Saturday, July 25, 2020

የዘር ፍጅት (Genocide)! - አቤቱ ጌታዬ ከመዓቱ ሰውረን - ከሚክያስ

ሕወሃት አዲስ አበባ ከከተመበት ቀን ጀምሮ የታወጀው አማራውን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዶክትሪን ዶክተር አብይ ሥልጣን ላይ ሆነውም አልተገታም። ዛሬ ላይ ገሃድ የሆነው የዘር ፍጅትና አስቃቂ ግድያዎች የሕወሃት የዘር ፍጅት ምዕራፍ ቅጥያ ነው። የዛሬ ሠላሳ ዓመት ገደማ ጠባቂና ተከላካይ የሌለው ምስኪኑ አማራ በወያኔው ሹም ትዕዛዝ አርባጉጉና በደኖ ላይ ከገደል ተወርውሯል። ኦርቶዶክሱና አማራው ላይ ያነጣጠረው ይህ ዘርን የማጽዳት አረመናዊ ጭፍጨፋ ከቡራዩ እስከ አዲስ አበባ፣ ከአርሲ እስከ አዳማ፣ ከባሌ እስከ ሐረርጌ፣ ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ፣ ወዘተ፣ ተካሂዷል። አማራውና ኦርቶዶክስ ክርስትያኑ ላይ የደረሰው የዘር ፍጅት ናዚ ጀርመን እስራኤሎች ላይ ካደረገው እልቂት በዓይነት ይለያል።፣

አማራ ይህ ዓይነቱ ዘግኛኝ ግፍ የሚፈራረቅበት ሌሎች ያጡት ነገር ግን እርሱ ብቻ የጨበጠው ጥቅም ኖሮ አይደለም። አማራ እንደ ሌሎች ወገኖቹ ደሃ ነው። ታድያ ምን አጠፋ -እግዚአብሄርን ማምለኩ፣ ሃገርን፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዲራውን መውደዱ ነው ወንጀሉእንደው ለነገሩ አማራው ብቻ ነው ኢትዮጵያን የሚወደው?ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ ወላይታው፣ ሲዳማው፣ ጋሞው፣ ቤንሻንጉሉ፣ ጉራጌው፣ ወዘተ፣ ሁሉም ኢትዮጵያን ይውዳል። ለምን ይሆን ታድያ አማራው ለእልቂት የተመረጠውን የተለየ በደል ሰርቶ ነው ሕወሃትና ኦነግ አማራው ሠለባ እንዲሆን የፈረዱትቅኝ ገዥዎች የተሸነፉት በመላው ኢትዮጵያዊ ትብብር ነው። አማራው ብቻውን አድዋ አልዘመተም። ግን ለምን ይሆን አማራው ላይ ብቻ እልቂት፣ ግድያ፣ እገታ፣ ማምከን፣ ንብረት ማቃጠል፣ ወዘተ፣ የተፈረደውበእርግጥ አማራው ላይ እልቂት እንዲፈጸም ሠይጣናዊ ሃሳቡን ያረቀቀው ወያኔ "ዘር ከዘር አፋጅቴ ኢትዮጵያን ለሺህ ዓመት በማን አለብኝነት እገዛለሁከሚል አላዋቂነት የተነሳ ነው። ወያኔ ይህን ድንቁርና የወረሰው ከቅኝ ገዥዎች ነው። ይህን አላዋቂነት ጽንፈኞችና አማራ-ጠል ምሁራን ተጋሩት። ይህን አላዋቂነት ሃገር እንድትፈርስ የሚፈልጉ ሁሉ ከአድማስ አድማስ አናፈሱት። በዘር እልቂት ሽፋን ሚኒልክ ቤተ መንግሥት መግባት የሚፈልጉ ሁሉ ዘረኝነትን በወጣቶች ዓዕምሮ ውስጥ እንዲያድር ብዙ ደከሙ።

