Thursday, April 22, 2021
አማራንም ኢትዮጵያንም ማጥፋት ፈጽሞ አይቻልም! - ሚኪያስ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Tuesday, April 20, 2021
Stop 🛑killing
Be the voice for the voiceless
@Dr Abiy Ahimed
#stop killing Amhara
#stop killing Tigray
Saturday, April 10, 2021
Sunday, April 4, 2021
Monday, March 29, 2021
ተረኝነት ለወያኔም አልጠቀማት
ኦነግ - ፊንፊኔ ብሎ አውጆ ሥልጣን ከመያዙ በፊት ሥራ ላይ እያዋለ ያለው ቀዳሚው ስልት ወይም የሥራ ልምምድ "ተረኝነት" ይባላል። "አማራ ሶስት ሺህ ዓመት ገዝቷል፣ ትግሬ ሃያ ስምንት ዓመት ገዝቷል፣ ተራው የእኛ ነው" የሚለው የተረኝነት ቦለቲካ ከየት እንደመጣ አይታወቅም። ግን መሬትን በመቸብቸብ፣ ገንዘብ በመዝረፍ፣ ሥልጣን ካለችሎታ በመያዝ - የሚተገበረው ተረኝነት ለነገ የሚቀመጥ አበሳ ነው። በኃይለሥላሴ ዘመን እኮ ሥልጣን በትምህርት ችሎታ ነበር የሚለካው። በደርግ ዘመን የነበሩት እውቅ የኦሮሞ ልጆች ከፍተኛ ቦታ የያዙት በእውቀታቸው ነበር። በንጉሡም በደርግም ዘመን ቁልፍ ቦታ ላይ የነበሩት የኦሮሞ ምሁራን ለዕይታ እኮ አልነበረም ወንበሩን የያዙት በእምቅ ችሎታቸውን አስተዳደርን ሊተገብሯት እንጂ።
Sunday, March 21, 2021
የኦነግ ሥልጣን የመያዣ ስልቶችና ኢትዮጵያን የማፍረስ እቅዱ – ከሚክያስ
Saturday, March 13, 2021
#stop killing each other
አማራ ይህ ዓይነቱ ዘግኛኝ ግፍ የሚፈራረቅበት ሌሎች ያጡት ነገር ግን እርሱ ብቻ የጨበጠው ጥቅም ኖሮ አይደለም። አማራ እንደ ሌሎች ወገኖቹ ደሃ ነው። ታድያ ምን አጠፋ -እግዚአብሄርን ማምለኩ፣ ሃገርን፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራውን መውደዱ ነው ወንጀሉ? እንደው ለነገሩ አማራው ብቻ ነው ኢትዮጵያን የሚወደው?ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ጋሞው፣ ቤንሻንጉሉ፣ ጉራጌው፣ ወዘተ፣ ሁሉም ኢትዮጵያን ይውዳል። ለምን ይሆን ታድያ አማራው ለእልቂት የተመረጠው? ምን የተለየ በደል ሰርቶ ነው ሕወሃትና ኦነግ አማራው ሠለባ እንዲሆን የፈረዱት? ቅኝ ገዥዎች የተሸነፉት በመላው ኢትዮጵያዊ ትብብር ነው። አማራው ብቻውን አድዋ አልዘመተም። ግን ለምን ይሆን አማራው ላይ ብቻ እልቂት፣ ግድያ፣ እገታ፣ ማምከን፣ ንብረት ማቃጠል፣ ወዘተ፣ የተፈረደው? በእርግጥ አማራው ላይ እልቂት እንዲፈጸም ሠይጣናዊ ሃሳቡን ያረቀቀው ወያኔ "ዘር ከዘር አፋጅቴ ኢትዮጵያን ለሺህ ዓመት በማን አለብኝነት እገዛለሁ" ከሚል አላዋቂነት የተነሳ ነው። ወያኔ ይህን ድንቁርና የወረሰው ከቅኝ ገዥዎች ነው። ይህን አላዋቂነት ጽንፈኞችና አማራ-ጠል ምሁራን ተጋሩት። ይህን አላዋቂነት ሃገር እንድትፈርስ የሚፈልጉ ሁሉ ከአድማስ አድማስ አናፈሱት። በዘር እልቂት ሽፋን ሚኒልክ ቤተ መንግሥት መግባት የሚፈልጉ ሁሉ ዘረኝነትን በወጣቶች ዓዕምሮ ውስጥ እንዲያድር ብዙ ደከሙ።
Wednesday, March 10, 2021
Monday, March 8, 2021
Sunday, March 7, 2021
Tuesday, February 23, 2021
Monday, February 15, 2021
ኢትዮጵያ ምንም አትሆን፣ ግን እስከመቼ እንዲህ በስቃይ! አምላኬ?
