች ስለአካባቢያቸውም ሆነ የዓለም ዙርያ እንቅስቃሴና ክንውኖች እውነቱን የማወቅ መብት አላቸው። ሰዎች እውነትን ሲረዱ ወደፊት ሊተገብሩ ስላቀዱት ዓላማ ግንዛቤ ይጨብጣሉ። በኦሮምያ የስልጣኑ ባሌቤት ኦሕዴድ ቀድሞውም ቢሆን በእብለት መሠረት ላይ የታነጸ በመሆኑ እውነት ማንጸባረቅ አይችልም። ድርጅቱ ባለቀልም የዋርካ ሥዕል ያለበት ባንዲራ እያውለበለበ ወደ ስብሰባ አዳራሽ ከመንጎድ ውጭ ፋይዳው አይታይም። በአሮምያ ክንውኖች ሁሉ ህፀፅዊ(fallacious) ወደ መሆን ደርሰዋል። በየስብሰባው ውሃ የመይቋጥሩ አረፍተሃሳቦች (fallacious arguments) ይወረወራሉ። ባለስልጣናት ሕዝቡን በመናቅ አደናጋሪና አሳሳች (deceptive, misleading ; fallacious testimony) መረጃዎችን ይበትናሉ። የውስጡ መሠረታዊ ችግር ሳይመረመር ላይ ላዩን የተድበሰበሰ (disappointing; delusive) መፍትሄ መሰል ሃሳብ ቀርቦ ስብሰባው በተዳፈነ ሠላም (fallacious peace) ይጠናቀቃል። በእርግጥ ሁሉንም በአንድ ላይ መጨፍለቅ (generalization) ተገቢ አይደለም። የለበሱትን ሕዝባዊ አደራ በንፃት የሚጠብቁ ቢኖሩም የሙሰኞቹ ጥቁር ሥራ ግን በጎ ክንውኖችን ማጉደፉ አልቀረም። እውነት ኦሮምያ ምድር ሞታ ልትቀበር ትንሽ ቀርቷታል።
መሬት (Land)፣ መሬት በሕዝባዊ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስትውል ልማት ባግባቡ ይፋጠናል። በሃገራችን የመሬት ጉዳይ የፍትህ ጉዳይ አልፋና ኦሜጋ ነው። የተፈጥሮ ኃብት (Natural resources) ከጉልበትና ዓዕምሮ (labour and mental) ጋር ሲዋሃድ ምርትን (production) ያስገኛል። መሬት የተፈጥሮ ኃብት ዋነኛ መፍለቅያ ምንጭ ነች። ማንም ሠላምንና ጸጥታን፣ ልማትንና እድገትን የሚፈልግ ስብስብ የመሬትን ጉዳይ ፍትሃዊ (justify) ለማድረግ ሲል ጠቃሚ መሠረታዊ ህጎችን (system of rules)በቅጡ ይቀርጻል። ይህ ጉዳይ ፈጽሞ ተግባራዊ መሆን ካልቻለ ጥቁር ገበያዎች (black markets) እንደ አሸን ይፈላሉ። ጥቁር ገበያ በሙስና (Corruption) የሚመራ ፖለቲካዊ ምጣኔ ኃብታዊ ፍዳና ዕዳ ነው። መሬት የመንግሥት ኃብት እንዲሆን ፈላስፎችና የምጣኔ ኃብታዊ ሊቆች እጅግ ሠፊ ሳይንሳዊ ትንታኔ ሠጥተዋል። "መሬት ላራሹበኢትዮጵያ ተራማጆች ዙርያ ዘወትር ሲነሳ የቆየ ታሪካዊ መፈክር ነበር። የተጨቋኖችና አጋሮቻቸው እምቅ አስተሳሰብ የወለደው ይህ ታሪካዊ መፈክር ተንቆ ይባስኑ የኦሮምያ መሬት የቀማኞችና ሙሰኞች መገልገያ ሆኗል። በኦሮምያ መሬት አሞሌ ጨው ተሸክሞ ለመጣ ሁሉ በቀላሉ እንደምትቸረቸር ኮማሪት ተንቃለች። መሬት "በሶስተኛ ደላሎችስም እንደዋዛ የምትለወጥ ጉቦኛ ባለሥልጣናትና መዝባሪው ነጋዴ የሚሻሟት አሳዳሪ የራቃት ባለቤት አልባ ሆናለች። መሬት በኦሮምያ ምን ያልሆነችው አለአሜሪካ የተፈጠረችው በቀይ ሕንዶች ደም ላይ ነው። አሜሪካ የተገነባችው በአፍሪካውያን ባርያዎች ግፍና ሰቆቃ ነው። ይህን ግፍ የዲሞክራሲ ቋሚ ምሰሶ ወይም ዓምድ አይደለም። ገዥው መንግሥት ሰዎችን በፌደራል ፖሊስ ጥይት ካስገደለ በኋላ "ለዲሞክራሲው ግንባታ ገና ነን፤ አሜሪካ እስከ ስድሳዎቹ መባቻ ድረስ ሰዎች ይገደሉ ነበርብሎ ያወራል። አገዛዙ ልማቱን እየዘረፈ፣ ሰዎችን እንደ ቀይ ሕንዶች ከቀዪአቸው እያፈናቀለ፣ ጥሬ ሃብቱን ለባዕድ እየቸረቸረና "መሬቴን አትንኩያሉትን ነዋሪዎች እያሽመደመደ "ዲሞክራሲው ገና አልጎለበትምብሎ ያሾፋል። ይህን ትምህርት የቀሰሙት ከሱዛብን ራይስ ከሆነ ያሳዝናል። መልካሞቹን የዲሞክራሲ እሴቶችና የመልካም አስተዳደር መርህን ካደጉት ሃገሮች ተሞክሮ እየቀሰሙ ማዳበር ሲቻል መሬትን ለመቀራመት ብሎ ተወላጁን፣ አገር በቀሉን (indigenous) መግደል የዲሞክራሲ ባህሉም ወጉም አይደለም።
ኢንቨስትሜንት፣ (investment) እኔ ራሴ investment, establishment, department, እንደው ምናለፋችሁ «ment» ያለበት እንግሊዘኛ ሲነገር እፈራ ነበር። ግናስ የሠፈራችን አንድ አጉራ ዘለል "ኢንቬስተርተብሎ ከውጭ ሲመጣ ቃሉን ተለማመድኩኝ። ምን ሊቨሰትር ነውብዬ ስጠብቅ አቀባባይ ረድፈኞችን በእንግሊዘኛ ደልሎ አስደልሎ መሬት ጨመደደ። መሬቱን ደግሞ ሸጦ ገንዘቡን መሬቱን ከሰጡት ከባለስልጣናት ጋር ተካፈላው ሲባል ሰማሁ። በኦሮምያ ብዙ ኢንቬስተሮች ይስተናገዳሉ። ከባለሱቁ አንስቶ እስከትላልቅ ሳሙና፣ ዘይትና ብስኩት ፋብሪካ ድረስ በሙስናው ማህደር ተመዝግቦ በጉቦኛው ማህተም ይለፍ የተመታለት የንግድ ተቋም ሁሉ "እንቬስትሜንትተብሎ ይወደሳል። ባንዳንድ አካባቢዎች የኢንቬስትሜንቱ ባለቤቶች (clandestine wealth) "የማይታዩት ባለስልጣኖችወይንም ተባባሪዎቻቸው ሲሆኑ የንግድ ፈቃዱ የተመዘገበው ባንድ ጭቁን የኢንቬስተሩ ሎሌ ነው። ይህ ዘመናዊ የሎሌነት ሥራ የተቀዳው በቅኝ ግዛት ሥር ከነበሩት የአፍሪካ ሃገሮች ነው።
ስብሰባ (session)፣ አስተማሪያችን "ስብሰባ ሎጂክ (logic) መጠቀምያ ጠቃሚ ጊዜ ነውሲሉ እሰማ ነበር። የፍርድ ሸንጎ ሠብሳቢ የነበረው አጎቴ ደግሞ "የስብሰባ አዳራሽ ዝም ብሎ ተሰባስቦ እንቅልፍና ራስ ምታት መሸመችያ ቦታ አይደለምይል ነበር። ሰው ከተሰበሰበ ንድፈ ሃሳብ አፍልቆ፣ እልባት ያለው ውሳኔ ሸክኖ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ አለበት (Theory + practice = Praxis)። ኦሮምያ ስብሰባ ታበዛለች። በሃያ አምስት ዓመታት ኦሮምያ ያስተናገደችው ስብሰባ በሜትር ሲለካ የዓለም ሊግና የተባበሩት የዓለም መንግሥታት ማህበር ካደረጉት ስብሰባ በሶስት እጥፍ ይበልጣል። ምን ንድፈ ሃሳብ ተወረወረምን ተወሰነምን ተፈየደምንም። በእርግጥ እድሜ ለሙስና ሠማይ ጠቅስ ሕንጻዎች ቆመዋል፣ ጥሬ ኃብቱንና ምርቱን ማጓጓዣ ይሆን ዘንድ መንግሥት ዘመናዊ መንገድ አንጥፏል። የሕዝቡ ኑሮ ግን አልተሻሻለም። የሕዝቡ ባህልና እሴቶች ተደፍጥጠዋል። ተሰብሳቢዎች የሙስናንና ጉቦ መርሆችን በሰምና (wax) ወርቅ (gold) አሽሞንሙነው ይለያያሉ። ሰሙ "ሙስና ይጥፋሲሆን ወርቁ ደግሞ"ሙስና እጥፍ ይሁንነው። የመናገር ችሎታ፣ በእጅ የመሄድ አክሮባትና ድፍረት መለማመጃ የሆነው የኦሮምያው ሙስና ወለድ ስብሰባ ብዙ ገንዘቦች አባካኝ ጎጂ ባህል እየሆነ መጥቷል። ሃቀኛ ነጋዴዎች የመንግሥት ገቢ ለመክፈል ማለዳ ወደ አገር ውስጥ ገቢ ሲሄዱ "ፋይሉ አልተገኘምተብለው በኪራይ ሰብሳቢዎች ይባረራሉ። ችግሩን ለማን አቤት ይባላል። አለቆች ስብሰባ ላይ ናቸው። ሃቀኞች ዓመታዊውን ግብርና መንግሥት የደነገገውን ቫት ለመክፈል እንኳን ተቸግረዋል። የመንግሥትን ገቢ ለማስገባት ሙስና ለምን አስፈለገፋይሉ ጠፍቷል በመባሉ ምክንያት ግብር የተቆለለበት ሃቀኛ ነጋዴ ሲጉላላ ማየቱ አሳዛኝ ነው። ይህ ክፋት ኬንያና ናይጄርያም እንኳን አልተከሰተም። በኦሮምያ "ስብሰባሙስናን ማጠናከርያና ኪራይ ሰብሳቢዎችን ማሰልጠኛ ሠንበቴ ከሆነች ሰነበተች።
ፍትህ (justice)፣ በኦሮምያ ፍትህ ደብዝዛለች። ደብዳቢውና ተደብዳቢው ፖሊስ ጣብያ ቢሄዱ ተደብዳቢው ይታሠራል። ዘራፊና ተዘራፊ ሸንጎ ፊት ቢቀርቡ ተዘራፊው ተሸማቆ ከእልፍኙ በአፋጣኝ እንዲወጣ ይደረጋል። ዳኛና ጠበቃ የጥቅም ትሥሥር አድርገዋል። ፍርደ ገምድል ዳኛው የባለጉዳዩን ሳይሆን የጠበቃውን እጆች ያያል። ደህና ጉቦ ሰጪ ጠበቃ ዝናን ያተርፋል፣ በርካታ ደንበኞች ያፈራል። ለፍትህ የቆሙ ጠበቆች ደግሞ ሥራ ፈተዋል። "ፍትህ ይስፈንእያሉ ሲጮኹ ሙሰኛው ዳኛና መሠሪው ጠበቃ ይሳለቁባቸዋል። ፍትህ በኦሮምያ እጅግ ተረግጣለች። ታድያ በአቋራጭ ለመክበር ኢፍትሃዊ ነገሮችን ሳይፈሩ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። በኢፍትሃዊ አሠራሮች ልምድን የቀሰሙት ደላሎችና አቀባባዮች የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ። እነርሱ ለዳኞችና ጠበቆች ሐሰትን አደልቦ እንደምን ማሸነፍ እንደሚቻል ህግን ሳይፈሩ፣ ሰውን ሳያፍሩ ምክር ያካፍሏሉ። ክፉዎች የምክር አገልግሎት በሚሰጡባቸው ቢሯቸው ውስጥ የፍትሃብሄር ህግና መጽሃፍ ቅዱስ ሁለቱም ጠረቤዛው ላይ ተቀምጠዋል። እግርግዳው ላይ ደግሞ "እግዚአብሄር ያያልየሚል በእንግሊዘኛና ኦሮምኛ የተጻፈ ጥቅስ ተሰቅሏል። አይ ዘመን!
