Tuesday, February 3, 2015

Documentary:U.S Policy:ETHIOPIA A FAILED STATE!

ሰበር ዜና
የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ሚዲያ አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊ አለመሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ

የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ሚዲያ አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊ አለመሆኑን ሰማያዊ ፓርቲ ገለጸ

ጥር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ያወጣው ረቂቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ውድድር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰዓት አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን አስታውቋል።
ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችን በረቂቅ የሰዓት ድልድሉ ላይ ጊዮን ሆቴል ጋብዞ ውይይት አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ኃላፊዎች ባቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዲያ አጠቃቀም ረቂቅ ድልድል መሰረት 55 በመቶ በፓርላማ መቀመጫ ወንበር ላላቸው ፓርቲዎች፣ 20 በመቶ ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው ዕጩዎች ብዛት እንዲሁም ቀሪ 25 በመቶ ለሁሉም ፓርቲዎች በዕኩል የሚከፋፈል እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል በውይይቱ ላይ የተገኙት የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ  የሚዲያ ሰዓት አጠቃቀም በሚቀርቡ እጩዎች ብዛት እና በእኩልነት የሚከፋፈል የድልድል መስፈርት መሆን ሲኖርበት የፓርላማ መቀመጫ እንደመስፈረት መቀመጡ ትክክል አለመሆኑን ለኢሳት ገልጸዋል ኢህአዴግ የድልድሉ መስፈርት ላይ እንደሚስማማ በመግለጽ፣ በመቶ የተቀመጠው መጠን ላይ ግን መሻሻል እንዲደረግ እንደሚፈልግ መግለጹንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

Wednesday, January 28, 2015

www.goolgule.com

አንድነት በደጋፊዎቹ ላይ “አረመኔያዊ” ያለው ድብደባ መፈፀሙን ተናገረ

አንድነት “አሁንም እሰለፋለሁ” ይላል፤ አስተዳደሩ “አይቻልም” ይላል
sileshi
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ሕጋዊ በሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ሊሣተፉ በወጡ አባሎቼና ደጋፊዎቼ ላይ በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ ሲል ከስሷል፡፡
ፓርቲው በሌሎች ከተሞች የጠራቸው ሰላማዊ ሰልፎች ንግ በስኬት መጠናቀቃቸውን ገልጿል፡፡
ከፖሊስ ምላሽ አለማግኘቱን አዲስ አበባ ላይ የተጠናቀረው የመለስካቸው አምሃ ዘገባ ይናገራል፡፡
ለዝርዝሩ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡
የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ያጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ
በሌላ በኩል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ አስተዳደር ግን ከተማይቱ ውስጥ የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ይካሄዳል በማለት ሰልፉ እንዳይደረግ አሳስቧል፡፡
ባለፈው ሣምንት ፖሊስ አባሎቼ ላይ አካሄደ ያለውን ከባድ ድብደባ ለሚመለከታቸው ገለልተኛ አካላት እና ለዓለም ማኅበረሰብም እንደሚያሳውቅ አንድነት ገልጿል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡ (ምንጭ: አሜሪካ ድምጽና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ)