በዛሬው ኢሳት ሬዲዮ ስርጭት
_ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በውስጥ ሽኩቻ ተጠምዷል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው አስቀድሞ የተጀመረው የእርስ በእርስ ፍጥጫ እየከረረ መጥቷል። በአቶ መለስ የተወገዱት የቀድሞ የህወሀት አመራሮች እንዲመለሱና ህወሀትን እንዲያጠናክሩ የቀረበው ሀሳብ የፍጥጫው አንዱ ምክንያት ነው ተብሏል።
_የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስርዓቱን እየከዱ ወጥተው በሚቀሩ ዲፕሎማቶች ምትክና በሌሎች ቦታዎች የ71 ዲፕሎማቶች ምደባ ሊያደርግ መሆኑ ተገለጸ። ትላንት ኢሳት እንደዘገበው 6 ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ከድተዋል። ከጥቂት ወራት በፊትም ከሎሳንጀለስ ቆንስላ ጽ/ቤት ወ/ሮ የሀረር ወርቅ በቀለ የተባሉ ዲፕሎማት የስራ ጊዜያቸው ቢጠናቀቅም እዚሁ ቀርተዋል። በደቡብ ኮሪያ ሴዑል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ዲባባ አብደታ ወደ አዲስ አበባ መጠራታቸውም ታውቋል። ምክንያቱ አልተገለጸም።
_ድምጻችን ይሰማ የትላንቱን የፍርድ ቤት ውሳኔ ድራማ ሲል አጣጣለው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ለተጠናከረ ትግል እንዲዘጋጁ ጥሪ አድርጓል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በተመለከተ ባወጣው መግለጪያ በደሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊ በደል ነው ብሏል። እጅ ለእጅ ተያይዘን ህወሀትን እናስወግድም ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አስተላልፏል።
_በሸዋና በወሎ ድርቅ ገብቷል። ዝናብ የለም። ባለስልጣናት በፓርቲ ስብሰባ ተጠምደዋል። በሰሜን ሸዋ በዋግ ህምራና በወሎ በርካታ አከባቢዎች ድርቅ ተከስቷል። በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከዝናብ አለመከሰት ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ አደጋ እንዳንዣበበ መረጃዎች ያመለክታሉ። በአንጻሩ የህወሀት የልማት ዲስኩር ተጠናክሮ ቀጥሏል።http://ethsat.com/?p=33903