ሚክያስ
ኢትዮጵያ ትላልቅ አደጋዎችን ተቋቁማ ነው ኅልውናዋን የምታስቀጥለው። በፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ወቅት ንጉሡ ሀገር ጥለው ቢሰደዱም እነ አበበ አረጋይ፣ ኃይለማርያም ማሞ የመሳሰሉ ጀግኖች መንግሥትዋ የተበተነ ኢትዮጵያን ታደጉ። ኢጣልያ ባንድ በኩል ከጀርመን ጋር ያደረገችው መተባበር ዓለም አቀፍ ጫና ሲያሳድርባት በሌላ በኩል ደግሞ አርበኛች ያሳረፉባትን ዱላ መቋቁም ተስኗት አዲስ አበባን ለቃ ፈረጠጠች። ደርግ ሥልጣን በያዘ ማግስት ዘመናዊ ሶቭየት ሕብረት ሠራሽ ብረት ለበስ የጦር መሳርያ እስከአፍንጫዋ የታተቀችዋ ሶማልያ ድንገት ወረራ ስታደርግም ኢትዮጵያ ዝግጁ አልነበረችም። ንጉሡ ከአሜሪካ የሸመቱትን መሳርያ ማስረከብ ያልፈለገው የአሜሪካው ፕሬዚዴንት የካርተር አስተዳደር ኢትዮጵያን እጅግ ነበር የጎዳት። ይሁንና ግን ባጭር ጊዜ ውስጥ ሠልጥኖ ወደ ግምባር የገባው ሚሊሽያ ለወራት በጀግንነት ሲከላከል ለቆየው የኢትዮጵያ አየር ኃይልና የጦር ሠራዊት ብርቱ አጋዥ በመሆን ሶማልያ በቁጥጥሯ ስር አድርጋ የነበሩትን መሬቶች ለቃ ወደ ሞቃዲሾ እንድትፈረጥጥ አደረጋት። ኢትዮጵያ ሌላ መከራም ወደቀባት። ሕወሃት የተባለ ከኢጣልያም ሶማልያም የባሰ ነጻነቷን የሚለበልብ እርኩስ ዘረኛ ኃይል ከራሷ ጉያ ውስጥ ወጣ።
የህወሃት የዘር ፖለቲካ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ በማድረግ፣ ድህነትንና ስደትን በማባባስ ብቻ አላበቃም፤ አማራውን በማስፈጀት ጭምር እንጂ። ህወሃት አራት ኪሎ እንደገባች የዘር ፖለቲካውን በአማራው አንገት ላይ እንደ ዘንዶ ጠመጠመች።"በዘሩ እየተመካ ብሄረሰቦችን ሲጨቁን የነበረው አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም፣ ትግሬን ትታችሁ አማራውን ፍጁ" የሚል የዘር መድሎ (apartheid)ህግ የቀረጸችው ህወሃት - እልቂቱን የበደኖውና አርባጉጉው ተራራ አምባሳደር አድርጋ በላከችው አቶ ታምራት ላይኔ በኩል ተፈጻሚ አደረገች። የዘር ማጽዳቱ (ethnic cleansing) ሂደት በቡርቃ ዝምታ ትርክት ጎልብቶ የመኖር ዋስትና በተነፈገው ደሃው አማራ ላይ ተከታተለ። ለሰላሳ ዓመታት መዋቅራዊ ድጋፍ ተችሮት በበደኖና አርባጉጉ የተጀመረው አማራውን የመፍጀት (genocide) እቅድ የተፈናቃዮችና የሟቾች ቁጥር በማስመዝገብ ብቻ እየታለፈ ነው። አማራው ላይ የሚደረገው የዘር ማጽዳትና የዘር ፍጅት በግጥምና በጽሁፍ ብዛት፣ በሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ውግዘት፣ በሃዘን መግለጫዎችና ማሳሰብያዎች እሮሮ፣ በፍትሃትና ነፍስ ይማር ጸሎት ሊቆም አልቻሉም። ማዕከላዊውን ኃይል ማጠናከር ያልቻሉት ዶክተር አብይ ከመጡ በኋላም አማራው እየታረደ ነው።