አቀባባይ ረድፈኛ ሚና (liaison role between the corruptor and corruptors of public officials) አቀባባይ ረድፈኛ (እንደ ራሴ አተረጓጎምበሙያው ደላላ ያልሆነ ስልታዊ ደላላ ነው። ከደላሎች የሚለየው ነገር ቢኖር ባለስልጣኖችን በጥቅም አሳውሮ መቅረብ መቻሉ ነው (dangerous liaison)። የመናገርና የማሳመን ፣ የማዘበራረቅና የማዛባት ችሎታ የተላበሱት አቀባባይ ረድፈኞች አገዛዙ ባመቻቸው የሙስና መሠላሎች ወደ ላይ የወጡ የዘመኑ አራዶች ናቸው። እነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች ጉቦ ሰጪንና ጉበኛን፣ ሠነፍ ተማሪንና ቦዘኔ አስተማሪን፣ ባለስልጣንንና አራጣ አበዳሪውን፣ ፍርደገምድል ዳኛውንና ቆቁን ጠበቃ፣ ወዘተ፣ አገናኝ ናቸው። ካለነዚህ አቀባባይ ረድፈኞች እገዛ ውጭ ባለስልጣን ሊመዘብርና ሙስና ሊቀበል ያዳግተዋል። መሥሪያ ቤቶችን ሁሉ የሙስናና ምዝበራ አርማ ተሸካሚ ያደረጉት እነዚህ በስልታዊ ብረዛ ሳይንስ የተካኑት አቀባባይ ረድፈኞች ዋዛ አይደሉም። ህግና ፍትህ ሚኒስቴር – ሙስናና አድልዎ ሚኒስቴር፣ የንግድ ሚኒስቴር – የምዝበራ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስቴር – መሃይምነት ማስፋፍያ ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር የጨረታና መሬት ሽሚያ ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር – የዋጋ ንረት ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር – ኢንቬስትሜንትና ሃዋላ ሚኒስቴር፣ የእርሻ ሚኒስቴር – እንጀራና በርበሬ ላኪ ሚኒስቴር፣ ወዘተ፣ እንዲሆን ሚናውን የተጫወቱት መለኞች ከአስመጭና ላኪዎቹ ወይም ሕንጻ አከራዮቹ ባለስልጣኖች ቢሮ ላፍታም ቢሆን የማይርቁ የሙስናና ዝርፍያው ተቋም (kleptocracy) ባለውለታዎች ናቸው።
ቋንቋ (mother tongue)፣ በኦሮምያ ኦሮሚፋ ብቻ ነው የሥራ ቋንቋ። ልጆቿ ሌላ ክልል ሄደው መሥራት አይችሉም። እሷም ከትግራይ ወይም አማራ አልያም ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ ወይም ደቡብ ክልሎች የሚመጡትን ልጆች አታስተናግድም። አትድረሱብኝ – አልደርስባችሁም ብላለች። ኦሮምያ አማርኛ ቋንቋን እንደ መጨቀኞ መሣርያ ያህል በመጥላትዋ ሳብያ አፈሯን ፈጭተው፣ ውሃዋን ጠጥተው ያደጉትን ኦሮምኛ የማይችሉትን አንጡራ ልጆቿን እንኳን የጉዲፈቻ ዜግነት ከልክላቸዋለች። ኦሮምያ አማርኛ የነፍጠኞች ቋንቋ መሰላት እንጂ የጋራ መግቢያብያ ቋንቋ ልማትን እንደሚያፋጥን ቴክኖሎጂንም እንደሚያስፋፋ አላጤነችም። አማርኛ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ ለብዙ ዓመት ማገልገሉ ማንንም ባልጎዳ ነበር። የሆነስ ሆነና የኢትዮጵያ ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ እንግሊዘኛ መሆኑስ ይታወቃልኦሮምያ ይህን የልማት እንቅፋት ሽራ ይልቅስ ብዝህነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ አንድነትን ማጠናከር ቀዳሚ ሚናዋ ሊሆን ይገባል።
ባጠቅላይ ሃቀኝነት፣ ደግነት፣ ፍትሃዊነት፣ ሙስናንና ጉቦን መጸየፍ – እነዚህ የሕዝቡ የመልካም ባህርይ መገለጫ የሆኑት እሴቶች በኦሮምያ ውስጥ ወደ ጉሮኖ ተወርውረዋል። እነዚህን እሴቶች ዳግም ሊያንጸባርቅ የሞከረ ሁሉ መሳለቅያ ይሆናል። ኬንያና ናይጄርያ በሙስናና ጉቦ ጫፍ ላይ የደረሱ ሃገሮች እየተባሉ ሲነገር ቆይቷል። ኦሮምያ ደግሞ በጥቂት ዓመታት ክብረወሰኑን አልፋ የሙስናና ጉቦ ፍልስፍና የተሃድሶ ምድር እንዳትሆን ያሰጋል። ይህን የመሳሰሉት ግፎች ናቸው ዛሬ ሕዝቡን ለአመጽ ያነሳሱት። የፍትህ መዛባት፣ እስር፣ ግድያና የምጣኔ ኃብቱ ይዞታ ልዩነት ካልተገደቡ በቀር ሕዝቡን ለመብቱ ከመታገል የሚያቆመው አንዳች ኃይል የለም። የፌደራል መንግሥቱ እጆች "አመድ አፋሽወይም የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ እንዳሉት"የኢትዮጵያ ሕዝብ ወርቅ ቢያነጥፉለት..."ሆኖ አይደለም ይህ ሁሉ አመጽ የበረከተው። ሙስናው፣ የአስተዳደር በደሉ ኑሮውን አናግተውበት በድህነትና ሰቆቃ ጅራፍ መገረፉ፣ በአምባገነኖች (tyranny, timocracy, oligarchy, plutocracy) ውሳኔ ብቻ መነዳቱ አልበቃ ብሎ ቀማኞች መሬቱንና የመሬቱን የተፈጥሮ ገጸበረከት በጠመንጃ አስገድደው (military command) በጠራራ ፀሃይ ስለሚዘርፉት እንጂ። የእርምቱ እርምጃ ከሰላው ጫፍ ይጀመር።
ጥቂቶቹ የትግራይ ሕወሓት መሪዎች ለም የሆኑትን የጎንደርና ወሎ አጎራባች መሬቶች በማናለብኝነት ተነሳስተው ወደ ትግራይ ክልል መደባለቃቸው ያስከተለውን አደጋና የህዝብ ቁጣ በሚቀጥለው ጊዜ እዘግባለሁ።
እግዚአብሄር ቸር ዘመን ያምጣልን፣ አሜን

Tuesday, March 8, 2016

የነብርን ጭራ አይዙ ከያዙ አይለቁ!