ሃገር ጠሎች አማርኛን፣ የቅኝ ግዛት ሽንፈት ምልክት የሆነውን የሚኒልክን ሃውልት እንደጦር ይፈራሉ። አማርኛ እኮ የአማራ ብቻ ቋንቋ አይደለም። የሚኒልክ ሃውልት እኮ የኢትዮጵያ ብቻ መኩርያ አይደለም። መላው አፍሪካና በቅኝ ግዛት የማቀቁ ሃገሮች ሁሉ የሚኒልክ ሃውልትን ይወዳሉ። በብዙዎች የአፍሪካ ሃገራት እኮ በሚኒልክ ስም አደባባይ፣ መንገድ፣ አዳራሽ፣ ትምህርት ቤት፣ ወዘተ፣ ተሰይሟል። "የሚኒልክ ሃውልት ይፍረስየሚለውን የቅኝ ግዛት ሃሳብ በሞኝ ምሁራን ዓዕምሮ ውስጥ አስቀምጠው ሲዘርፉ የነበሩ ወያኔዎች የማታ ማታ የት ደረሱዛሬ በሕይወት ያሉት ወያኔዎች ወደ ቀልባቸው ተመልሰው በወገናቸው አምሃራው ላይ የደረሰው እልቂት ይከነክናቸው ይሆንእግዚአብሄር ይወቀው። አቶ ስብሃት "አማራና ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን አከርካሬአቸው ተሰብሯል፣ ከዚህ በኋላ አያንሰራሩምሲል የተናገረው አረፍተ ትዕቢት - "ነፍጠኞች የሠበሩን ቦታ ላይ ቆመን ነፍጠኞችን ሰብረናልወደሚለው አረፍተ-ከንቱ ማደጉ ያሳዝናል እንጂ የሳይንስ እድገት ማሳያ ጥበብ አይሆንም። ወያኔ ያበላሸውን ሥርዓት ዳግም ለማበጀት ግብረገብ ማስተማሩ እንጂ ማሳሳቱ ምን ይበጃልለዓመታት የተደከመባቸውን በጥቂት ደቂቃዎች በእሳት አጋይቶ ማውደም ሃይፐር ሶኒክ ጄት እንደ መሥራት የሚኮራቸውን ግፈኞች መክሮ ገስጾ መመለሱ እንጂ ማመጻደቁ ምን ይበጃል?እግዚአብሄር እኮ ሁሉን ያያል። አምላክ እኮ የምስኪኖች ዋይታ ይሰማል።

ባለፈው “ተከብቤአለሁ” ሳብያ የሞቱ ዜጎች ሃዘን ሳይወጣልን በሰሞኑ ጥቃት ሻሸመኔ እንደ ሶርያዋ አሌፖ ስትጋይ፣ ምስኪኖች እጅና እግራቸው ተቆራርጦ አቅመ ደካሞች ደግሞ በገጀራና ጦር ተሸቅሽቀው ተገድለዋል፣ አንድ ባለሉካንዳ ተገድሎ በሥጋ መስቀያ ሜንጫ ላይ ተንጠልጥሏል። ጥቃቱ ጅማንም መቷል። በሰሞኑ ፍጅት ባጠቃላይ ከ230ሰዎች በላይ ተገድለው ሌሎች 200 ያህል ሰዎች ቁስለኛና አካለ ጎዶሎ ሲሆኑ 250 መኪኖች ተሠባብረው፣ 20 ያህል ተቃጥለዋል። አረመኔዎች 35 ፎቆች እንዲሁም ከሺህ በላይ መኖርያ ቤቶች አቃጥለው ጨፍረዋል። በቦስንያ ጭፍጨፋ ሰው ተዘቅዝቆ አልተሰቀለም። አርመኖች ላይ በደል ሲፈጸም የሴት ልጆች ጡት አልተቆረጠም፣ ሰው ተዘቅዝቆ አልተሰቀለም። የአርሲ ነገሌውና የሻሸመኔው ውድመት ከሩዋንዳው እልቂት ጋር ሲነጻጸር እንኳን በዘግናኝነቱ ላቅ ይላል። የሰው ልጅ በፍቅርና በመተሳሰብ በሚኖሩባት የምድር ገነት ተብላ በምትወደሰው ኢትዮጵያ ኦነግ ሸኔ በአይዞህ ባዮቹ እየታገዘ ማንንም ሳይፈራ ጥቃት ፈጽሟል። እስላም ክርስትያን የሞሉባት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘግናኝ እልቂት መፈጸሙ እጅግ ያስለቅሳል።

መንግሥት የዘር ፍጅት ሲፈጸም፣ ጥብቅ ቁጥጥር ባለማድረጉ ተጠያቂ ነው። ግፈኞች ደሞዝ የሚከፈላቸው ባለሥልጣኖችና ሥርዓት አስጠባቂዎች ቆመው እንዲያዩ ቀጭን ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ፣ አራጆች ተባባሪዎቻቸውን ጠርተው ቤተ ክርስትያን ሲቃጠል፣ ዜጎች በገጀራ ሲሰቀሰቁ፣ ቤት ንብረት ሲጋይ፣ ትምህርት ቤቶች ሲቃጠሉ እገዛ እንዲያደርጉላቸው መመርያ ሲሰጧቸው መንግሥት መረጃ አልነበረውም ማለት አይቻልም። ሽብርተኞች ቤርጎና መኖርያ ቤት ተከራይተው እቅድ ሲነድፉና የሚገደሉ ሰዎች እንዲሁም የሚቃጠሉ ንብረቶችን ስም ሲመዘግቡ መንግስት አላውቅም ማለት አይችልም። መንግሥት እንደ መንግሥትነቱ ኃላፊነቱን አልተወጣም። ዛሬ በኦሮምያ ክልል የሚኖሩ አማሮች፣ የሸዋ ኦሮሞዎች፣ ትግራዋዮችና ጉራጌዎችን ጨምሮ መላው የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ስጋት ላይ ናቸው።

መንግሥትና የጸጥታ አስከባሪዎች ባሉበት ኦነግ ሸኔ ይህን ሁሉ መከራ መፈጸሙ ብዙ ጥያቄዎችን ይጭራል። ይህን ሁሉ ሰቆቃ የሚያስተውልስ እንደምን ቆም መሄድ ይችላል? “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” ማለትስ አሁን ነው። ምን እንላለን፤ ማንስ ሕይወታችንን ይታደገን፣ ማንስ ለፍትህ ይጩህ ። “አቤቱ ጌታዬ ከዘር ፍጅት (Genocide)፣ ከመዓቱ ሰውረን” ብቻ እንጂ።

