Sunday, February 15, 2015

ወያኔ ማንነቱን ሕዝቡ ጠንቅቆ ከማወቁና በሚፈጽማቸው በደሎችና ግፎች ከመንገሽገሹ የተነሣ በተፈጠረበት እጅግ በጣም ከባድ በራስ ያለመተማመን ችግር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለተቃዋሚ ወይም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዛ ሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች በተጻራሪ ነጻነታቸውንና መብቶቻቸውን እየከለከለ በራሱ ፍላጎት ብቻ በጠባቡ ከልሎ የሚሰጣቸውን የመጫዎቻ ሜዳም እንኳን ሊሰጥ በፍጹም አልፈለገም፡፡ እንደወያኔ አስተሳሰብ ይሄ ስልቱ ጊዜው አልፎበታል ፡፡ ቢያደርገው “ልቆጣጠረው በማልችለውና ባልጠበኩት አቅጣጫ ሄዶ ያስበላኛል” ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም ብቻውን ሮጦ አሸነፍኩ ብሎ በማስጨብጨብ አሁንም መንግሥት ነኝ ሊል ፈልጓል፡፡

No comments:

Post a Comment