እነሆ እኛ ኢትዮጵያዉያን ህብረት፣ መደጋገፍ፣ ስምምነትና አርቆ አሳቢነት የሚጠይቅበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል። ያለፉት ዓመታት የወያኔውን ጥቁር ሥርዓት ምንነት አሳይቶናል። ይህንን ብቻ አይደለም፤ በአምባገነን ሥርዓትና ለቅኝ ገዥዎች በባንዳነት በሚያድር ሥርዓት መካከል ያለውን ልዩነትም በሚገባ አሳውቆናል። የንጉሡ ዘመን ኋላ ቀር ነበር። የደርግ ዘመን አምባገነን ነበር። በሁለቱም ሥርዓት ወቅት ግን ሃገር ነበረች። ኢትዮጵያ እስከ ባህረ በሯ ሉዓላዊ እስከ ሕዝቦቿ ክቡር ነበረች። ዛሬ ለየት ያለ ነው። ወያኔ ዘረኛ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሙስናዊ አምባገነን ሥራዓት ቋሚ ተጠሪ ስብስብ ተቋም ብቻ አይደለም። ወያኔ "የአናቁረህ ግዛ" ግፍ አራማጅ ብቸኛ የቀማኞች ድርጅት ብቻ አይደለም። ወያኔ ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያን ለውጭ ባለሃብቶች የሸበሸበ የኃጢአተኞችና "የአስረሽ ምቺ" ዳንኪረኞች፣ መዝባሪዎች ስብስብ ብቻ አይደለም። ወያኔ የሁሉም የኃጢዓት ሥርዓቶች ድምር ነው። ወያኔ ድንገት ከተሰባሰበበት ደደቢት ሸለቆ ተንከባሉ ሠይጣን ዋሻ ውስጥ ለአመታት ከርሞ ዲያቢሎስ ሳያኝክ የተፋው የርኩስ ሥርዓት ቁንጮ ነው። እድሏ ሆኖ ቅድስት ኢትዮጵያ የዚህ ሥርዓት ተሸካሚ ሆናለች። እንዲያ እንዳልተከበረች፣ እንዲያ እንዳልተፈራች ሃገራችን ኢትዮጵያ ለቅኝ ገዥዎች ቅርጫ ቀረበች። ሥርዓቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን በቁሟ የገነዘ፣ ሕዝቧን ያስጨነቀ መሪር ሥርዓት ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችንን ከዚህ ሥርዓት የሚገላግላት ቆራጥነትና በህብረት መነሳት ብቻ ነው። ህዝብን በመርዘኛ ራዕይ ሰልቦ፣ ወጣቱን በሥራ አጥነት አጠውልጎ ለስደትና ሴተኛ አዳሪነት እየዳረገ፣ ነዋሪውን በልማት ስምና በከተማ ማስፋፋት እያፈናቀለ ሕዝብን በቅኝ ገዥዎች ቋንቋና በምጣኔ ኃብት እድገት እያደናገረ የሃገሪቱን ሃብት መዝብሮ ወደ ውጭ በማሸሽና በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ በመዝፈቅ በጥቂቶች ስም ሃብት እያከማቸ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሊገዛ የሚቃጣ ዘመነኛ የግፍ ሥርዓት አራማጅ ወያኔ ብቻ ነው።
በዘረፉት ገንዘብ ልጆቻቸውን እንደ ልዑላውያን ልጆች በምዕራቡ ዓለም ወይም ቻይና በቅምጥል ሊያኖሩ የሚያስቡ ሞኞች ወቅቱን ያልተገነዘቡ ብቻ ናቸው። ከጭቁን ሕዝብ በተመዘበረ ነዋይ ኬክ ገዝቶ መዘመር፣ ሻምፓኝ አንስቶ ጤንነትን መመኘት ሲዖል አፋፍ ቆሞ ዲያቢሎስን መጋበዝ መሆኑን እንዲሆም ከረሃብተኞች በተነጠቀ ገንዘብ በተገዛ ሸማ መዋብ በደም በተለወሰ ክር የተሰፋ መሆኑ ገና ያልገባቸው ይልቁንም የሥርዓቱ መበስበስ ገና ያልታያቸው ርህራሄ ቢሶች ብቻ ናቸው። ከድሆች መሬት ነጥቆ በሙስና፣ በዘረፋ በተገነቡ ዘመናዊ ሕንፃ ውስጥ መኖር ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ መቀበር መሆኑ ገና ያልገባቸው እብሪተኞች ብቻ ናቸው። ከድሆች አፍ በተነጠቀ ገንዘብ ሠማይ ጠቀስ ፎቆቻቸውን ወደ ላይ አንጋጠው የሚመለከቱ የፀሃይ ብርሃን የማትጠልቅ የሚመስላቸው መሃይማን ብቻ ናቸው። ግንዛቤ ያጠራቸው ባለስልጣናትና ልጆቻቸው የሙስናው ተጠቃሚዎች፣ ገና በሼራተንና ሂልተን አልኮል የሚራጩት፣ የሉካንዳው ቤት ሠልፈኞች፣ የዳንኪራ ቤቱ ጋጠ ወጦችም ጭምር ሕዝባዊው ሱናሜ መምጣቱን ፈፅሞ ያልተገነዘቡት ዘመኖች ናቸው። እነርሱ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደሚፈነጥዙ ዓይነት የግፍ ሥሪቶች ናቸውና የገናናዋ ኢትዮጵያ እንባ ያቅበዘብዛቸዋል። የገባቸው፣ አዎ የገባቸው ገዥዎች፣ ነገ ዓይደለም ዛሬውኑ ራሳቸውን ነፃ ያወጣሉ። የገባቸው፣ የአምላክ ምህረት የቀረባቸው፣ ይቅርታ ጠይቀው መጪው ዘመን ለነሱም ለሃገሪቱም ብሩህ እንዲሆን ይተጋሉ። የገባቸው፣ ልባቸው ያልደነደነው የግፍ ሥርዓት ፈጽሞ እንዲቀበር የሚመኙ የሕዝቡን ጥያቄ ይቀበላሉ። የገባቸው፣ የድሆች እንባ ሲንቆረቆር አይተው ልባቸው በርኅራሄ የረሰረሰው አዲስ ታሪክ ይሠራሉ። ያዘኑ፣ የረሃብተኛውን ሕጻን አጥንት የቆጠሩ የነጠፉ ጡቶችን አይተው የሚያለቅሱ ገዥዎች ሥልጣናቸውን በሠላም ለህዝብ ያስረክባሉ። ዕድሉ አሁንም አለ። ይህ ዕድል ነገ ላይኖር ይችላል። ሳዳም ሁሴንና ጋዳፊ፣ ያውም ሃገራቸውን ከልብ የሚወዱት እንኳን ይህ ዕድል አምልጧቸዋል። እናንተስ?