Wednesday, January 24, 2018

“ተስፈኛው ባለሃብት” ከሚኪያስሙሉገታ

ተስፈኛው ባለሃብት” 
ከሚኪያስሙሉገ
ኢትዮጵያ ለፍተው ጥረው ኃብት ያካባቱ ሰዎች ነበሯት።  እነ አቶ ከድር ኤባና በቀለ ሞላ ለሃገራቸው ብዙ ከለፉ ባለጸጋዎች መካከል ነበሩ። ትልቁ ነገር ለፍተው ጥረው አንቱ የተባሉትም ሆነ የሕዝብ ኃብት መዝብረው የከበሩ፣ ኃብቶቻቸው በስሞቻቸው ወይንም በልጆቻቸው ወይን በዘመዶቻቸው የተመዘገቡ ነበሩ። ዛሬ ለየት ይላል።
ገና አስቀድሞ አምባገነንነትን ለመጣል ታገልን የሚሉት በብዙ ሺህ የትግራይ ልጆች ደም ተረማምደው መዲና ከተማዋን አዲስ አበባን የተቆጣጠሩት “ተጋዳላዮች” ዋነኛ ዓላማቸው የሃገሪቱን ኃብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ነበር። ኤፈርት የተባለው በሕጋዊ መንገድ የተመዘገበው ትልቅ ኮርፖሬሽን ዋነኛ ሥራው የቱባ ባለስልጣናትን ኃብት ማጠራቀም ሲሆን ሌላኛው ስልት ደግሞ ሕንጻውን፣ የኮንስትራክሽንና የትራንስፖርት ድርጅቶችን፣ ፋብሪካውን፣ ሆቴሉን፣ እንዱስትሪውን፣ የቡናና ጫት ንግዱን፣ ጉዲፈቻውን፣ ወዘተ፣ በማይታወቅ ሰው ስም አዙሮ መቆጣጠሩ ነው። ይህ የነሱን ኃብት በስሙ አስመዝግቦ የባርነት አደራውን የሚወጣው “ተስፈኛ” ኃብታም ቢመስልም ኃብታም እንዳልሆነ ውስጡ ያውቀዋል። በሰው ፊት ቸርና ለጋሽ ሆኖ የመቅረቡ ስልታዊ አካሄዱ ደግሞ ስለሚያሳፍረው ዓዕምሮውን አንካሳ አድርጎታል።
ኃብት ደክመው ለፍተው ሲያገኙት እርካታን ይሰጣል። በንጉሡና በደርግ ዘመን በሙሰናና በዓየር ባየር ገንዘብ ያካብቱ ኃብታሞች ቢኖሩም እንኳን እንዲህ እንደዛሬው አሳፋሪ ደረጃ ላይ አልደረሰም ነበር። በንጉሡ ዘመን የነበሩት ጥቂት በንጉሡ ልጆች ወይም በከፍተኛ ባለሥልጣኖች ተይዘው የነበሩ ኃብቶች በቀላሉ ተወርሰዋል። በደርግ ዘመን ባለሥልጣናት በራሳቸውም ይሁን በሌሎች ስም ያስመዘገቡት ኃብት እንደነበር ብዙም አልተነገረም። እንደውም አብዛኛዎቹ ባለስልጣናት መኖርያ ቤት እንኳን አልነበራቸውም ይባላል።
ዛሬ ሙስናን መዋጋቱ ከባድ የሆነው በርካታ ትላልቅ ተቋሞችና ድርጅቶች “በተስፈኞች” ስም ተመዝግበው መያዛቸው ነው። ወይዘሮዋ  “ኃብት በስሜ ከተገኘ ይወረስ” ያሉት ከኤፈርት ውጭ ያለውን ጠቅላላ ኃብታቸውን በሚያምኗቸው ተስፈኞች ስም ስላስቀመጡ ነው። ቢሆንላቸው አብዛኛዎቹ ባለሥልጣናት የሥራ መልቀቅያ እያስገቡ ኃላፊነታቸውን ቢለቁና ቻይና ሄደው ያካበቱትን ቢበሉ ደስተኞች ነበሩ። እነሱም እኮ ሰው ናቸው፣ ትግሉ በፈረጠመ ቁጥር ይሰጋሉ። ከዚህ ቀደም አስራ ሰባት ዓመት በጦርነት ኋላም ሃያ ስድስት ዓመት አዲስ አበባ ውስጥ ሲኖሩ እንደ ሂሳብ ሹም በተለያዩ ሰዎች ያስመዘገቡትን የሙስና ኃብቶቻቸውን ቀንና ሌት ሲቆጣጠሩ ዓዕምሯቸው ባክኗል። የቀድሞዎቹ “ተጋዳላይ” የዛሬዎቹ “አካውንታንት” የሙስና ኃብቶቻቸውን ኃብት በአደራ የሰጡትን ተስፈኛ እስከመርሳት የደረሱም አሉ። 
