በአምሃራው ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅትና (Amhara Genocide)
የኅልውና ትግሉ
ፍጡር ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የተፈጸመ ታላቅ ፍዳን፣ መከራን፣ ግድያንና ጭፍጨፋን ስናጠና በናዚ ጀርመን ወቅት የነበሩ እስራኤሎች ላይ የተደረገው የዘር ፍጅት (Holocaust)፣ የቦስንያ ጭፍጨፋ(Bosnia Genocide)፣ እንዲሁም የአርመኖች ጭፍጨፋ (Armenian Genocide) ከፊታችን ድቅን ይላል። በአፍሪካም የሩዋንዳው እልቂት (Rwandan Genocide) ከነዚሁ ጋር አብሮ የሚደመር ዘግናኝ ታሪክ ነው። ናዚ እስራኤሎችን ለማጥፋት አስቀድሞ ከፍተኛ መረጃን ሲሰበስብ ቆይቷል። ምንም እንኳን ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ልቅ ቅርርብ የማያደርጉ ቢሆንም - እስራኤሎች ምን እንደሚበሉ፣ ምን እያሉ እንደሚጸልዩ፣ ኃይማኖታዊ ምሥጢሮቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንኳን ምን ዓይነት ግኑኝነት እንደሚያደርጉ እነሱን መስለው በተጠጓቸው ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦችና ረዳት መስለው በቀረቧቸው ግለሰቦችይመረጅ ነበር። እስራኤሎች ትውፊቶቻቸው፣ ምሳሌአዊ አነጋገሮቻቸው፣ ባጠቃላይ ሁለንተንዊ እንቅስቃሴዎቻቸውና ፈሊጦቻቸው ሳይቀር በናዚዎች እየተመዘገበ ምርመራና ጥናት ይደረግበት ነበር። እነሆ ታድያ ናዚዎች "ይግደራደሩናል፣ ዓላማችንን ያሰናክላሉ፣ በጸሎት ኃይል እርምጃዎቻችንን ይገታሉ" የሚሏቸውን እስራኤሎች አስቀድመው ካላጠፉ በቀር እርካታና ሠላም ማግኘት አልቻሉም። እስራኤሎች በእነሱ ላይ ከተፈጸመው ተሞክሮ ተነስተው ነው ዛሬ በመረጃና ጸረ-መረጃ ሙያ የላቀ ሥፍራን የተጎናጸፉት። ከላይ የጠቀስኳቸው ዓይነት የዘር ማጥፋት ሠለባ በመሆን ላይ ከሚገኙት መካከል አንዱ ነገድ በኢትዮጵያ ምድር የሚገኘው አማራ ነው።
አማራ በሰሜንና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ደጋው ላይ የሠፈረ ነገድ ነው። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2007 በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ መሠረት የአማራ ሕዝብ ወደ 29 867 817 ይጠጋል ይላል ዊኪፔድያ ላይ የተጻፈ ማስረጃ። ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህል32,5% ይሆናል ማለት ነው። የአማራው ነገድ ቋንቋ የሆነው አማርኛ በጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ (ቤተ አምሃራ) እንዲሆም ሰሜን ሸዋ ውስጥ ይነገራል። የአማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሁም በየዘመናቱ ለሚነሱት ገዥዎች የመንግሥት የሥራ ቋንቋ ነው። ባለ ለም መሬቱ አማራ ደሃ ነው። መሥራት አቅቶት አይደለም - በየዘመናቱ የሚነሱት የኢትዮጵያ ጠላቶችን ስለሚዋጋ እንጂ። አማራዎች ናቸው ተብለው የተፈረጁት ያለፉት ዘመን ገዥዎች ለክልሉ አንዳች አላደረጉለትም። አማራ ደሃም ቢሆን ድህነቱ ግን እምነቱንና ጀግንነቱን አይፈታተንበትም። አማራው እግዚአብሄርን በጽኑ ያምናል። አማራው እግዚአብሄርን ቀርቶ ካህናቱን ቀሳውስቱንና ገዥዎቹን ሳይቀር ያከብራል። "እንዳልኮራ ደሃ ነኝ፤ እንዳልፈራ ጎንደሬ" ነኝ ተብሎ የተጻፈው አንድ መፈክር የአማራውን ምንነት አጉልቶ ያሳያል። አማራ ትዕግስተኛ ነው። አማራ አማኝ ነው። አማራ የልቡን አይደብቅም። አምሃራ ቆራጥም ነው። አማራ - አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራውንና ሃገሩ ኢትዮጵያን እንደ ዓይኑ ብሌን ይጠብቃል። ታድያ ምን በደል ኖሮበት ነው አምሃራው እንዲያልቅ የተፈረደበት?