ዶክተር አብይ የቀድሞው ህወሃት የዝርፊያ ሥርዓት ተጠቃሚዎቹን ዓዕምሮ ሳያጸዱ ደምረው ያቋቋሙት ብልጽግና ሁለት ተጻራሪ ፍላጎቶች ያሏቸውን ቡድኖች አንድ ላይ የሰበሰበ ድርጅት ነው። ይህ ውስጣዊው ችግር የዶክተር አብይን የመምራት አቅም ውሱን አደረገው። ኦነግ ሸኔ -እምዕራብ ወለጋ ላይ በከፈተው ጦርነት ሳብያ በኢትዮጵያ ውስጥ የተረጋጋ መንግሥት እንዳይኖር ሆነ። ዶክተር አብይ በምዕራብ ኢትዮጵያ ሃገርን ያስተዳድራሉ ማለት አይቻልም። የዶክተር አብይ መንግሥት መከላከያ ኃይል ፊት ለፊት ካገኘው ኦነግ ሸኔ ጋር ሲፋለም – የኦነግ ደጋፊ የሆኑት ብልጽግና ውስጥ ያሉ ረድፈኞች እጫካ ካለው ኦነግ-ሸኔ ጋር ይደራደራሉ። መከላከያው አባ ቶርቤን ሲከላከል እነዚሁ ረድፈኞች በሌላ ስውር መንገድ አማራውን ያስጠቃሉ። እርሳቸው ዶክተር አብይ ጉያ ሥር ተሸሽገው ያሉት መሠሪዎች ኢትዮጵያን መንግሥት አልባ አደረጋት።
ቁጥር ሥፍር የሌላቸው የኦሮሞ ምሁራን በብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ ስለሚረኩ ህወሃትን እንደ ባለውለታ አማራን እንደ ጠላት ይመለከታሉ። የኦሮሞ ፖለቲከኞች "አሃዳዊ" በሚለው ቅርጽ እየባነኑ ነው። የብሄር ብሄረሰብ ቀለም ቀብታ ክልልነትን ከአንቀጽ 39 ጋር "እንኩ" ያለችው ህወሃት ከመቶ ዓመት በላይ ለመግዛት፣ ከፍተኛ ኃብት እውጭ ለማስቀመት፣ ጥሬ ሃብት ወደ ትግራይ ለማሸሽ፣ ወዘተ፣ ነበር እንጂ ፌደራሊዝም ተስማምቷት አልነበረም። ህወሃት ከንጉሥ ኃይለሥላሴም ይልቅ ጨቋኝ አሃዳዊ ነበረች። ይህ መሰሉን ህወሃት የተጠቀመችበትን የተበላ እቁብ ፖለቲካ እንደገና አድሶ ሌላ ምዝበራና ስርቆት እፈጽማለሁ የሚለው ተረኛ፣ ይህ ተላላ ፖለቲከኛ – ለሕዝብ ተቆርቋሪ መንግሥት የሆነ መንግሥት እንዳይኖር በማድረግ አማራን አስፈጀ። ብልጽግና ውስጥ ያሉት ተጻራሪዎች የጀርባ ላይ እባጭ የሆኑባቸው ዶክተር አብይ እነሱን ለማርገብ የተጠቀሙት ሌላናው ዘዴ ኦሮሙማን ማጠናከር ሆነ። እነሆ በመሬት ዝርፊያና ሥልጣንን በማጠናከር ላይ ብቻ የሚያተኩረው የኦሮሙማ ፖሊሲ ኢትዮጵያን ክብሯን ለማስጠበቅም ሆና አማራን ከዘር ጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም የለውም።
ዶክተር አብይ ህግና ሥርዓት ማስከበረ ካልቻሉባቸው አካባቢዎች አንዱ የደቡብ ኢትዮጵያ ምድር ነው። "ክልል ልሁን" ያለው የሲዳማ መሬት ክልል እስኪሆን ድረስ በዘር ዱላው አርባ ተገርፏል። አሁንም "ክልል ካሎሆንን ሞተን እንገኛለን"የሚሉት የደቡብ መሬቶች እራሳቸው ዶክተር አብይ በላኩት በአባ ዱላ በትር ሳይገረፉ እንዲሁ ክልል አይሆኑም። የዘር ፖለቲካው የወለደው ክልል የተባለው እንግዴ ልጅ – መልክዓ-ምድራዊም ሆነ አስተዳደራዊም ቅርጽ የማይበጅለት የደመ ነፍሱ ህወሃት የጋኔን ምች ነው። ክልል - የዘር ፖለቲካው መሪ - የተራራው ጀርባ ዓጽመ ርስት ነው። አንዱ የነቃ ጮሌ "ክልል እንሁን" ብሎ ያሳምጻል፣ ብዙዎች ሞተው፣ ተገርፈው መሬቱ ክልል ሲሆን፣ ጮሌው ከዱላ የተረፉትን ወገኖቹን በፍርሃት ቆፈን አስሮ ይግጣቸዋል። የዘር ፖለቲካ ትወና የተካነች፣ ውሸታሞች የሚያበለጽጓት፣ እርጉም ባህል መሆኗ ፍንትው ብሎ የታየው አዋሳ ከተማ ውስጥ አብሮ የኖረው ወንድማማቹ የወላይታና ሲዳማ ሕዝብ አንገት ላንገት ተያይዞ ሲቀነጣጠስ ነው።
የዘር ፖለቲካ እረፍት የላትም። በጉራ ፈርዳ፣ ቤንች ማጂ ምድር የሚንቀለቀለው የዘር ፖለቲካ ደራሽ የሌለውን አማራ ወገኔን ቁም ስቅሉን አብልታለች። ቤንሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ ምድርን በቀርክሃ ዱላ ስትገርፍ የቆየችው የዘር ፖለቲካ ዞር ብላ ደግሞ ፍርጃ ያልተለየውን አማራን በሾለ ቀስት ቀሰፈችው። ግፍ ክፉ ነች፣ ነገ ተመልሳ የቤንሻንጉል ጉሙዝ የዘር ግድያ መሃንዲሶች ላይ መከራ ታዘንባለች።
ለኢጣልያ ያደሩ ባንዶች የወለዷቸው ልጆች ያፏፉት የዘር ፖለቲካ ቀማኖችን እንጂ ብቁ አስተዳዳሪዎችን አላበቀለም። የዘር ፖለቲካ ለተላላኪው ጫት መቃምያ፣ ለአስመሳዩ ጮማ መቁረጭያ፣ ለጮሌው ንዋይ መሰብሰብያና የምዕራብ ሃገሩ መኖርያ ፈቃድ ማግኛ ነች። ሰው ሳይደክም ላገኘው ገንዘብ አይሳሳም። ሕወሃት ነፍሷን አይማረውና ብልግናን አስፋታ ነው ወደ መቃብር የወረደችው። ዛሬም አንድ ባለሥልጣን ራስ ምታት ቢይዘው አስፕሪን ለመዋጥ አውሮፓና አሜሪካ ለመሄድ ይዳዳል። እንግዲህ አስቡት፣ ደሃው በዋጋ ግሽበት እያለቀሰ፣ ወጣቱ ሥራ ፍለጋ እየደከመ ይህ ሁሉ የውጭ ምንዛሬ ሲባክን ሜድያው እንደዘበት "እገሌ ሊታከሙ አሜሪካ ገቡ"ብሎ ያወራል።
ባለሥልጣናቱ በሶስት ምክንያቶች ወደ ውጭ እየሄዱ የውጭ ምንዛሬ ያባክናሉ፣ አራተኛው ደግሞ ጉደኛ ነው። አንደኛው ምክንያት መዝናናት ነው። "የደላው ሙቅ ያኝካል" እንዲሉ ለመዝናናት ውጭ ይሄዳሉ። በንጉሡና በደርግ ዘመን ሶደሬ ወይንም ላንጋኖ መሄድ እንደማለት ነው። ሁለተኛው ምክንያት ስጋት ነው። ልዩነት ሲከሰት ስጋት የሚያድርበት ባለሥልጣን በህክምና አስታኮ ዞር ብሎ ሁኔታውን የሚከታተለው እምዕራቡ ሃገር ባለው ዩ ትዩብና ፌስ ቡክ ነው። ሶስተኛው ምክንያት ጸጸትና ፍርሃት ናቸው። ዘረኞች የግፍ ሥራቸው ሁልጊዜ ያባንናቸዋል። እነዚህ ባለሥልጣናት ኦዲት ከማይደረገው የሃገሪቱ ኃብትና የመሬት ወረራ ድርሻቸውን ሞጭልፈው ቤተሰቦቻቸውን አስቀድመው ልከዋል። ኮሽ ሲል በስብሰባ ስም ዶላር አፍሰው እግሬ አውጭኝ ይላሉ። ችግሩ ከተባባሰ እዛው ይቀራሉ። አራተኛው የጉድ ነው። ለፍርድ መቅረብ የሚገባቸው ወንጀለኞች በሞቀ ሽኝት አምባሳደር ተደርገው ይላካሉ። ወገኖቼ እንግዲህ ፍረዱ! በንጉሡና በደርግ ዘመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጥራትንና የአምባሳደር አሿሿም መስፈርትን አጢኑ። እንደው ለመሆኑ - አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ "Compare and contrast Intellectual and Moral integrity during the reign of Emperor Hailesselasie with that of both EPRDF 1 and EPRDF 2» ብሎ ቢጽፍ አርዕስቱ ብቻ A+አያሰጠውም።
መጣጥፉን እንዲህ ብሎ ቢጀምርስ፣ "ሃገሬ ኢትዮጵያ የጉድ ሃገር ከሆነች ሠነበተች። በዓለም ባንክ ብድር የሚሰሩት ፋብሪካና ኢንዱስትሪዎች ከሁለት አቅጣጫ ሲቦተለኩላቸው ቆይተዋል። አንዱ ከአበዳሪዎቹ ሲሆን ሌላው ከተበዳሪው የሃገራችን መንግሥት ነው። ፕሮፕጋንዳዎቹ ግን አቅጣጫ ማስቀየሻ እንጂ የሃገር ኃብት ሲሆኑ አልያታየም። አበዳሪ ሃገራትና ሙሰኛ መሪዎች በምክክር ስለ "ድርብ አሃዝ እድገት" ሰምና ወርቅ ሲቋጥሩ የሸቀጦች ዋጋ ይንራል፣ ሥራ አጥነት ይስፋፋል፣ ድህነት ይባባሳል። ባለሥልጣናት በዘረፉት ገንዘብ እውጭ ላስቀመጧቸው ልጆቻቸው ወጪ ሲሸፍኑ ብድሩ ተመልሶ አበዳሪው እጅ ይገባል፣ እዳውን ኢትዮጵያ ትከፍላለች። ብድርና ዘረኝነት ተጣምረው ለኢትዮጵያ ሃገሬ የቆላ ቁስል ከሆኑ ሶስት አስርት ዓመታት ሆናቸው። ይህ የቆላ ቁስል እንዲሽር ደጋጎች የወጠኑት ኦሮ-ማራ በኦሮሙማ ክፉ ሃሳብ ተዋጠ። ኦሮሙማ የዘረኝነቱ ፖለቲካ ክፍል ሁለት ነች"።
ክፉ ለራሱ ደግ ለራሱ ነው። ግፍ ውላ አድራ አርሞ ኮትኩቶ ያሳደጋትን እንደምትበላ በገሃድ የታየው አቶ ስብሃት፣ ባለቤታቸውና እህታቸው ወታደሮቹ ከገደል ተሸክመው ሲያወጣቸው ነው። የዘር ፖለቲካ ልጆቿን ተራ በተራ ቅርጥፍ አድርጋ በልታቸዋለች። የዘር ፖለቲካ - ተመራማሪ፣ አንባቢ የተባለውን መለስ ዜናዊና ቡራኬ ሰጭዋን ጳጳስ ሳይቀር በሾሉ ጥርሶቿ አኝካ ውጣ የተረፉትን አንገላታና አባዝና ጊዜው ሲደርስ እስከነ ጓንታቸው ሠለቀጠቻቸው። እንደ ጎርፍ በፈሰሰው ደም የተገዛ ምድራዊ ቅንጦትና ሃገር ማቅ አልብሶ እውጭ ገንዘብ ማሸሽ መጨረሻው ዛሬ ያየነው ነው። ሕወሃቶች ተዋርደው እንዲህ መቀመቅ ሲወርድ እያዩ አሁንም ዘረፋና መሬት ወረራ የሚያስቡ ኦሮሙማዎች በእውነት ቂሎች ናቸው ። ትልቁ ባለሥልጣን፣ የቀድሞው የትግራይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ ለማኝ ሆነው ራሳቸውን ክደው - ሃሰን እብራሂም ነኝ እያሉ ሲዋሹ - የዘር ፖለቲካ በእርግጥም ላሳዳጊዋም እንደማትሳሳ ፍንትው ብሎ ያሳያል። ወገኖቼ ይህን ሁሉ እያየን ዓለም ከንቱ መሆኗን ካልተረዳን አሁንም ሞኞች ነን። ስብሃት ነጋ "እኔን ያየህ ተቀጣ" እያሉ ሳለ - ዛሬም በዘረፋና በቅሚያ ለማደግ መጓጓቱስ የት ያደርሳል?ወገኖቼ አሁንስ ይመራል። ሥልጣንና የመሬት ወረራ የአንድ ስንቲም ሁለት ግልባጭ በሆኑባት ኢትዮጵያ እንደምን አድርጎ ፍትህ ማስፈን፣ አማራውን ማዳን እንደሚቻል ማሰቡ እጅግ ይከብዳል። ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ወራ እስከምትይዝ፣ እንዲህም ተዋርደን አናውቅም። በእርግጥ ኢትዮጵያ ምንም አትሆን፣ ግን እስከመቼ እንዲህ በስቃይ! አምላኬ?