ነገ አደራውን የሚረከበው መንግሥት በሙስና የተገነቡ ንብረቶች ወደ መንግሥት ኃብትነት ማዞሩ እጅግ ይከብደዋል። ከቱባው ሙሰኛ ባለስልጣን ጀርባ ያሉትን “ተስፈኞች” ለማወቅ የግለሰቦችን የኋላ የገንዘብ ታሪክ ማጥናቱ ራሱ ትልቅ ሥራ ነው። ቀድሞ “ጋሪ ነጂ” ወይንም “ሱቅ በደሬቴ” የነበረ ጮሌ ሰው ባለትልቅ ፋብሪካ ሊሆን ይችላል። የዚህን ዓይነቱን ሰው የኃብት ክምችት ማጣራቱ ቀላል ሊሆን ቢችልም የሁሉንም ተስፈኞች ኃብት ማጣራቱ ደግሞ ሁሌም ቀላል ሊሆን አይችልም። በርካታ ኃብቶች ወደ ዶላርና ወርቅ እየተለወጡ ወደ ውጭ ሃገር ወጥተዋል። በውጭ ሃገራትም ሃብታም የሆኑ “ስውር ተስፈኞች” አሉ። ይህን ሁል ማጣራቱ ቀላልም ከባድም ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ እንዲህ ተመዝብራ፣ ሙሰኞች እንዲህ ቀልደውባት አያውቅም።
ተስፈኛው ባለኃብት” ኃብታም ለመባል በተስፋ የሚኖር ተላላ ነው። በስው ፊት ቸርና ለጋሽ በመምሰል አክብሮትን የሚፈልገው ተስፈኛ ዋነኛው የኃብቱ ምንጭ የሆነው ቱባው ባለስልጣን የሚሰነዝርበት ቁጣና ዘለፋ ደግሞ ያኮስሰዋል። “አንተ፣ ዋ፣ ገንዘቤን መጫወቻ አደረከው አይደል” የሚለው በየቀኑ በስልክ የሚሰማው የቱባው ሙሰኛው አለቃው ድምጽ ያስበረግገዋል። ሰዎች ኃብታም እየመሰላቸው በየምርቃቱና ስብሰባው የሚጋብዙት ይህ “ተስፈኛ” እየዛቀ የሚለግሰው ገንዘብ ጭብጨባ ብቻ አይደለም ታላቅ ቁጣና ዛቻንም ያስከትልበታል። እንደ አውሮፕላን የምትበር ዘመናዊ መኪና የገዛው “ተስፈኛ” ከፊት ለፊቱ በርካታ ሰዎችን ሲመለከት ልቡም እንዲሁ በስጋት ትበራለች። ታድያ ሙስና ላይ የሚደረገው ውጊያ እንዲከሽፍ በማድረግ ረገድ ደግሞ ከቱባው ሙሰኛ ባለሥልጣን የበለጠ ትግል ያደርጋል። ተስፈኛው ለሙሰኛ ገዢ ኅልውና ሲል በጽናት የሚታገል ባርያ ነው። የዚህ ዓይነቱ የመደብ ትግል በታሪክ የመጀመርያው ነው።
የተስፈኛ የምጣኔ ኃብት ዘርፍን የፈለሰፈው ሂትለር ባይሆንም እንኳን እርሱ ግን በከፍተኛ ደረጃ በሥራ ላይ አውሎታል። ሂትለር ከእስራኤሎች ተሰብስቦ በአራት ማዕዘን እየተጠፈጠፈ ያሰራውን ወርቅ ስማቸው ለማይታወቅ ሰዎች አድሏል። እነዚህ ተስፈኞች በሂትለር የመጨረሻዎቹ የጭንቅ ሠዓታት ወደ ውጭ ሃገር በተለይም ወደ ደቡብ አሜሪካ ሸሽተዋል። እነዚያ ሰዎች እስከቅርብ ቀን ድረስ እየታደኑ ቢያዙም እስካሁን ያልታወቀ ኃብትም በወራሾቻቸው ስም በየሃገሩ ይገኛል። 
ተስፈኛው ባለሃብት” ኃብታም ለመሆን ሲል ባዶ ተስፋን ሰንቆ የሙሰኛን ኃብት ተሸክሞ የሚዞር “ማሞ ቂሎ” ሰው ነው። የሱ ያልሆነው ኃብት በህልሙ የሱ ይመስለዋል። ሲነቃ ደግሞ ባዶው ተስፋ ስጋትን ያሳድሩበታል። “ተስፈኛው ባለሃብትን” ከዚህ ሁሉ ጭንቀት የሚገላገለው እውነቱን ተናግሮ ኃብቱን ወደ ሕዝብ ንብረትነት ሲያዞር ብቻ ነው። በቸር ያውለን።