ከመቸውም ጊዜ በላይ ዛሬ በየአማሮች ቤት ዘራቸው እንዲጠፋ በተፈለገበት ምክንያት ላይ የሃሳብ ልውውጥ ይደረጋል። አንዳንዶች "አማራ ጥንት በብሉይ ዘመን ከእስራኤሎች ጋር በነበረው ግኑኝነት ምክንያትይሆን በአረቦቹ የተጠላው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ሌሎች ደግሞ "በቅኝ ግዛቱ ወረራ ወቅት ቆራጥ ተጋድሎ ያደረጉት አማሮች ብቻ ናቸው ተብሎ ተወርቶብን ይሆን ፈረንጆቹ የጠሉን” ሲሉ ሌላ ጥያቄ ይሠነዝራሉ።"እኛ አማራ ነኝ ከማለት ይልቅ - ኢትዮጵያዊ ነን - በማለታቸው ነው ጥርስ የተነከሰብን” እያሉ በሃዘን የሚናገሩም አይጥፉም። በዛ ያሉ አማሮች "ገዥዎች የአማርኛ ቋንቋ ስለሚናገሩ የፖለቲካው ጭቆና የተደረገውበመላው አማራው ትብብር ነው በሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል እንድናልቅ የተፈረደብን” ሲሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ። ሁሉም የመሰለውን እንደምክንያት ያቀርባል፤ ትክክለኛውን ለማወቅ ግን በዚህ ጉዳይ ላይ የፖለቲካ፣ ህግ ወይም የታሪክ ተመራማሪዎች ወደፊት ጥናት ያደርጉበት ይሆናል። ወያኔና ሻዕቢያ አማራው ነገድ ለምን እንዲጠፋ ፈለጉ - የሚለውን ስንቃኝ - በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ በአማራ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ የዘር ማጥፋት በደሎች ድቅን ይሉብናል። አቶ ስብሃት "አማራና ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አከርካሬቸው ተሰብሯል፣ ከዚህ በኋላ አያንሰራሩም" ሲል በትዕቢት የተናገረው አረፍተ ነገር ወያኔ አማራውን ለማጥፋት ያቀነባበረው ምስጢራዊ ተልዕኮ በከፊልም ቢሆን መስመር መያዙን ይጠቁማል። ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ አማራውን ከእልቂት ለማዳን ገና በጠዋቱ ያቋቋሙት "መላ አማራ ሕዝቦች ድርጅት" (መአሕድ) በወቅቱ ብዙዎች አማሮች ኢትዮጵያዊነትን ያዳክማል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተው ነበር። ዛሬ ከብዙ ጥፋት በኋላ ግን ከአቶ ስብሃት አፍ ያፈተለከው አነጋገር በርካታ አማሮችን ከአሸለቡበት አንቅቷል። ያለፈው አልፏል ከአሁን ወድያ ግን አማራው በቅጡ ተደራጅቶ ወደ ፕሮፌሰር አስራት ምክር በመመለስ በወያኔ የሚተገብረውን አማራውን የማጥፋት ዕቅድ በህብረት ማምከንይኖርብናል::