ፈጣሪ እባክህ አማራውን ታደገው፣ ኢትዮጵያን ስቃዩን አንሳላት! አሜን።
Tuesday, February 2, 2021
#Abiy stop killing Amhara
የአማራው ለብቻው መደራጀት ኢትዮጵያዊነትን ያዳክማል?
አንድ ወቅት ላይ አፍቃሪ ወያኔ የሆነው የኢትዮጵያ ፊርስት ድረገጽ አዘጋጅ ቤን የተባለው ጋዜጠኛ አቶ መለስንና አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ቃለመጠይቅ አቅርቦላቸው ነበር። አቶ መለስን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው።(ቃለ መጠይቁን ስለረሳሁት ሃሳቡን እንጂ ቃል በቃል ላስቀምጠው አልችልም)። "እንደው ኦሮም ኦሮሞ ሲባል ይለጠጥና ኢትዮጵያዊነትን አያዳክምም?" እርሳቸው ሲመልሱም "አያዳክምም - ኦሮሞው በኦሮሞነቱ ማንነቱ ሲከበርለትና እውቅና ሲሰጠው እንደውም ኢትዮጵያዊነት ያጠናክራል" አሉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ጠየቃቸው። "እንደው ይህ በዘር በዘሩ መደራጀት ኢትዮጵያዊነትን አያላላም፣ አያፈርስም?" እሳቸውም እንደ አለቃቸው ሲመልሱ "አያዳክምም - ለምሳሌ እኔ ሲዳማ ነኝ፣ ሲዳማነቴ ሲታወቅልኝና ማንነቴ ሲከበርልኝ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ። ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት ይጠናከራል"። ሁለቱም መልሳቸው ላይ ማንነት (identity) የምትለዋን ጽንሰ ሃሳብ አንስተዋል። ማንነታቸውን ያወላገደባቸው አማራ ነው ወይንም ሁሉንም ገዥዎች አማሮች ናቸው ለማለት ነው። ይህ የተሳሰተ ፍልስፍና፣ ወደ ስልጣን ላይ ለመውጣት የተፈበረከ፣ ይህ እኩይ ፍልስፍና ነው አማራውን ያስጠቃው። ወያኔና ሻዕቢያ የሁሉም ዘር ጠላት አማራ ነው ሲሉ ለልጆቻቸው እያስተማሩ በምስኪኑ አማራ ላይ የግፍ ጣታቸውን ቀሰሩበት። አማራው የተሳለቀበትና ማንም እየተነሳ የሚያንቋሽሸው በዚህ ፍልስፍና፣ እዛው ደደቢት ውስጥ በተቀመረው የተሳሳተ ርኩስ ንድፈሃሳብ ነው።
Tuesday, January 19, 2021
#Stop Killing Amhara
በአምሃራው ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅትና (Amhara Genocide)
የኅልውና ትግሉ
ፍጡር ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የተፈጸመ ታላቅ ፍዳን፣ መከራን፣ ግድያንና ጭፍጨፋን ስናጠና በናዚ ጀርመን ወቅት የነበሩ እስራኤሎች ላይ የተደረገው የዘር ፍጅት (Holocaust)፣ የቦስንያ ጭፍጨፋ(Bosnia Genocide)፣ እንዲሁም የአርመኖች ጭፍጨፋ (Armenian Genocide) ከፊታችን ድቅን ይላል። በአፍሪካም የሩዋንዳው እልቂት (Rwandan Genocide) ከነዚሁ ጋር አብሮ የሚደመር ዘግናኝ ታሪክ ነው። ናዚ እስራኤሎችን ለማጥፋት አስቀድሞ ከፍተኛ መረጃን ሲሰበስብ ቆይቷል። ምንም እንኳን ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ልቅ ቅርርብ የማያደርጉ ቢሆንም - እስራኤሎች ምን እንደሚበሉ፣ ምን እያሉ እንደሚጸልዩ፣ ኃይማኖታዊ ምሥጢሮቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን ምን ዓይነት ግኑኝነት እንደሚያደርጉ እነሱን መስለው በተጠጓቸው ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦችና ረዳት መስለው በቀረቧቸው ግለሰቦችይመረጅ ነበር። እስራኤሎች ትውፊቶቻቸው፣ ምሳሌአዊ አነጋገሮቻቸው፣ ባጠቃላይ ሁለንተንዊ እንቅስቃሴዎቻቸውና ፈሊጦቻቸው ሳይቀር በናዚዎች እየተመዘገበ ምርመራና ጥናት ይደረግበት ነበር። እነሆ ታድያ ናዚዎች "ይግደራደሩናል፣ ዓላማችንን ያሰናክላሉ፣ በጸሎት ኃይል እርምጃዎቻችንን ይገታሉ" የሚሏቸውን እስራኤሎች አስቀድመው ካላጠፉ በቀር እርካታና ሠላም ማግኘት አልቻሉም። እስራኤሎች በእነሱ ላይ ከተፈጸመው ተሞክሮ ተነስተው ነው ዛሬ በመረጃና ጸረ-መረጃ ሙያ የላቀ ሥፍራን የተጎናጸፉት። ከላይ የጠቀስኳቸው ዓይነት የዘር ማጥፋት ሠለባ በመሆን ላይ ከሚገኙት መካከል አንዱ ነገድ በኢትዮጵያ ምድር የሚገኘው አማራ ነው።
አማራ በሰሜንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ደጋው ላይ የሠፈረ ነገድ ነው። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ መሠረት የአማራ ሕዝብ ወደ 29 867 817 ይጠጋል ይላል ዊኪፔድያ ላይ የተጻፈ ማስረጃ። ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህል32,5% ይሆናል ማለት ነው። የአማራው ነገድ ቋንቋ የሆነው አማርኛ በጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ (ቤተ አምሃራ) እንዲሆም ሰሜን ሸዋ ውስጥ ይነገራል። የአማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሁም በየዘመናቱ ለሚነሱት ገዥዎች የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ነው። ባለ ለም መሬቱ አማራ ደሃ ነው። መሥራት አቅቶት አይደለም - በየዘመናቱ የሚነሱት የኢትዮጵያ ጠላቶችን ስለሚዋጋ እንጂ። አማራዎች ናቸው ተብለው የተፈረጁት ያለፉት ዘመን ገዥዎች ለክልሉ አንዳች አላደረጉለትም። አማራ ደሃም ቢሆን ድህነቱ ግን እምነቱንና ጀግንነቱን አይፈታተንበትም። አማራው እግዚአብሄርን በጽኑ ያምናል። አማራው እግዚአብሄርን ቀርቶ ካህናቱን ቀሳውስቱንና ገዥዎቹን ሳይቀር ያከብራል። "እንዳልኮራ ደሃ ነኝ፤ እንዳልፈራ ጎንደሬ" ነኝ ተብሎ የተጻፈው አንድ መፈክር የአማራውን ምንነት አጉልቶ ያሳያል። አማራ ትዕግስተኛ ነው። አማራ አማኝ ነው። አማራ የልቡን አይደብቅም። አምሃራ ቆራጥም ነው። አማራ - አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራውንና ሃገሩ ኢትዮጵያን እንደ ዓይኑ ብሌን ይጠብቃል። ታድያ ምን በደል ኖሮበት ነው አምሃራው እንዲያልቅ የተፈረደበት?
ከመቸውም ጊዜ በላይ ዛሬ በየአማሮች ቤት ዘራቸው እንዲጠፋ በተፈለገበት ምክንያት ላይ የሃሳብ ልውውጥ ይደረጋል። አንዳንዶች "አማራ ጥንት በብሉይ ዘመን ከእስራኤሎች ጋር በነበረው ግኑኝነት ምክንያትይሆን በአረቦቹ የተጠላው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ሌሎች ደግሞ "በቅኝ ግዛቱ ወረራ ወቅት ቆራጥ ተጋድሎ ያደረጉት አማሮች ብቻ ናቸው ተብሎ ተወርቶብን ይሆን ፈረንጆቹ የጠሉን” ሲሉ ሌላ ጥያቄ ይሠነዝራሉ።"እኛ አማራ ነኝ ከማለት ይልቅ - ኢትዮጵያዊ ነን - በማለታቸው ነው ጥርስ የተነከሰብን” እያሉ በሃዘን የሚናገሩም አይጥፉም። በዛ ያሉ አማሮች "ገዥዎች የአማርኛ ቋንቋ ስለሚናገሩ የፖለቲካው ጭቆና የተደረገውበመላው አማራው ትብብር ነው በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል እንድናልቅ የተፈረደብን” ሲሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ። ሁሉም የመሰለውን እንደምክንያት ያቀርባል፤ ትክክለኛውን ለማወቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ፣ ህግ ወይም የታሪክ ተመራማሪዎች ወደፊት ጥናት ያደርጉበት ይሆናል። ወያኔና ሻዕቢያ አማራው ነገድ ለምን እንዲጠፋ ፈለጉ - የሚለውን ስንቃኝ - በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ በአማራ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት በደሎች ድቅን ይሉብናል። አቶ ስብሃት "አማራና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አከርካሬቸው ተሰብሯል፣ ከዚህ በኋላ አያንሰራሩም" ሲል በትዕቢት የተናገረው አረፍተ ነገር ወያኔ አማራውን ለማጥፋት ያቀነባበረው ምስጢራዊ ተልዕኮ በከፊልም ቢሆን መስመር መያዙን ይጠቁማል። ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ አማራውን ከእልቂት ለማዳን ገና በጠዋቱ ያቋቋሙት "መላ አማራ ሕዝቦች ድርጅት" (መአሕድ) በወቅቱ ብዙዎች አማሮች ኢትዮጵያዊነትን ያዳክማል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተው ነበር። ዛሬ ከብዙ ጥፋት በኋላ ግን ከአቶ ስብሃት አፍ ያፈተለከው አነጋገር በርካታ አማሮችን ከአሸለቡበት አንቅቷል። ያለፈው አልፏል ከአሁን ወድያ ግን አማራው በቅጡ ተደራጅቶ ወደ ፕሮፌሰር አስራት ምክር በመመለስ በወያኔ የሚተገብረውን አማራውን የማጥፋት ዕቅድ በህብረት ማምከንይኖርብናል::
Thursday, January 14, 2021
Stop 🛑
ጨፍጫፊው ቡድን በመተከል ባሉ አማሮች ላይ የሚያደርሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ መንግስት ማስቆም ያልፈለገው ለምንድነው?
#stop killing Amhara people
Wednesday, January 6, 2021
Saturday, January 2, 2021
የተረኝነት ፓለቲካ
ዶክተር አብይ ኦህዲድን ለሁለተኛ ጊዜ ጠፍጥፈው ጠርበው ስሙን ኦዴፓ ብልጽግና አሉት። አዲሱ ኦዴፓ (ODP) ጠፍጣፊ ሆኖ ኢሕዴን-ብአዲንን እንደገና ጠፍጥፎ አዴፓ (ADP) ብልጽግና አለው። ኦህዴድ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ተጠፍጥፎ የተሠራው “አማራውን ወክያለሁ” እያለ የሚቃዠው የቀድሞው ኢሕዴን ሶስተኛ ጊዜው ነው ተጠፍጥፎ ሲሰራ። ኢሕዴን - አዴፓ ብልጽግና እስኪባል ድረስ ብዙ ጊዜ ተጠርቧል። “አማራው ጀግና ነው ጥፍጥፎች አይመሩትም” ያለው ጄኔራል በሴራ ከተወገደ በኋላ በታማኝናት የሚያገለግለው አዴፓ ዛሬ የኦዴፓ ካባ አልባሽ ሆኗል። ኦዴፓ ብልጽግና ባለጊዜና ተረኛ ሆነ።