ዛሬ የበደሉ ጽዋ ሞልቶ ቢፈስ ሕዝብ በቁጣ ተነስቷል። ሕዝብ በቃኝ፣ መረረኝ ብሏል። ሁሉም ሊተባበርና ከትግሉ ጎን መሰለፍ አለበት። ዛሬ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ወላይታ፣ ሲዳማ፣ አኙዋክ፣ ከንባታ፣ ከፊቾ እያልን የገበጣ ጨዋታ የምንጫወትበት ወቅት አይደለም። እኛ ኢትዮጵያውያን እንደቀድሞ ተታለን አንድ የበሰበሰሰ ሥርዓት በሌላ አፋኝ ሥርዓት ሲተካ አይተን ዝም የምንል ወይንም ወያኔ አንዱን ዘር ካንዱ ሊያጋጭ በተለመው "የአልሞት ባይ ተጋዳይ" ስልቱ ውስጥ የምንዘፈቅለት ቂሎች አይደለንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ትግሉን አመካኝቶ ሌላ ነውጥ ሊያመጣ የሚችል ኃይልን እሹሩሩ የምንልም አይደለንም። እኛ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በኋላ ፈጽሞ አንከፋፈልም። የወያኔው ሥርዓት የጥቁር አምባገነንነትን ቀለም፣ የአንድ ዘር የበላይነት የቅኝ ገዥዎች ቅጅ የግፍ አገዛዝ መርህን፣ የእብለት አካሄድንና የሸፍጥ ስልት ፖለቲካ ምንነትን እንድናውቅ አስችሎናል። በእርግጥ ዘረኝነትንና ልዩነትን አሽቀንጥረን በኅብረት እንድንታገል፣ በአንድ ላይ እንድንቆምም ትምህርት ሆኖናል። በልማት ስም ቅኝ አገዛዝዝን በዲሞክራሲ ስም ጭለማ ያመጣብንን ሥርዓት ሁላችንም መርምረነዋል። እነሆ ዛሬ - ሁላችንም በአንድነት "መሬት ላራሹና" "ሕዝባዊ መንግሥት" ይመስረት መፈክሮችን የምንተገብርበት ወሳኝ ዘመን ላይ ደረስናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ተነስቷል። ዛሬ የተጀመረው ሕዝባዊ ትግል ቢዳከም እንደገና መቀመቅ ውስጥ የምንገባው እኛው ነንና ትግሉን ይበልጥ ማፋፋም አለብን። "የነብርን ጭራ አይዙ - ከያዙ አይለቁ!
ሕዝብ ያሸንፋል፤ ኢትዮጵያ እንደቀድሞዋ በነጻነትዋ ትራመዳለች። ኢትዮጵያ ግርማ ሞገሥዋ ይመለሳል።
ሚክያስ ግዛው

Friday, January 22, 2016

ሕወሃት ስልጣን ከጨበጠ ጀምሮ በኢትዮጵያ የዘረጋዉ ፖለቲካ በዘር ላይ የተመሰረተ ከፋፋይ ፖለቲካ ነዉ። ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰብ አገር ናት። በታሪኳ የተሰሩ ብዙ ስተቶችና በደሎች አሉ። በአንጻሩም ደግሞ ኢትዮጵያዉያን ከተለያዩ ቋንቋዎችና ክልሎች በሰላም በፍቅር ኖረዋል፣ ተዋደዋል፣ ተደባልቀዋል።ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያዉያን በሃገር ዉስጥ እና በአለም ዙሪያ ባደረጉት ሰላላምዊ ስለፎች ለማየት እንደተቻለዉ አብሮ የመሥራቱንና በጋራ የመንቀሳቀሱን አማራጭ የወሰዱ ይመስላል። ይህ መልካ ጅማሬ የበለጠ ተጠናክሮ ከገፋ ያለምንም ጥያቄ የሕወሃት ፍጻሜ እንደሚሆን መጠራጠር የለብንም።
አምላክ ኢትዮጵያን ይጠብቃት።

Tuesday, January 19, 2016