Sunday, May 4, 2014
Friday, May 2, 2014
Thursday, May 1, 2014
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።
ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋል። ኦህዴድ በወያኔ ቅጥረኛነት የኦሮሚያ ወጣቶችን በማስጨፍጨፍ ላይ ያለ እኩይ የአድርባዮች ስብስብ ነው። ወጣቶች የተቃወሙት ይህንን ነው።እነዚህ ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባቸዋል። ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል። የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል ያገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ ያገባናል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድ ጥሪ ያደርጋል። በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።
የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይን ያነሱ ወጣቶች ብቻ አይደሉም። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ናቸው። ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ ካለቀ በኋላም አልተፈቱም። ይህ ሰቆቃ ማብቃት አለበት።
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም፤ ወያኔ ይወገድ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
Friday, April 4, 2014
ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ!
መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?
የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው “እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!” በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።
በመንገዶች ላይ ጥቂት በጫት የሚነዱ መኪናዎች በመቶ የሚቆጠሩ መኪናዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ይችላሉ፤ ሲያደርጉም በየቀኑ እየታየ ነው፤ በማኅበረሰባዊና በፖሊቲካ ግንኙነትም አንድ ሰው የሚዘራው መርዝ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት ፍጥነት የማኅበረሰቡን አባላት ያዳርሳል፤ እንቆቅልሹ እንደሚለው ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! ማለት መርዝ፣ እሳት፣ ተላላፊ በሽታ በሕዝቡ ላይ ማሰራጨት ከአምስትና ከአሥር ዓመታት በኋላ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም።
ድብብቆሽ አይጠቅምም፤ሁለት ነገሮችን በግልጽ ማውጣት አለብን፤አንደኛ በአሜሪካና በአውሮፓ መሽጎ ፍርሃቱንና ሽቁጥቁጥነቱን ለመሸሸግ መርዙን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚረጨው ለምንድን ነው? አገዛዙ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያት ግልጽ ነው፤ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ነው፤ ከአገዛዙ ጋር በሚደረግ ትግል ከታች ሆነው ከሥልጣን ውጭ የሆኑ ዜጎች በሥልጣን ላይ ከተቀመጡት ጋር እየተቆራቆዙና እየተጋጩ ናቸው፤ ይህንን እኔ የላይና-የታች ግጭት (vertical conflict) የምለው ነው፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር የሚደረገው ትግል ይህ ነው፤ ይህንን ለማክሸፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ ትግሉን ከላይና-ታች አውጥቶ ወደጎን-ለጎን ግጭት (horizontal conflict) ሊለውጠው ይፈልጋል፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ ሰዎችም ትግሉን ጎን-ለጎን ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው።
የፖሊቲካ ትግልን የሚመሩ ሰዎች በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት ስሜት እየተሳቡ ትግሉን የላይና-የታችነቱን ጠብቀው በተደራቢነት የጎን-ለጎን ትግሉን ይጨምሩበታል፤ ይህ ሲሆን ሀሳብ፣ ጉልበትና ሀብት ይከፋፈላል፤ ይበታተናል፤ ወደዓላማ ለመድረስም ያስቸግራል፤ ወያኔ ወደመጨረሻው ላይ ኢሕአዴግ ብሎ የሰየመውን ቀፎ አስቲፈጥር ድረስ በስሙ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚያነሣ ነገር አልነበረውም፤ ወያኔን ለድል ያበቃው የማታለያ ስሙ እንደሆነ በበኩሌ አልጠራጠርም፤ ከሃያ ሁለት ዓመታት የጎሣ ሥርዓት በኋላ ኢትዮጵያ ቆስላለች እንጂ አልሞተችም፤ የአሐዝ ማስረጃ ለማቅረብ ባልችልም በብዙ ጎሣዎች መሀከል ጋብቻ እንደዱሮው እየቀጠለ ነው፤ ይህንን የቆየ የዝምድና ሰንሰለት ለመበጠስ የሚጥሩም አሉ።
ኒው ዮርክ ተቀምጦ ትኩስ ውሻ (ሆት ዶግ!) እየበላ ለእስላም ኦሮሞዎች የመገዳደያ መመሪያ የሚሰጥ ሰው የመንፈስ ጤንነቱን እጠራጠራለሁ፤ ይህንን የኒው ዮርክ ቀረርቶ ተከትሎ ሌላ የመጠላለፍ አዋጅ ሰማን፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ለአጼ ምኒልክ ስለዘፈነ ከበዴሌ ቢራ ፋብሪካ ጋር ለማስታወቂያ የገባው ውል ሥራ ላይ ከዋለ የበዴሌን ቢራ አንጠጣም ተባለና ማስታወቂያው ተሰረዘ ይመስለኛል፤ ማን እንዳሸነፈ ወደፊት ጊዜ ይነግረናል፤ አሁን ደግሞ ሌላ ማዘዣ ሰማሁ፤ “የስ” በሚለው ውሀ ጠርሙስ ላይ እንስራ የተሸከመችው ኮረዳ መስቀል አድርጋ ነበር፤ ልጅቱ ከነመስቀልዋ የምትታይበትን ውሀ እስላሞች አንገዛም ስላሉ ነጋዴዎቹ መስቀሉን አወለቁባት! ይህንን ማዘዣ ላወጣው አክራሪ እስላም ወረባቦ ቅዳሜ ገበያ ሄዶ እንዲጎበኝ አሳስበዋለሁ፤ ዛሬ ተለውጦ እንደሆነ አላውቅም እንጂ እኔ ብዙ ጊዜ ተመላልሼ እንዳየሁት የወረባቦ ኮረዶች ሁሉ ትልልቅ መስቀል በአንገታቸው ላይ ይታይ ነበር፤ መስቀል የእምነት መግለጫ ይሆናል፤ አያጠራጥርም፤ ግን መስቀል ጌጥም ይሆናል! መስቀል የናዚ ምልክትም ሆኖ ነበር! ለማናቸውም የዚህ ዓይነቱን መጠላለፊያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገምዱ ሰዎች ዓላማቸው ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ፍቅርንና ሰላምን ለማደፍረስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊ ትምህርት ክፉን በክፉ አትመልሱ ነውና ለተበጠሰው መስቀል አጸፋውን ለመመለስ ማሰብ አይገባም።
ከኒው ዮርክ የተሰማው ቀረርቶም ሆነ የመስቀል ማስወለቁ ጉዳይ የተከሰተበትን ጊዜ ልብ ልንለው ይገባል፤ እስላሞች ስለነጻነት የሚያደርጉት ንቅናቄ በጣም እየጋለ በመሄድ ላይ እያለ ክርስቲያኖችም የዜግነት ግዳጃቸው አድርገውት ድጋፋቸውን በሚሰጡበት ጊዜ ነበር፤ ይህ መሆኑ ጥርጣሬን ይጋብዛል፤ የገጠመውን የእስላሞችና የክርስቲያኖች ሰልፍ በማደፍረስ ወይም በመክፈል የሚጠቀም ማን ነው? የሚጎዳውስ ማን ነው? ሁሉም የትግል አጋፋሪዎች ለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ክብደት ቢሰጡት ትግሉ በጎን-ለጎን እንዳይሄድና እንዳይዳከም ይረዳል፤ ከዚያም በላይ አክራሪነት የሚባለውና የሚያስከትለውም ሽብርተኛነት የሚመጣው እንዲህ እያለ ነው፤ እግዚአብሔር ከዚያ ያውጣን!
ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006
መጋቢት 2006
(ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog)
Sunday, March 30, 2014
ጎሠኛነትና ሽብርተኛነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
ጎሠኛነትና ሽብርተኛነት (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)
March 29, 2014
የጎሠኛነት አጭር ትርጉም ዓለምን በራሱ ጠባብ ኢምንትነት የሚለካ ሰው ነው፤ ለኪው መለኪያው ነው፤ መለኪያውም ለኪው ነው፤ ጎሠኛነት የዘረኛነት የባሕርይ ልጅ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት መሠረታቸው ድንቁርና ነው፤ የድንቁርናው ዓይነተኛ መገለጫ ‹‹ንጹሕ›› የሚለው ቃል ነው፤ ለዚህ ዋና ምስክር አድርጌ የማቀርበው አዶልፍ ሂትለርን ነው፤ ስለ‹‹አርያን ዘር›› ማንነትና ‹‹ንጹሕነት›› የሂትለር Mien Kampf የሚለውን መጽሐፍ ነው፤
የሰው ልጆች ባህል የሚባለው ሁሉ፣ ዛሬ የምናየው የሥነ ጥበብ፣ የሳይንስና የሳይንስ ጥበብ (ቴክኖሎጂ) ውጤት ሁሉ የአርያን ዘር የፈጠራ ውጤቶች ናቸው፤ … ‹ሰው› የሚባለውም እሱ ብቻ ነው።
የሂትለር ዘረኛነት የሰውን ልጅ ሁሉ ጉድጓድ ውስጥ ከተተው፤ አርያኑን ከንጹሕ የሰው ዘርነት ወደብቸኛ የሰው ዘርነት አሸጋገረው፤ ይህ ንጹሕ ድንቁርና ነው፤ የጎሠኞችም መነሻና መድረሻ፣ መንገዱም ይኸው ነው፤ በቅርቡ በፌስቡክ ላይ የታየው የቋንቋ ንጽሕና ክርክር የዚሁ የዘረኛነትና የጎሠኛነት ድንቁርና ቅጥያ ነው፤ ስለቋንቋዎች ባሕርይ ምንም ዓይነት እውቀት ሳይኖረው ቋንቋውን በማንገሥ እሱ ራሱ የነገሠ እየመሰለው ይደሰታል፤ ዓባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል እንደሚባለው፤ ሙት ቋንቋ ካልሆነ በቀር ቋንቋ እንደሰው ልጅ ይጋባል፤ ይዋለዳል፤ ይለወጣል፤ በ1944 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ጊዜ አገር ለማየት ከአዲስ አበባ የወጣሁት በጣልያን ትሬንታ ኳትሮ (34) ከባድ የዕቃ መጫኛ መኪና ላይ ተጭኜ ነው፤ ደብረ ማርቆስ ስገባ የሚናገሩት አይገባኝም ነበር፤ እኔ ከለመድሁት የሸዋ አማርኛ ጋር በጣም የተራራቀ ነበር፤ ወሎም ሄጄ አንደዚያው ነበር፤ ዛሬ ከስድሳ ዓመታት በኋላ ሌላ ነው፤ ዘረኛነትም ሆነ ጎሠኛነት የእውቀት፣ የመሻሻልና የእድገት ጸር ነው፤ ቆሞ-ቀር ነው፤ የአእምሮው እይታ አጠገቡ ካለው ወንዝና ጉብታ አያልፍም፤ ራሱ በፈጠረው ግርዶሽ መተናፈሻውንና መንቀሳቀሻውን ያጠበበ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ!
ዘረኛነትና ጎሠኛነት ከስጋትና ከፍርሃት የመነጨ ነው፤ አልጋው ፍርሃት፣ ትራሱ ስጋት ስለሆነ ጭንቀቱ እያባነነው እንቅልፍ አይወስደውም፤ ሲያቃዠው ያድራል፤ ለየት ያለና ትንሽም ሻል ያለ ነገር ሲያይ ሆን ብሎ እሱን ለማኮሰስ ወይም ለማሳነስ የመጣበት እየመሰለው ይደነግጣል፤ ስለዚህም ከሱ የተሻለውን በማጥፋት እሱ ወደትልቅነት የሚሸጋገር ይመስለዋል፤ ስለዚህም ዘረኛነትና ጎሠኛነት የሽብርተኛነት ምንጭ አንዱና ዋናው ምክንያት ከሱ የተለየውን ለማጥፋት ያለው ዝንባሌ ነው፤ ዘረኛነትና ጎሠኛነት ልብን በጥላቻ ያቆሽሻል፤ አእምሮን በክፋት እየመረዘ ያደነዝዛል፤ ሰውነትን ወደርኩስ መንፈስነት ይለውጣል፤ በባነነና በቃዠ ቁጥር የሚታየው ማታለል፣ ማጥፋት፣ ማፍረስ፣ ማዋረድ፣ ማጎሳቆልና ማደህየት ብቻ ነው፤ ለዘረኛና ለጎሠኛ እድገት ማለት የሌሎች መቀጨጭና መሞት ነው፤ ማደህየት፣ ማሰቃየት፣ ማቀጨጭና መግደል፣ ንብረትንም ማውደም የሽብርተኛነት መገለጫው ነው፤ የሽብርተኛነት ማለትም የዘረኛና የጎሠኛ የደነዘዘ አንጎል ጥፋትን እንደልማት፣ መቀጨጭን እንደእድገት ይመለከታል።
የዘረኛና የጎሠኛ ሽብርተኛነት የሚፈጥረው የደነዘዘ አንጎል ራስንም አይምርም፤ ለራሱ ልጆችና ቤተ-ዘመዶች አያስብም፤ በዙሪያው ያለውን ከሱ የተለየ ዓለም በሙሉ ወደአንጠርጦስ ሲከታቸው የሱም ወገኖች አብረው አንጦርጦስ ቢወርዱ ግድ የለውም! አይጸጽተውም! የተረፉት በሙታኑ መቃብር ላይ አሸብርቀው ሕያዋን መስለው ይታያሉ፤ እነሱ ባያዩትም የቆሙበት መቃብር ጠርንፎ ይዟቸዋል፤ ሕያዋኑና ሙታኑ ተቆራኝተዋል፤ ሙታኑ በተፈጥሮ ሕግ ይበሰብሳሉ፤ ሕያዋን የሚመስሉት በገዛ ሥራቸው ይበሰብሳሉ።
ዘረኛም ሆነ ጎሠኛ ሂሳቡ ምንጊዜም ጅምላ ነው፤ የዘረኛነትም ሆነ የጎሠኛነት የደነዘዘ አንጎል የሚያየው ጅምላ ነው፤ የጥፋቱ ሁሉ መሠረት የሚሆነውም ጅምላውን ደፍጥጦ አንድ አድርጎ ማየቱ ነው፤ ስለዚህም ጥፋቱ ጅምላ ነው፤ የሽብርተኛነት ሂሳብም ጅምላ ነው፤ ዘረኛም ሆነ ጎሠኛ ወይም ሽብርተኛ ራሱንም የሚያየው የጅምላ አካል አድርጎ እንጂ ራሱን የቻለ ነጻ ሰው አድርጎ አይደለም፤ ብቻውን አይደለም፤ ራሱን የሚያየው በጅምላ ከሌሎች መሰሎቹ ከሚላቸው ጋር ነው፤ ከአሱና ከመሰሎቹ የተለዩ ግለሰቦችንም ሲያይ በነጠላ ሳይሆን በጅምላ ነው፤ ለዚህ ምክንያት አለው፤ ራሱን በጅምላ የሚያየው ምሽጉ ውስጥ ሆኖ ከፍርሃት ነጻ ለመሆን ነው፤ ከእሱ የተለዩትንም በጅምላ የሚያየው ሁሉም ኢላማ ስለሆኑ ነው፤ ይህንን ሁነት በትክክል ለመገንዘብ አንድ ሀ ና ለ የሚባሉ ጎሣዎች አሉ እንበል፤ እነዚህ ጎሣዎች ውስጥ ሁ፣ ሂ፣ ሃ፣ ሄ፣ ህ፣ ሆ የሚባሉ አባሎች አሉ፤ ደግሞም ሉ፣ ሊ፣ ላ፣ ሌ፣ ል፣ ሎ የሚባሉ አባሎች አሉ፤ በትክክል ማሰብ የሚችል ሰው ሁሉ በአንዴ እንደሚገነዘበው ሉ የአንዳቸውንም የሌሎቹን የለ ጎሣ አባሎች ተግባር ሊፈጽም አይችልም፤ ሌሎቹም ሉ ን ሊሆኑ አይችሉም፤ የዘረኛና የጎሠኛ መሠረታዊ ድንቁርና እነዚህን ልዩነቶች ማየት ሳይችል በ‹ሀ› በ‹ለ› መሀከል ያለው ልዩነት በጣም ጎልቶ ይታየዋል፤ የድንቁርናውም፣ የጥላቸው፣ የፍርሃቱም፣ የክፋቱም፣ የተንኮሉም፣ የሽብርተኛነቱም መነሻ ይኸው ራሱን ማሰብ እንደሚችል ሰው ያለዘር ወይም ያለጎሣ ምርኩዝ መቆም የማይችል ዝልፍልፍ ደካማ መሆኑ ነው።
በድንቁርናው ከዝልፍልፍነትና ከደካማነት ያወጣኛል ብሎ የመረጠው መንገድ የጎሣ ምሽጉ ውስጥ ገብቶ በ‹ሀ›ና በ‹ለ› መሀከል ያለውን ልዩነት መስበክ ነው፤ በ‹ሀ› ውስጥ ያለ ጎሠኛ በ‹ሁ›ና በ‹ሂ› መሀከል ያለው ልዩነት፣ በ‹ለ› ውስጥ ላለ ጎሠኛም በ‹ሉ›ና በ‹ሊ› መሀከል ያለው ልየነት አይታየውም፤ ስለዚህም ድንቁርናው ከጥላቻውና ከክፋቱ ጋር እየተጋገዘ ወደቀላሉ የጅምላ ውሳኔ ይመራዋል፤ የሽብርተኛነትም ዋናው የድንቁርና ዘዴ ጥፋት በጅምላ ነው።
በዘረኞችና በጎሠኞች አመለካከት አንድም አህጉር ውስጥ የተለያዩ ሰዎች አይኖሩም ነበር፤ የትም ቦታ ቢሆን ሰዎች እንደሰዎች እየተገናኙ እየተፋቀሩ አይጋቡምና አይዋለዱም ነበር፤ በደቡብ አፍሪካ የነጮች ዘረኛ አገዛዝ ‹የክልሶች ክልል› አይፈጠርም ነበር፤ የሰው ልጅ ሰው ሲሆን የሚያደርገው ያስደንቃል፤ በአንድ የአውሮፓ አገር አንድ ወያኔን እንደክፉ በሽታ የሚጠላ ሰው አውቃለሁ፤ ሚስቱ ወያኔ ነች! በአፍሪካ አዳራሽ ይሠራ የነበረ አንድ ግብጻዊ አውቃለሁ፤ ሚስቱ የአሜሪካን ይሁዲ ነበረች! እስክንድር ነጋ ሚስቱ ትግሬ ነች፤ ርእዮት ዓለሙ ጓደኛዋ ትግሬ ነው፤ የሰው ልጅ ሰውነቱን የሚያሳየው ለራሱ አስቦ፣ ከጅምላው ወጣ ብሎ ለብቻው ሲቆም ነው፤ ስለዚህም ለሽብርተኛነት ተፈላጊ የሆነው ነገር ሁሉ ድንቁርናም ሆነ ጥላቻና ክፋት ከጅምላ አመለካከት ጋር ርእዮትና እስክንድር የለባቸውም ብሎ በእርግጠኛነት ለመናገር ይቻላል፤ ስለከሳሾቹ ሳይታለም የተፈታ ነው፤ እነሱው ይናገሩታል፤ ደፍረው የማይናገሩት አሸባሪነታቸውን ብቻ ነው።

Subscribe to:
Posts (Atom)