ኦነግ - ፊንፊኔ ብሎ አውጆ ሥልጣን ከመያዙ በፊት ሥራ ላይ እያዋለ ያለው ቀዳሚው ስልት ወይም የሥራ ልምምድ "ተረኝነት" ይባላል። "አማራ ሶስት ሺህ ዓመት ገዝቷል፣ ትግሬ ሃያ ስምንት ዓመት ገዝቷል፣ ተራው የእኛ ነው" የሚለው የተረኝነት ቦለቲካ ከየት እንደመጣ አይታወቅም። ግን መሬትን በመቸብቸብ፣ ገንዘብ በመዝረፍ፣ ሥልጣን ካለችሎታ በመያዝ - የሚተገበረው ተረኝነት ለነገ የሚቀመጥ አበሳ ነው። በኃይለሥላሴ ዘመን እኮ ሥልጣን በትምህርት ችሎታ ነበር የሚለካው። በደርግ ዘመን የነበሩት እውቅ የኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ ቦታ የያዙት በእውቀታቸው ነበር። በንጉሡም በደርግም ዘመን ቁልፍ ቦታ ላይ የነበሩት የኦሮሞ ምሁራን ለዕይታ እኮ አልነበረም ወንበሩን የያዙት በእምቅ ችሎታቸውን አስተዳደርን ሊተገብሯት እንጂ።
Monday, March 29, 2021
Sunday, March 21, 2021
የኦነግ ሥልጣን የመያዣ ስልቶችና ኢትዮጵያን የማፍረስ እቅዱ – ከሚክያስ
Saturday, March 13, 2021
#stop killing each other
አማራ ይህ ዓይነቱ ዘግኛኝ ግፍ የሚፈራረቅበት ሌሎች ያጡት ነገር ግን እርሱ ብቻ የጨበጠው ጥቅም ኖሮ አይደለም። አማራ እንደ ሌሎች ወገኖቹ ደሃ ነው። ታድያ ምን አጠፋ -እግዚአብሄርን ማምለኩ፣ ሃገርን፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራውን መውደዱ ነው ወንጀሉ? እንደው ለነገሩ አማራው ብቻ ነው ኢትዮጵያን የሚወደው?ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ጋሞው፣ ቤንሻንጉሉ፣ ጉራጌው፣ ወዘተ፣ ሁሉም ኢትዮጵያን ይውዳል። ለምን ይሆን ታድያ አማራው ለእልቂት የተመረጠው? ምን የተለየ በደል ሰርቶ ነው ሕወሃትና ኦነግ አማራው ሠለባ እንዲሆን የፈረዱት? ቅኝ ገዥዎች የተሸነፉት በመላው ኢትዮጵያዊ ትብብር ነው። አማራው ብቻውን አድዋ አልዘመተም። ግን ለምን ይሆን አማራው ላይ ብቻ እልቂት፣ ግድያ፣ እገታ፣ ማምከን፣ ንብረት ማቃጠል፣ ወዘተ፣ የተፈረደው? በእርግጥ አማራው ላይ እልቂት እንዲፈጸም ሠይጣናዊ ሃሳቡን ያረቀቀው ወያኔ "ዘር ከዘር አፋጅቴ ኢትዮጵያን ለሺህ ዓመት በማን አለብኝነት እገዛለሁ" ከሚል አላዋቂነት የተነሳ ነው። ወያኔ ይህን ድንቁርና የወረሰው ከቅኝ ገዥዎች ነው። ይህን አላዋቂነት ጽንፈኞችና አማራ-ጠል ምሁራን ተጋሩት። ይህን አላዋቂነት ሃገር እንድትፈርስ የሚፈልጉ ሁሉ ከአድማስ አድማስ አናፈሱት። በዘር እልቂት ሽፋን ሚኒልክ ቤተ መንግሥት መግባት የሚፈልጉ ሁሉ ዘረኝነትን በወጣቶች ዓዕምሮ ውስጥ እንዲያድር ብዙ ደከሙ።