(ኢሳት ዜና ጥር 15 ቀን 2010 ዓም) የፓለቲካና የሕሊና እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ጥፋተኞቹም በህግ እንዲጠየቁ ሲል ለኮንሶ ሕዝብ መብት የሚታገሉ ሃይሎች ገለጹ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የኮንሶ ሕዝብ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች ኅብረት በህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ካለጥፋታቸው ተወንጅለው በእስር የሚማቅቁ የፓለቲካና የሕሊና እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቁ ጠይቋል። ከህግ አግባብ ውጪ በዜጎች ላይ እስራትና ግድያ ጨምሮ የተለያዩ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ የስርዓቱ ባለስልጣናትና ትእዛዙን ተቀብለው ወንጀሉን የፈጸሙ ግለሰቦችና ተቋማት ተለይተው በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ወንጀለኞቹ ተለይተው ጉዳያቸው በገለልተኛ አጣሪ አካል ተመርምሮ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል ታጋዮቹ አሳስቧል። ስርዓቱ ሁሉንም እስረኞች ለመልቀቅ የገባውን ቃል በማጠፍ 52 የአካባቢው ተወላጆች ብቻ ክሳቸው ተቋርጦ በይቅርታ ስም እንዲፈቱ በማድረግ ትግሉን ለማዳከም አገዛዙ የሚያደርገው ሙከራ እንደማይሳካም ገልጸዋል። የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ፣ ምሁራን፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የባህልና የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ቁጥራቸው ከ400 በላይ ሰላማዊ ዜጎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብሎአል። ይህም አገዛዙ ለሕዝብ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብሏል መግለጫው። የኮንሶ ተወላጆች ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በጋራ በመሆን ይህን አምባገነን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመጣል ሁሉንም ያሳተፈ ስርዓት እስኪፈጠርና የወያኔ ግብአተመሬት እስኪፈጸም ትግላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ባለፈው ሳምንት አገዛዙ በኮንሶ ግጭት ምክንያት ከታሰሩት ውስጥ 52 ሰዎች ክሳቸው ተቇርጦ በምህረት ወይም በይቅርታ እንደምፈቱ ቢገልጽም፣ የተፈቱት ሰዎች አንዳንዶቹ የተፈረደባቸውን ጊዜ የጨረሱ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ የተፈቱት በይቅርታ ወይም በምህረት ሳይሆን በዋስ ነው። አንዳንዶቹ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየተጠየቁ እንደሆነም ከቤተሰቦቻቸው ለማወቅ ተችሎአል። አሁንም ድረስ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
(ኢሳት ዜና ጥር 15 ቀን 2010 ዓም) የፓለቲካና የሕሊና እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና ጥፋተኞቹም በህግ እንዲጠየቁ ሲል ለኮንሶ ሕዝብ መብት የሚታገሉ ሃይሎች ገለጹ
ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የኮንሶ ሕዝብ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች ኅብረት በህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ካለጥፋታቸው ተወንጅለው በእስር የሚማቅቁ የፓለቲካና የሕሊና እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲለቀቁ ጠይቋል።
ከህግ አግባብ ውጪ በዜጎች ላይ እስራትና ግድያ ጨምሮ የተለያዩ የመብት ጥሰቶችን የፈጸሙ የስርዓቱ ባለስልጣናትና ትእዛዙን ተቀብለው ወንጀሉን የፈጸሙ ግለሰቦችና ተቋማት ተለይተው በህግ ሊጠየቁ ይገባል። ወንጀለኞቹ ተለይተው ጉዳያቸው በገለልተኛ አጣሪ አካል ተመርምሮ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ሲል ታጋዮቹ አሳስቧል።
ስርዓቱ ሁሉንም እስረኞች ለመልቀቅ የገባውን ቃል በማጠፍ 52 የአካባቢው ተወላጆች ብቻ ክሳቸው ተቋርጦ በይቅርታ ስም እንዲፈቱ በማድረግ ትግሉን ለማዳከም አገዛዙ የሚያደርገው ሙከራ እንደማይሳካም ገልጸዋል። የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ፣ ምሁራን፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የባህልና የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ቁጥራቸው ከ400 በላይ ሰላማዊ ዜጎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ብሎአል። ይህም አገዛዙ ለሕዝብ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብሏል መግለጫው።
የኮንሶ ተወላጆች ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በጋራ በመሆን ይህን አምባገነን ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመጣል ሁሉንም ያሳተፈ ስርዓት እስኪፈጠርና የወያኔ ግብአተመሬት እስኪፈጸም ትግላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ባለፈው ሳምንት አገዛዙ በኮንሶ ግጭት ምክንያት ከታሰሩት ውስጥ 52 ሰዎች ክሳቸው ተቇርጦ በምህረት ወይም በይቅርታ እንደምፈቱ ቢገልጽም፣ የተፈቱት ሰዎች አንዳንዶቹ የተፈረደባቸውን ጊዜ የጨረሱ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ የተፈቱት በይቅርታ ወይም በምህረት ሳይሆን በዋስ ነው። አንዳንዶቹ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ እየተጠየቁ እንደሆነም ከቤተሰቦቻቸው ለማወቅ ተችሎአል። አሁንም ድረስ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Thursday, November 16, 2017