Monday, March 29, 2021

ተረኝነት ለወያኔም አልጠቀማት

ኦነግ ፊንፊኔ ብሎ አውጆ ሥልጣን ከመያዙ በፊት ሥራ ላይ እያዋለ ያለው ቀዳሚው ስልት ወይም የሥራ ልምምድ "ተረኝነትይባላል። "አማራ ሶስት ሺህ ዓመት ገዝቷል፣ ትግሬ ሃያ ስምንት ዓመት ገዝቷል፣ ተራው የእኛ ነውየሚለው የተረኝነት ቦለቲካ ከየት እንደመጣ አይታወቅም። ግን መሬትን በመቸብቸብ፣ ገንዘብ በመዝረፍ፣ ሥልጣን ካለችሎታ በመያዝ የሚተገበረው ተረኝነት ለነገ የሚቀመጥ አበሳ ነው። በኃይለሥላሴ ዘመን እኮ ሥልጣን በትምህርት ችሎታ ነበር የሚለካው። በደርግ ዘመን የነበሩት እውቅ የኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ ቦታ የያዙት በእውቀታቸው ነበር። በንጉሡም በደርግም ዘመን ቁልፍ ቦታ ላይ የነበሩት የኦሮሞ ምሁራን ለዕይታ እኮ አልነበረም ወንበሩን የያዙት በእምቅ ችሎታቸውን አስተዳደርን ሊተገብሯት እንጂ።

No comments:

Post a Comment